Cheta Woreda Communication

Cheta Woreda Communication

Share

Photos from Cheta Woreda Communication's post 23/05/2026

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ለሚደረገው የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የሥራ ስምሪት ተሰጠ::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስተዳደርና ፖለቲካ መቀመጫ እንዲሁም የካፋ ዞን ርዕሰ ከተማ በሆነቹ ቦንጋ በቀን 18 ለሚደረገው ክልል አቀፍ የብልጽግና ፓርቲ ማጠቃለያ ድጋፍ ሰልፍ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የመጀመሪያ ዙር የሥራ ስምሪት ተሰጠ::

የድጋፍ ሰለፉ በብልጽግና ፓርቲ የተመዘገቡ ስኬቶችና ድሎችን አስመልክቶ የሚደረግ ሀገራዊ ይዘት ያለውና የዞኑ ህዝብ ለብልጽግና ፓርቲ ያለውን ፍቅር የሚገልጽበት ልዩ ኩነት በመሆኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሙያዊ ስነምግባር አክብሮ ጥራት ያለውን መረጃ ለህዝቡ ማድረስ እንዳለባቸው የካፋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢኖቨሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ ተናግሯል::

አቶ ተፈሪ እንዳሉት ሁሉም ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የሚሰሩት ትክክለኛ ተዓማኒና ጥራት ያለውን መረጃ ለህዝብ ለማድረስ በመሆኑ በሰልፉ ዕለት ተግባራትን በቁርጠኝነት መፈፀም የሚያስችል ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አቶ ተፈሪ አመላክተዋል::

የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አዳሙ እሸቱ በበኩላቸው ከፊታችን ግንቦት 18 በቦንጋ ከተማ የሚደረገው የብልጽግና ፓርቲ ማጠቃለያ የድጋፍ ሰልፍ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ሁሉም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በመረዳት ይህንን የሚመጥን የሚዲያ ሽፋን መስጠት እንዳለባቸው ገለፀዋል::

በተለይ በድጋፍ ሰልፉ ወቅት ህዝቡ ለፓርቲ ያለውን ስሜትና ፍቅር በአደባባይ የሚገልጽበት ታላቅ ቀን በመሆኑ ይህንን ድባብና ኩነቶችን በተገቢው በመከታተል ጥራት ያለውን እና በትክክለኛ መረጃ ላይ የተደገፈ በ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሽፋን መስጠት ከሁሉም እንደሚጠበቅ አቶ አዳሙ እሸቱ አሳስቧል::

በመድረኩ የተገኙት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የድጋፍ ሰልፉ ለሀገረ መንግስት ግንባታው ሂደት ያለው ሚና ጉልህ በመሆኑ የተሰጣቸውን የሥራ ሃላፍነት ሙያዊ ስነምግባር አክብረው ጥራት ያለውን እና ተገቢ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አመላክተዋል::

በቀጣይ ተጨማሪ የሥራ ሥምሪት የሚሰጣቸው የሚዲያ ባለሙያዎች እንዳሉ ማወቅ የተቻለ ሲሆን በድጋፍ ሰልፉ ላይ መላው ህዝብ ተሳታፊ እንዲሁን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮሚቴ አሳስቧል ሲል የዘገበው የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

ወታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356

በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single

በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR

Photos from Cheta Woreda Communication's post 22/05/2026

የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የወጣቶች ሚና የጎላ ነው ስሉ የወረዳ ምክትል አስተዳደርና ሥራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ከተማ ከፍያለው ተናገሩ።

በካፋ ዞን ጨታ ወረዳ በባሺ ቀይ ማዘጋጃ የ7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ በወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት የብልፅግና ፓርቲ የይምረጡኝና የቡና ጠጡ መርሃግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳ ምክትል አስተዳደርና ሥራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ከተማ ከፍያለው በሀገር ደረጃ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው የወጣቱ ኃይል ነው በማለት የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የወጣቶች ሚና የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።

የለውጡ መንግስት ብልፅግና ወደስልጣን ከመጣበት ማግስት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችን አስመዝግቧል በማለት በቅርበት የመገልገል መሻትን በመቀበል በክልል የመደራጀት ጥያቄን መልስ የተሰጠበት ነው ብልዋል።

የወረዳ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ መስፍን በበኩላቸው ፓርቲያችን ብልፅግና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሁኖ በርካታ ድሎች ያስመዘገበ ነው በማለት በወረዳ ደረጃም የዘመናት ጥያቄ የነበሩ የባንክ አገልግሎት፣ የንፁህ መጠጥ ውኃና የመብራት አገልግሎትን ጨምሮ የህዝብ ጥያቄዎችን እየፈታ መጥቷል በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ወጣቱ ኃይል የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዘመን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይጠበቅበታል ያሉት ኃላፊው በዲጂታል መረብ የዘመነች ኢትዮጵያን ለመገንባት የብልፅግና ፓርቲ አስቻይ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን የወጣቱ ሚና የጎላ ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እረገድ የበኩላን መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ወጣቶች የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ ለይቶ የማወቅ፣ የማስተዋወቅና የመምረጥ ኃላፊነታቸው በአግባቡ በመወጣት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እንዲያሻግሩ ጠይቀዋል።

ምክትል አስተዳደር አቶ ከተማ አክለው የዛሬ ፍሬዎች የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ በወረዳ ደረጃ ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ በሰፊው መሰራቱን አስታውሰዋል።

በኢኮኖሚ ዘርፍ እንደወረዳ የተሻለ እምርታ ተመዝግቧል ያሉት አቶ ከተማ በ2013 ዓ/ም 17ሚልዮን ብር ብቻ መሰብሰቡን በማስታወስ በ2018 ዓ/ም እስካሁን ከ92 ሚልዮን ብር በላይ መሰብሰቡን በመናገር የተመዘገበው ለውጥ የብልፅግና ፓርቲ ትሩፋት ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ወጣቱ ኃይል በስንዴ ነዶ የተወከለውን የብልፅግና ፓርቲን እንዲመረጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወጣቶችም በተለያዩ የድጋፍ ኩኔቶች የብልፅግና ፓርቲ ወገንተኝነታቸውን እና ከፓርቲ ጎን መሆናቸውን አሳይተዋል።

በኤልያስ ጋሎ

የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፦ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356

በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single

በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/

Want your business to be the top-listed Media Company in Bonga?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Kafa Cheta
Bonga