IPN World

IPN World

Share

04/22/2026

ብናይ ቀደም ኣፍቃሪኣ ዝተቀተለ መርዓዊ😭😭😭😭

04/22/2026

አስደማሚ ክስተት በአዲስ አበባ፡ በሐሰት ታፍነናል በማለት ገንዘብ የጠየቁ ታዳጊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ::

ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የካ አባዶ አካባቢ በራሳቸው ፍቃድ ከቤት በመጥፋት ቤተሰቦቻቸውን በውሸት ጠለፋ በማሸበር 300 ሺህ ብር ለመቀበል የሞከሩ ታዳጊዎችና ተባባሪዎቻቸው በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ለትምህርት ቤት በሚል ሰበብ ከቤታቸው የወጡት የ15 እና የ16 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ታዳጊዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመሄድ ይልቅ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ እንደነበር ምርመራው አረጋግጧል።

ቤተሰቦቻቸው በልጆቹ መጥፋት ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በነበሩበት ወቅት፣ ታዳጊዎቹ በስልክ ደውለው ታግተናል በሚል ሰበብ ገንዘቡ ካልተላከላቸው ጉዳት እንደሚደርስባቸው በማስፈራራት ለመቀበል ጥረት አድርገዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሪፖርቱ እንደደረሰው ባደረገው ፈጣን ክትትል ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ታዳጊዎቹን ከሁለት ወንዶች ጋር በቁጥጥር ስር አውሏል።

ታዳጊዎቹ በሰጡት ቃል ወደ ውጭ አገር ለመሄድ በማለም ድርጊቱን አስቀድመው እንዳቀነባበሩት አምነዋል።

በአሁኑ ሰዓት ፖሊስ አራቱን ተጠርጣሪዎች እና ለታዳጊዎቹ መኝታ ቤት ያከራየውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን እያካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በበኩሉ፣ ሆቴሎች እና የመኝታ ቤት አከራዮች ለታዳጊዎች አገልግሎት መስጠት እንደሌለባቸው አሳስቦ፤ ወላጆችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸው የት እንደሚውሉ እና ከማን ጋር እንደሚሆኑ በቅርበት እንዲከታተሉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

Via የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Chicago?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Chicago, IL