PR Department Getachew
23/05/2022
10/12/2021
፟ በስነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ ፟
የባለስልጣኑ አመራርና ሠራተኞች ዓለማቀፉን የፀረ- ሙስና ቀን ህዳር 30/ 2014 ዓ/ም በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አከበሩ።
የባለስልጣን መ/ቤቱ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው በዚሁ በዓል ላይ ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጂነር ባልቻ ሬባ እና ም/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሚሊዮን ሃይለሚካኤል እንዲሁም አጠቃላይ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ዋና ዳይሬክተሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሙስና ሀገራት ሊያገኙ የሚገባቸውን ጥቅም የሚያሳጣና ዕድገትን የሚፈታተን በመሆኑ አጥብቀን ልንጠላውና ልንርቀው እንደሚገባ ገልፀው ሁላችንም እንደመንግስት ሰራተኛ የአገልጋይነት መንፈስን በመላበስ ህብረተሰቡን በንፁህና ቅን ልቦና ማገልገል አለብን ብለዋል።
የባለስልጣን መ/ቤቱ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሠለሞን ኪዳኔ ከሙስና ጋር የተያያዘ ሰፊ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሙስና ሀገራቀፍ ብቻ ሳይሆን በዓለማቀፍ ደረጃም የልማትና የዕድገት ፈተና ሆኖ እንደቀጠለ ያለ መሆኑን ገልፀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ሀገራት የህግ ማዕቀፎቻቸውን ተግባራዊ በማድረግና ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ በማፍራት ሊከላከሉትና በእጅጉም ሊቀንሱት እንደሚችሉ አብራርተዋል።
ከቀረበው ሰነድ በማስከተልም ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በዋና ዳይሬክተሮቹና የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
በመጨረሻም አጠቃላይ ሠራተኞቹና አመራሮቹ ምዕራባውያን በኢትዮጵያና በአፍሪካም ላይ መልሰው ሊጭኑት የሚፈልጉትን እጅ የመጠምዘዝና እኛ የምንለውን ብቻ ስሙ ጩኸት ለማስቀልበስ በዓለማቀፍ ደረጃ ሲካሄድ በቆየው # በቃ ( # No more) ንቅናቄ መቀላቀላቸውን በይፋ አሳውቀዋል።
Welcome to Ethiopian Communications Authority official face book page
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa
1000
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |