Yetseda HIWOT RADIO Program
18/10/2025
ሕይወት ሁነት አዘጋጅና የማስታወቂያ ባለሞያ በስራ ላይ ነን!
አብራችሁን መስራት የምትፈልጉ ደውሉ!
☎️ 0910-95-94-87/0912-06-69-03
28/08/2024
እኚህ ሀዋሳዎች ምንኛ በረቱ
አንዱ ለአዳማ
አንደኛውም ለአዲስ
ለአመት መሻገሪያ መባ አበረከቱ
ዳግማዊ አሰፋ በምስራቅ ተጉዞ አዳማ ይገኛል፦
ይቅር ሳንባባል አመቱ እንዳያልፈን፣
ቂምና ጥላቻን እዚሁ አስቀርተን ፣
በአሮጌው ካኖረነው ስለሚፈነዳ፣
አዲስ ወይናችንን በአዲስ አቁማዳ፣
ከልብሳችን ይልቅ ልቦናችን ይጽዳ።
እያለ ይጣራል
በለው ገበየሁም በዋና ከተማ አዲስ አበባ ላይ፦
ከየአኗኗራችን በማንኪያ ቆንጥሮ
ፊደልን በመልኩ በስርአት ሰድሮ
የተሸፈነውን ማንነታችንን፣
ያልተገለጠውን የየውስጣችንን፣
መሆን ያለበትን የወደፊታችንን፣
እንኳን መሃይም ሆንኩ በሚል የዳቦ ስም
የየልባችንን ይነግረናል በግጥም
እንግዲህ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም ብለን ሁለቱንም አይኖቻችንን ልከንላችኃል በዚያ ያላችሁ እንድትጠቀሙ ይሁን🥰🥰🥰