World Class Excellence Center
25/05/2026
15/05/2026
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት አስተያየት ለማሰባሰብ እና ውይይት ለማድረግ የተደረገ ጥሪ
የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ከወቅቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ይቻል ዘንድ፤ ነባሩን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሠረት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቷል።
የሕጉ ረቂቅ ጸድቆ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት፣ በሕጉ ቀጥተኛ ተገዢ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችንና ባለሙያዎችን ማሳተፍ፣ ግብዓት
መሰብሰብና ግልጽ ውይይት ማድረግ አፈላጊ በመሆኑ፣ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ የሚመለከታችሁ ግብር ከፋዮች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ የሕግና የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ፍላጎት ያላችሁ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የገንዘብ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ፤በአካል በመገኘት አስተያየታችሁን እንድትሰጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በተጨማሪም፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የጽሑፍ አስተያየት መስጠት ለምትፈልጉ አካላት፣ የአዋጁን ዝርዝር የድንጋጌዎች ረቂቅ (በአማርኛ ቅጂ) በገንዘብ ሚኒስቴር ድኅረ-ገጽ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ያዘጋጃችሁትን ዝርዝር አስተያየት እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል አድራሻ [email protected] እንድትልኩልን በአክብሮት እንጋብዛለን።
Website link :-https://www.mofed.gov.et/media/filer_public/ea/58/ea58858b-a3c1-4640-88c6-dadac6fe088a/yataakese_asetadaadare_awaaje_maashaashaayaa_amaarenyaa_05152026_second_draft_clean.pdf
10/05/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 17:00 |