Sumuda Design And Consultancy Plc
20/04/2026
የሀዋሳ ከተማን ውድ እና ዘመናዊውን ቤት ጨርሰን አስረከብን!!💪💪
በሀዋሳ ከተማ ከዲዛይን እስከ ግንባታ ተረክበን እየሰራን ካሉት ስራዎች መካከል በሀዋሳ ከተማ, ታቦር ክ/ከተማ,አዲሱ መናኸሪያ አካባቢ የጀመርነውን Luxury G+2+T መኖሪያ ቤት በ 5 ወር ገንብተን በዚህ መልክ ጨርሰን አስረክበናል።
ሱሙዳ ይለያል ምንለው በምክንያት ነው!!
Architect and Contractor Bruk Mulugeta
Phone no -- 0911007254/0941651010
Hawassa
27/03/2025
✍️ስለ ሱሙዳ ሃውልት ምን ያህል ያውቃሉ ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✍️ሱሙዳ ሲዳምኛ ቋንቋ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙ ደግሞ ማህተም ማለት ነው፡፡በሌላ ትርጉም ባህል፣ አርማ፣ ማህተም፣ ምልክት የሚል ስያሜ አለው፡፡
✍️ሀውልቱ ሱሙዳ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት፦ ሀውልቱ በባህሪው ከሞዛይክ የተሰራ ስለሆነና የሲዳማን ብሔር ባህል፣ ታሪክና ማንነት የሚገልጽ በመሆኑ ነው።
✍️ሱሙዳ ሀውልት ሀዋሳ ውስጥ ፒያሳ በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ይገኛል።
✍️የሱሙዳ ሀውልት ግንባታው ከአለቀ ጊዜ ጀምረው ለጉብኝት ክፋት ሆነዋል።
✍️የሱሙዳ ሀውልት ቅርፁ የተሰራው በእንሰት የውስጠኛው የቅጠል ክፍል ተምሳሌት ነው፡፡ በሀውልቱ ቅርፅ ዙሪያ የተነሱ አከራካሪ ሀሳቦች፦ ቡና ለሲዳማ ህዝብ የገቢ ምንጭ ስለሆነ፤ የቡና ቅርፅ ይያዝ የሚል ሀሳብ ተነስቶም ነበር፡፡ በሌላ በኩል የጎጆ ቅርፅ ይሁን የሚሉም ነበሩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ያለውን ቅርፅ ተመርጧል፡፡ የእንሰት ቅርፅ የውስጠኛው መሽራው ክፍል ሊመረጥ ችለዋል።
✍️ቅርፁም የእንሰት ወይም ኮባ የውስጠኛው ወይም ሙሽራው ክፍል እንደሚያድግ ሁሉ የሲዳማም ህዝብ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሚጓዝ ማሳያነት ነው፡፡
✍️ሙሽራው በእንሰቱ እንደሚታቀፍ ሁሉ የሲዳማ ማህበሰብም ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ያለውን ትስስርና አቃፊነቱን የሚያሳይ ነው፡፡
✍️ ሱሙዳ ሀውልት የተለየዩ ህብረ ቀለማት ባሉት መብራቶች የሚታጀብ የውሃ ፋውንቴን ያለው ሲሆን በሦስት አቅጣጫ የኢትዮጵያን ባንዲራ የሚያሳይ መብራት ያለው ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው የሲዳማ ህዝብ ኢትዮጵያዊና ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገል፤ ከኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጋር አብሮ በመከባበርና በመፈቃቀር የሚኖር ህዝብ መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡ በሱሙዳው ከላይኛው ጫፍ የሚወርደው ፋውንቴን የሲዳማ ህዝብ በሀገር በቀል ዕውቀቱ የገነባው የቤት አሰራርን የሚያሳይ ትዕይንት ነው፡፡
✍️የሱሙዳ ሃውልት በወቅቱ ለግንባታው 14ሚሊዮን ብር ፈጅተዋል።
✍️የሱሙዳ ሃውልት 28 ሜትር ከፍታ አለው።
✍️ሱሙዳ በአራቱም አቅጣጫ የሲዳማን ብሔር ታሪክ፥ ባህልና ወግ የሚገልፁ ብዙ የስዕል አሻራዎች ይገኙበታል።
➙በሱሙዳው ታችኛው ክፍል በደቡብ አቅጣጫ የ"ሁሉቃ" (የሽግግር) ምስል የሚታይ ሲሆን ይህም ወደ አዲስ ዘመንና ምዕራፍ የመሸጋገር ምሳሌ ነው፡፡
➙ቀጥሎ በደቡባዊ ምስራቅ አቅጣጫ የሽምግልና ወይም ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት የሚታይ ሲሆን ይህም የሲዳማ ብሔር ዘመናዊ የዳኝነትና የፍትህ ስርዓት ባልነበረበት ዘመን የግለሰቦች ችግር ወይም ማህበራዊ ጉዳዮቹን ተወያይቶ መፍትሔ የሚያፈላልግበት የራሱ የሆነ ስርዓት እንዳለው ያመለክታል፡፡
➙በምስራቅ አቅጣጫ ትንሽ ወደ ላይ ከፋ ብሎ የሲዳማ ሴቶች ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመወያየት ልምድና ስርዓት እንዲሁም ከእነርሱ በስተጀርባ ጠንካራ ሴት ማለትም ንግስት "ፉራ" ስለመኖሯ የሚያሳይ በምስሉ ያሳያል፡፡
➙በላይኛው የሱሙዳ ክፍል ማለትም ወደ አንደኛ የሀውልቱ እርከን አካባቢ በደቡብ አቅጣጫ የፍቼ በዓል የሚከበርበትን ቀን ለማብሰርም ሆነ የቀንና የወራት አቅጣጠርን ለመለየት የከዋክብት ቆጠራ ተሰጥኦ ባላቸው አያንቶዎች (አዋቂዎች) ወራዊ ተግባራቸውን የሚያሳይ ምስል አለው።
➙ከዚህ ቀጥሎ በምስራቅ አቅጣጫ በኩል የሚታየው የሉዋ ስነ ስርዓትን ሲካሄድ ነው።
➙በዚህ አቅጣጫ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ያገቡ ሴቶችና ወንዶች የሚጨፍሩበት ባህላዊ (ሓኖ-ፋሮ) የሚታይ ሲሆን በዚህም በሲዳማ ብሔር ዘንድ ባህላዊ ስነ ስርዓትና ሌሎችም ማህበራዊ ጉዳዮች በሚከናወንበት ወቅት ሴቶችም እኩል ተሳታፊ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡
➙በሱሙዳው ፊት ለፊት ገፅታ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ባህላዊ የጦር መሣሪያ የያዙ የብሔር አርበኞች (ኤጀቶች) ከዚያም ቄጤላ፣ ቀጥሎ ደግሞ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ለነፃነታቸው እና ለመብታቸው የታገሉ ጀግኖች ይታያሉ፡፡ መልዕክቱም የሲዳማ ብሔር ለነፃነቱና ለመብቱ ከጥንት ጀምሮ ቀናዒና ታጋይ በመሆኑ በጥንታዊ የጦር መሣሪያ ከዚያም በዘመናዊ መሣሪያ በመታገልና መስዋዕትነትን በመክፈል የዛሬውን ሰላማዊ ህይወት ለዘመኑ ትውልድ እንደአስረከበ ያስረዳል፡፡
➙ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቄጣላ ጭፈራ የሚታይ ሲሆን ይህም የሲዳማ ብሔር ባህላዊ በዓላትን ሲያከብሩ እንዲሁም በአንድ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ድጋፍንና ተቃውሞን ስነ ቃሎችን በመጠቀም የሚገለፅበት ስልት ወይም ባህላዊ ይዘት ያለው ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑን ያሳያል፡፡
➙ከዚህ በኋላ በሱሙዳው አካል የሚታየው "ፋሮ" የሚባለውን የወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች ባህላዊ ጭፈራ በሲዳማ ብሔር ወጣቱ ትውልድ የብሔሩን ባህል የሚያደምቅበትና በማህበራዊ ህይወት ውስጥ የራሱ ድርሻና ሀላፊነት ያለው መሆኑን ያስረዳል፡፡
➙በሱሙዳው ጫፍ አካባቢ መጽሐፍ የያዙ ወጣቶች፤ ከዚያም ቀጥሎ የብርሃን ፍንጣቂን ሁለት እጆቿን ዘርግታ ለመቀበል የተዘጋጀች ወጣት ትታያለች፡፡ የዚህም መልዕክት መጪው የህይወት ራዕይ በዚህ እንዲሆንና ሁለንተናዊ ትራንስፎርሜሽን ለማሚጣት መሠረት እውቀት መሆኑን ያመለክታል፡፡ የመጽሐፍ ትርጉም ሌላኛው የሲዳማ ብሔር ዘመናዊን ትምህርት በአብዛኛው የመማር ራዕይ ያገኘው በተለይም ሚሲዮኖች ወደ ሀገራችን ከገቡ በኋላ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡
2017ዓ.ም ሀዋሳ
✍️ተጻፈ በጋዜጠኛ ዘርፉ ሳሙኤል ‼️
ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ
25/01/2025
ከዲዛይን እስከ ግንባታ ተረክበን እየሰራን ካሉት ስራዎች መካከል ዲዛይኑን በዚ መልክ ጨርሰን ግንባታውን በዛሬው ቀን የጀመርነው በሀዋሳ ከተማ, ታቦር ክ/ከተማ,ሜንቦ አዲሱ ኮሪደር አካባቢ እየገነባን ያለነው G+5+T ሁለገብ ህንፃ.
Architect and Contractor Bruk Mulugeta
ph no -- 0911007254/0941651010
ሱሙዳ ይለያል ምንለው በምክንያት ነው
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hawassa