Hanan Mohammed

Hanan Mohammed

Share

08/06/2026

ዛሬ ማምሻውን ምሽት 12:00 በጋምቤላ ከተማ በአንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል አማካኝነት ተከስቶ የነበረው ያልተጠበቀ የተኩስ ልዉዉጥ የነበረ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ማምሻዉን አሳዉቀዉኛል።

አባሉ በአሁኑ ሰዐት በከበባ ዉስጥ ያለ እና ተጨማሪ ዉድመት እንዳያስከትል በቁጥጥር ስር መኖሩን የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዉልኛል።

ክስተቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የክልሉና የፌዴራል ፀጥታ አካላት በቅንጅት ባደረጉት ፈጣን እንቅስቃሴ ሁኔታው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር ማድረግ ተችሏል።

​ የክልሉ መንግሥት ከጉዳዩ ጋር ተያይዘው ያሉ ዝርዝር ምክንያቶች በሕግና በሥርዓት ተጣርተው ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፀጥታ አካላትም አስፈላጊውን የጥበቃና የክትትል ሥራ በቀጣይነት እንደሚያከናውኑ አስታውቋል።

ሰላም ለጋምቤላ!!

ቻይና አብዲ

Photos from Hanan Mohammed's post 30/05/2026

አራዳ ፓርክ

25/04/2026

ኬኔዲ መንገሻና ብርቱካን ዱባለ


•በይ ላኪልኝ ጃኖ በይ ላኪልኝ ኩታ
አሰሪልኝ ጃኖ ፈተይልኝ ኩታ
ሲበርደኝ እንድለብሰው ማታ

•ልላክልህ ጃኖ ልላክልህ ኩታ
ላሰራልህ ጃኖ ልፍተልልህ ኩታ
ትዝ እንድልህ ትዝ እንድልህ የጥንቱ ትዝታ

•ልላክልሽ በቅሎ ልላክልሽ ፈረስ
ልላክልሽ በቅሎ ልሌክልሽ ፈረስ
የኔ አለም የልብሽ እንድደርስ

•ወይ ላክልኝ ፈረስ ወይ ላክልኝ ፈረስ
ወይ ላክልኝ በቅሎ ወይ ላክልኝ ፈረስ
ስትናፍቀኝ ስትናፍቀኝ ሌት ገስግሼ እንድደርስ

•ትቼያታለሁ ብለህ አውርተሃል አሉ
አይሰማ መስሎህ ያወራከው ሁሉ
ብወድህ ምናለ ባፈቅርህ ምናለ
ሰው ወዶ መሳሳት ዛሬ አዲስ አይደለም
… ዛሬ አዲስ አይደለም

•ተይ ጋምዬ… እንድህ አለ ብሎ
ተው ጋምዬ… ማነው የነገረሽ
ተው ጋምዬ… ድሮም ምቀኛ ሰው
ተው ጋምዬ… ምን ያወራል ብለሽ
ተው ጋምዬ…ምን ያወራል ብለሽ
ተው ጋምዬ…እንኳንስ ልተውሽ
ተው ጋምዬ…ጨክኜ ልጥልሽ
ተው ጋምዬ…በምኑም በምኑም
ተው ጋምዬ…ከአፌም አልነጥልሽ

•ያም መጥቶ እንዲህ ነው ሲሉኝ
ያም መጥቶ ትቶሻል ሲለኝ
በነገር ሆዴን ሲያቆሰለኝ
ኧረ እንዴት እውነት አይመስለኝም
•የኔ ሸጋ የኔ ሸጋ እንዴት አይመስለኝም

•እመኚኝ አንቺው በርትተሽ
ጠብቂኝ ይልቅ በርትተሽ
ወሬኛውን ትተሽ

•ኧረ እንዴት ልመንህ እኔ
ኧረ እንዴት ልመንህ እኔ
አጥቼህ ከጎኔ…
…ይቀጥላል

Website