Wollo Addis

Wollo Addis

Share

16/05/2026

''በትግራይ ክልል አዲስ ኃይል ስልጣን እንዲረከብ ፌደራል መንግስት እገዛ ያድርግ'' ጄ/ል ሳሞራ የኑስ

የትግራይ ክልልን ስልጣን የሚረከብ አዲስ ኃይል እንዲመጣ ፌደራል መንግስት ኃላፊነት ወስዶ ግፊት ያድርግ ሲሉ ጄነራል ሳሞራ የኑስ ጥሪ አቀረቡ። ሰሞኑን የተደረገው ''የፈርሰ ምክር ቤትን ተጠቅሞ ውዝፍ አመራር ወደ ስልጣን የመመለስተግባር'' ህዝቡን ለከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት የዳረገ ክስተት ብለውታል።

የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ ወቅታዊውን የትግራይ ፖለቲካዊ ሁኔታ አስመልክተው ዛሬ ከወጋሕታ ጋዜጣ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባካሄዱት ቃለምልልስ እንደገለጹት፣ የህወሓት አመራሮች ሰሞኑን የወሰኑት ህገወጥ ውሳኔ ህዝባዊ ድጋፍ ያለው እንዲመስል ብዙ የፕሮፖጋንዳ ስራ ቢሰራበትም እውነታው ግን ከመቶ በማይበልጡ ሰዎች ምክክር ብቻ ውስጥ ለውስጥ ተወስኖ ተግባራዊ የተደረገ የጥቂቶች ፍላጎት መሆኑን አብራርተዋል።

ድርጊቱን "በጣም መጥፎ" ሲሉ የገለጹት ጄነራል ሳሞራ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘው የትግራይ ተወላጅ በዚህ ድርጊት እጅግ መቆጣቱን ገልጸው የዚህ ዋና አላማ ደግሞ "ስልጣንን ለማስቀጠልና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ታሳቢ ያደረገ ተግባር" ሲሉ ገልጸውታል።

በጄ/ል ሳሞራ እምነት ይህ የ"እንጠየቃለን" ስጋት የፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆን የክልሉ ወታደራዊ አዛዦች ስጋትም ጭምር እንደሆነ በማብራራት ሁለቱም ተቀናጅተው ይህን ያስፈጸሙበት ምክንያት "ተጠያቂ እንሆናለን" ከሚል ስጋት የመነጨ እንደሆነ ያብራራሉ።

ጄነራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው የሰሞንኛው እንቅስቃሴ ዋና አላማ "ስልጣንን ለማስቀጠልና ከተጠያቂነት ለማምለጥ" መሆኑን ቢገልጹም እንደገና መልሰው ደግሞ የዚሁ እንቅስቃሴ ዋና ዓላማ "የፌዴራል መንግስት የሚያካሂደውን ሀገራዊ ምርጫ ለማስተጓጎል ያለመ" ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ይገልጻሉ።

የፌዴራል መንግስት ጉዳዩን በረጋ መንፈስ እና በብስለት ሊፈታው እንደሚገባ የሚመክሩት ጄነራል ሳሞራ፣ የትግራይ ህዝብ ከዚህ በላይ እነዚህን አመራሮች መታገስ እንደሌለበት በአጽንኦት ገልጸው ፌደራል መንግስት ኃላፊነት ወስዶ አዲስ ኃይል መጥቶ ስልጣን እንዲረከብ ግፊት እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ጄነራሉ "ወደፊት መጥቶ ስልጣን ይረከብ" የሚሉት አዲስ ኃይል የትኛው ኃይል እንደሆነ ግን በዚሁ ቃለምልልሳቸው በዝርዝር አልገለጹም።

አውራምባ
#በዝርዝር #ሸር

15/05/2026

''አዲስ አበባ ላይ ጎዳና የሚያስወጣ እና ምግብ የሚያስለምን ነገር የለም''

ክብርት ከንቲባችን አዳነች አበቤ " አዲስ አበባ ላይ ጎዳና የሚያስወጣ ነገር ምግብ የሚያስለምን ነገር ምን እንደሆነ ምክንያቱን አላውቅም።

በአሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ላይ ምግብ የሚያስለምን ምንም ምክንያት የለም። በየምገባ ማእከሎቻችን ትኩስ የተመጣጠነ ጣፋጭ ምግብ ተዘጋጅቶ ይጠብቃችሗል ጎራ ብላችሁ በነፃ መብላት ብቻ ነው ከናንተ የሚጠበቀው "ብላለች።

ምን ትጠብቃላችሁ በዚህ በተወደደ ኖሮ ጎራ እያላችሁ ብሉ እንጅ

Telephone

Website