HUfellow

HUfellow

Share

Photos from HUfellow's post 18/04/2026

👉ደዌያችሁን ወስጃለሁና (Nasa)

ደዌያችንና የእግዚአብሔር የድኅነት እቅድ
ሰው ልጅ ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር ለቅርብ ህብረት የተፈጠረ ሲሆን፣ በኃጢአት መግባት ይህ ህብረት ተቋርጧል። ኃጢአት የሰውን ልብ አበላሽቶ ከፍተኛ ውስጣዊ ችግር አምጥቷል። ጭንቀት፣ ኀፍረት፣ ፍርሃት፣ ስቃይ፣ መከራ እና በመጨረሻ ሞት የኃጢአት ፍሬዎች ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ 📖እንዲህ ይላል፦
“ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ፣ በኃጢአትም ሞት፤ እንዲሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ” ።(ሮሜ 5፥12)
ይህ የሚያሳየው ሰው ሁሉ በዚህ ደዌ ተጎድቶ እንዳለ ነው፤ ማንም ከኃጢአት ነፃ አይደለምና።

ሰው በራሱ ኃጢአትን ሊያሸንፍ አይችልም፤ መልካም ሥራዎች፣ ሃይማኖታዊ ልማዶች ወይም ጥረት ብቻ ሰውን ከዚህ ደዌ ሊያድኑት አይችሉም። ምክንያቱም ችግሩ ውጫዊ አይደለም፤ በልብ ውስጥ ያለ እንጂ ።

ስለዚህ ሰው የሚያስፈልገው ከውጭ የሚመጣ በራሱ ያልሆነ ድኅነት ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ብቻ የሚመጣ ነው።
   
ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ "የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው"።   (ትንቢተ ኢሳያስ 59:-16)
                

እግዚአብሔር ሰውን በፍቅር አየ፤ በኃጢአት የወደቀውን የሰዉ ልጅ ሊያድን ወሰነ። ይህን የድኅነት እቅድ ለመፈጸም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም🌍 መጣ።

እርሱ ኃጢአት የሌለበት ቢሆንም የሰውን ኃጢአት ተሸክሞ ስቃይን ተቀበለ።

ሲተፋበት ሲገረፍ ለእርድ እደሚነዳ በግ በሸላቶቹ ፊት ዝም ሲል ቀይ ልብስ አልብሰውት የእሾክ አክሊል ጉንጉን ደፍተውበት በመቃ(በበትር) ሲመቱት ሲዘባበቱበት ደግሞም ሊሰቅሉት መስቀሉን አሸክሞውት ጎልጎታ ሲወስዱት ከአመጸኞች ጋር ሲቆጠር  ሆምጣጤ በሰፍነግ ተሞልቶ በመቃም(በዘንግ) አድርገው ሲያጠጡት ይህ ሁሉ የሆነው ለእኛ ነው፤ እኛን ከኃጢአት እና ከሞት ሊያድነን ነው። እርሱ የእኛን ስቃይ ተሸክሞ፣ እኛ ያልቻልነውን አደረገ።

“እናንተ ደካሞችና ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ብሎ ተናገረ።

ይህ ጥሪ ዛሬም አለ፤በኃጢአት የተጨነቀ በሕይወት የደከመ ተስፋ የቆረጠ ሰው ሁሉ ወደ እርሱ እንዲመጣ ይጠራል። ወደ እርሱ መምጣት ማለት በእምነት መቀበል፣ ኃጢአትን መተው እና እርሱን እንደ ጌታ መከተል ማለት ነው።

ዛሬም የእግዚአብሔር ትዕግሥት አላለቀም፤ የምህረቱ ደጅ አልተዘጋም። ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም ይጠራል፤ “ና” ይላል።

ለኃጢአት መፍትሔ አለ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ በመስቀል ✝️ላይ ያደረገው ሥራ ለሰው ሁሉ በቂ ነው። ማንም በእምነት ወደ እርሱ ቢመጣ ይድናል፣ እረፍት ያገኛል፣ አዲስ ሕይወት ይቀበላል።

"ዛሬም አላለቀም ትዕግሥቱ
ባንተ ላይ ምህረቱ
ኢየሱስ ሲጠራህ ተው
ስማው ወደ ሞት አታዝግም
የፀጋ የምህረት ደጁ አልተዘጋም"





TELGRAM
INSTAGRAM
TIKTOK

Photos from HUfellow's post 13/03/2026

❤️
ለመንግስቱ መትጋት

ሁለተኛ ጢሞቴዎስ የተፃፈበት ምክንያት
1) ሩጫውን ስለጨረሰ
2) ተረካቢ ስለሚያስፈልግ
3) ወንጌልን የሚያጣምሙ ስላሉ
4) አብረው የነበሩ አንዳንዶች ጥለውት ስለ ሄዱ
ስለነዚህ ጢሞትዎስን ለማበረታታት ነበር
አደራው
አምስት አደራዎች ነበሩ
1) ቃሉን ስበክ /እንጂ አታስታክ
2) በጊዜም ያለ ጊዜውም ዝግጁ ሁን ፅና
3) ፈጽመህ እየታገስክ አስተምረህ አቅና
4) ገስጽ
5) አበረታታ
እነዚህ ትእዛዞች የሚሰጡበት ምክንያት
1) ትክክለኛ ትምርትን የማይታገሱበት ዘመን ስለመጣ
2) የሚያስፈልጋቸውን ሳይሆን የሚፈልጉትን ብቻ ስለሚሰሙ
3) ጆሮን የሚያሳክክ ስለሚሆንባቸው
4) ወደ ተረት ፈቀቅ ስለሚሉ
  ጳውሎስን በሁለተኛው ጢሞቲዎስ ምዕራፍ 4 ከቁጥር 5 ላይ
-አንተ ግን ነገረን ሁሉ በልክ አድርግ
- መከራን ተቀበል
- የወንጌል ሰባኪነትን ተግባር አድርግ (ቲቶ 1÷9) የወንጌል ሰባኪ -በቃሉ የሚኖር ነው                   -የሚወቀስ ነው
           -ለሌሎች ትክክለኛ ትምህርትን                               የሚያስተምር ነው
- አገልግሎትህን ፈጽሞ

Photos from HUfellow's post 20/02/2026

6

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Hawassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Hawassa