Menta cinema

Menta cinema

Share

26/04/2016

※※ ስራኝ እንደገና ※※
አይን አለኝ አላይም ጆሮ አለኝ አልሰማ፣
ህሌናዬ ቆስሎ መንፈሴ እየደማ፣
የማላመሰግን ባለኝ የማረካ፣
የብብቴን ጥዬ የቆጡን የምመኝ።
በልቸ ማልጠግብ ጠጥቸ ማረካ፣
የሰውን የምመኝ የእራሴን ሳልነካ፣
ውሉ እንደጠፋበት ልቃቂት በሆነች፣
ላይ ላይዋን አስውባ ውስጧን በመረዘች፣
በእሾሃማ ወርቋ ዙሪያየን ታጥሬ፣
በዚህች ቡትቶ አለም አለው እስከዛሬ።
ህሌናየን ሽጬ ስጋየን አርክሼ፣
በሀሰተኛ ምላስ ባሰት ቃል ተክሼ፣
ያኔ አቤት ማማሬ በንግስት ወንበሬ፣
ነፍሴ ጮቤ ስትረግጥ በወይን ሰክሬ።
ዛሬ ግን አባቴ
ቃልህን ዘንግቸ ለስጋዬ አድልቸ፣
የኖርኩበት ሂይዎት አንተን እረስቸ፣
ዛሬ ተፀፅቸ ህሌናዬ ደምቶ፣
ለበድን ስጋዬ ሳለ በቁም ሞቶ፣
መጣው ልጠይቅህ አንድ የይቅርታ ቃል፣
መቸም የእኔ ጌታ ምህረትህ መች ያልቃል።
አንተን ብቻ ላክብር ይንበርከክ ጉልበቴ ፣
ስምህን ላመስግን ቃል ያውጣ አንደበቴ፣
ትላንትን ረስቸ ቤትህ እንዲሆን ቤቴ፣
እንግዲህ አባቴ
ስራኝ እንደገና ዛሬ ይሁን ልደቴ።

Website