Islamic World
12/05/2022
«ከእናንተ መልካም ሰው ብሎ ማለት የተራቡ ሰወችን የመገበ ሰው ነው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
10/05/2022
(ሶለሏሁ አለይሒ ወሰለም) ከተናገሩት ተአምራዊ ሀዲስ አንድ...:-
ከ1400 አመታት በኋላ ሳይንስ ከደረሰባቸው የረሱል / ሰ.ዐ.ወ/ ተአምራት መካከል፤ የሚከተለው ሀዲስ አንዱ ነው፡፡
ረሱል /ﷺ/ እንዲህ ብለዋል፡ “የሰው ልጅን
ባጠቃላይ
አፈር ይበላዋል፤ (ዐጅቡ ዘነብ) (coccyx)
ሲቀር፤ የተፈጠረውም ከእሱ ነው (አካሉ የሚገነባውና)
የሚገጣጠመውም ከእሱ ነው” ብለዋል፡፡
ሀዲሱን ያወሩት አቡሁረይራ ናቸው፤ የዘገቡት ደግሞ
ሙስሊም ናቸው፡፡ ምንጭ ሰሂህ ሙስሊም፤ ገፅ 2955፤
ሀዲሱም ሰሂህ ነው፡፡
በአጭሩ የሀዲሱ መልክዕክት፤ የሰው ልጆች አካል፤ አፈር
ይበላዋል ይበሰብሳልም፤ (ዐጅቡ ዘነብ) የጭራ ግንድ
የተባለችው፤ ከጀርባ አጥንታችን ወደታች ስንወርድ ከስር
ጫፍ ላይ፤ ጭራ መብቀል የሚጀምርበት ስፍራ ላይ፤
ሶስት
ማዕዘን መሰል ትንሽዬ አጥንት አለች፤ እሷ ግን
አትበሰብስም፡፡ ሰው ሲፈጠር መጀመሪያ ከእሷ ነው፤
ከሞተም በኋላ በእሷ ላይ ነው እንደ አዲስ እየተገነባ
የሚመጣው፡፡ ለማለት ነው፡፡
ዘመናዊው ሳይንስም የሰው ልጆች ከሞቱ በኋላ ሁሉም
ነገር እንደሚበሰብስና፤ የጭራ ግንድ (ዐጅቡ ዘነብ)
የምትባለዋ አጥንት ግን እንደማትበሰብስ ደርሶበታል፡፡
የጭራ ግንድ (ዐጅቡ ዘነብ) ምንድን ነው??
ይህ የሰው ልጅ ሲፈጠር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ፤
የሚፈጠር የመጀመሪያው አካል ነው፡፡ የመጀመሪያው
ገመድ
በመባል ይታወቃል፡፡ የፅንሱ አካላት በሙሉ ከተፈጠሩ
በኋላ፤ ይህ አካል ከጀርባ አጥንቱ ከስር ጫፍ ላይ ሄዶ
ይረጋል፡፡ በሰዓቱ መጠኑም ምስር ያክላል፡፡ ይህ አካል
የሰው ልጅ ከሞተ በኋላም ህያው ሆኖ ይቀራል፤
በመጨረሻም የሰው ልጅ የቂያማ ቀን የሚቀሰቀስበት ፍሬ
ሆኖ ይቆያል፡፡
ሳይንቲስቶች በተለያዩ መንገዶች ይህን አካል ለመግደል
ብዙ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ህያው ሆኖ ነው
የቆየው፡፡ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ ያለ ሴልን
በማስወገድ በሱ ቦታ የጭራ ግንድ (የዐጅቡ ዘነብ)
ሴሎችን ተክተው አይተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የአላህ /
ሱ.ወ/ ታዕምር የሚገርመው፤ እነዚህ ሴሎች ቦታውን
ለቀው ከእምሮ ወደ ቦታቸው፤ ወደ የጀርባ አጥንት ጫፍ
መንቀሳቀስ መጀመራቸው ነበር፡፡
አላህ /ﷻ/ ረሱልን /ﷺ/ አስመልክቶ በሱረት
አልነጅም አንቀፅ 3 ላይ
“ከልብ ወለድም አይናገርም”
ይለናል፡፡
ሰለዋቱላሂ ወሰላሙሁ ዓለይህ!
By ustaz khalid kibrom
[ ሱረቱ አል-ሩም - 31 ]
ወደእርሱ ተመላሾች ሆናቸሁ (የአላህን ሃይማኖት ያዙ)፡፡ ፍሩትም፡፡ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁኑ፡፡
☞አጭር ..ጣፋጭ..ታሪክ ከ ነብዩ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ህይወት
ከእለታት አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
በመንገድ ላይ ሳሉ አንዲት በእድሜ
የገፉ አሮጊት ሴት እቃ ተሸክመው ይመለከታሉ።
ወደሴትየዋ ጠጋ በማለት እማማ
እቃውን ላግዞት? ሲሉ ጠየቋቸው።
>ሴትየዋ የአላህ መልእክተኛ ስለመሆናችው የሚያወቁት
ነገር አልነበረም፤ እቃውን
ከራሳቸው ላይ አውርደው ሰጧቸው፤ የአላህ
መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) እቃውን ተሸክመው
እስከቤታቸው በር ድረስ አደረሱላቸው።
>ሴትየዋም ትንሽ ጠብቀኝ ብላቸው ወደቤታቸው ገቡ፤
የአላህ መልእከተኛም (ሰ.ዐ.ወ)
ሴትየዋ እስኪወጡ ጠበቁ። ሴትየዋም ከቤት በመውጣት
እንዲህ አሉ፡- ?
በማለት የአላህ መልእክተኛን ጠየቋቸው።
>የአላህ መልዕክተኛም እንዴት አልቀበልም ሲሉ መለሱ።
ሴትየዋም ልጄ እኔ አደራ
የምልህ የሙሀመድን ሀይማኖት እንዳትከተል ነው አሉ።
የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ)
እኔ ሙሀመድ ከሆንኩኝስ ምን ይላሉ? ሲሉ ጠየቋቸው።
>ሴትየዋም አንተ ሙሀመድ ከሆንክማ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም ሙሀመድም የአላህ
መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለው። እንዲህ ነበሩ
የአላህ መልእክተኛ በፀባያቸው
አለምን የገዙት።
!! 🕌🕌
=======
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዓንሁ) .... :-
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ አለ፡-
"ድኃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን? እኛም፡- ከኛ ውስጥ ድኃ ማለት መጠቃቀሚያ ገንዘብ የሌለው ነው አልን፣ እሳቸውም ከኔ ኡመት ድኃ ማለት ነገ የቂያም እለት ሶላቶቹን፣ ጾሙን፣ ሶደቃውን ይዞ የሚመጣና ነገር ግን ያን በመሳደቡ፤ ይሄኛውን በማዋረዱ፣ እሱን ደግሞ ብሩን በመብላቱ፣ የዚህያውንም ደም በማፍሰሱ፣ ይሄንን በመምታቱ ሰበብ ከሐሰናቱ ተወስዶ ለተበዳዮች ይሰጥና የሱ ሐሰናት ሲያልቅበት ከተበዳዮች ኃጢአትን በምትኩ ተሸክሞ በጀሐነም የሚወረወር ነው"።
ሙስሊም ዘግበውታል
«አደራ መልካም ስነምግባር ይኑርህ፣ ዝምታንም አብዛ፣ ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ ይሁንብኝ ፍጥረታቶች ከተዋቡባቸው ነገሮች ሁሉ በእነዚህ በመሰሉ ነገሮች አልተዋቡም»።ረሱል ﷺ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Website
Address
Addis Ababa