Sololo Intercept

Sololo Intercept

Share

11/11/2025
17/10/2025

ኢቢሲ በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አዲስ ሪፖርት ዙርያ ያሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2025 ከሰሀራ በታች ከሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ ዕድገት አስመዝጋቢ ሀገር እንደምትሆን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትንበያ እንዳመላከተ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በዛሬው ዕለት መረጃ አጋርቷል።

ከኢቢሲ መረጃ ጋር አብሮ የተያያዘው ምስል እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ የ7.2 ፐርሰንት እድገት በማስመዝገብ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ቀዳሚዋ ሀገር ናት።

ይሁንና ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት መረጃው የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጧል።

አይ ኤም ኤፍ ትናንት በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዲሁም በድረ-ገፁ ላይ ያጋራው መረጃ እንደሚያሳየው ደቡብ ሱዳን የ24.3 ፐርሰንት እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚዋ ናት፣ ኢትዮጵያ እና ጊኒ ደግሞ እያንዳንዳቸው 7.2 ፐርሰንት እድገት በማስመዝገብ የሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/1MWaNg5Gqc/)

በተጨማሪ በአለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት ትንታኔ መሰረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሞ በቀጣዩ 2026 ከሰሀራ በረሃ በታች ካሉ አፍሪካ ሃገሮች በ7.1 ፐርሰንት እድገት አራተኛውን ትልቁ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠብቃል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮ ሁለተኛ ቦታን እንደያዘ ይፋ ቢደረግም አምና አስመዝግቦት ከነበረው 8.1 ፐርሰንት እድገት ወደ 7.2 ፐርሰንት አሽቆልቁሏል፣ ይህም የ0.9 ፐርሰንት መንሸራተትን ያሳያል።

አይ ኤም ኤፍ ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራት አማካኝ እድገት 4.1 ፐርሰንት መሆኑን ጠቅሶ የቀጠናው ሀገራት ኢኮኖሚ መሻሻል እያሳየ መሆኑ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቼክ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa