Derry Desalegn
17/02/2023
Sometimes you think people are stopping you from getting to the top and forget it's your mouth.
25/09/2021
የአንድ ሰው እውነተኛ ማንነት ያለው በሚነግርህ ነገር ላይ ሳይሆን በማይነግርህ ላይ ነው።ስለዚህ ፀባዩን በደንብ ለማወቅ ከፈለክ የሚነግርህን ነገር ሳይሆን የማይነግርህን አድምጥ።
22/06/2021
👉👉የራስህን ኑሮ ኑር👈👈
አንዳንዴ ቁጭ ብዬ ሳስብ የአንዳንዱ ህይወት ይገርመኛል።የራሱን ህይወት መኖር ይተውና የሌላውን ህይወት ሲኖር ይታያል።የራሱን ህይወት በቅጡ ሳይኖር የሌላውን ህይወት ይኖራል።ይህ ማለት ደግሞ ሁለት ሰዎች አንድ ህይወት ይኖራሉ።በአንድ አውሮፕላን ውስጥ አንድ ሽማግሌና አንድ ህፃን ጎን ለጎን ተቀምጠው ይሄዳሉ።ታዲያ በዚህ ጊዜ ልጁ ከኪሱ ቸኮሌት አውጥቶ ሲበላ ሽማግሌው ያየውና እንዲህ ይመክረዋል
''ቸኮሌት ለምን ትባላለህ ጥርስህን ያበላሻል ስለዚህ አትብላ'' ይለዋል።ልጁም መልሶ ''አያቴ 120 ዓመት ነው የኖረው''።ሽማግሌውም ቀበል አድርጎ ''ቸኮሌት ባለመብላቱ ነው አይደል?'' ሲል ልጁም ''አይደለም በማያገባው ስለማይገባ ነው።''ብሎ መልሶለታል። ዛሬም አንዳንድ ሰው በማያገባው እየገባ የሌላውን ህይወት ሲኖር ቆይቶ የራሱ ህይወት ኦና ሆና ይቺን ምድር ይሰናበታታል።እኔ እስከማውቀው ድረስ የራሱንም የሌላውንም ህይወት የምኖረው ብቸኛው 👉ያፈቀረ ሰው👈 ብቻ ነው።እሱም ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነው።................ስለዚህ ወደራስህ ተመለስ።
30/11/2020
👉አይ ሰው ሲገርም👈
1:ስለነገ በመጨነቅ ዛሬን ለመኖር አለመቻሉና ከዛሬም ከነገም ሳይሆን መንከራተቱ ያሳዝነኛልም ያስገርመኛልም
2:ልጆች ሳሉ መሰልቸታቸውና ትልቅ ለመሆን መሮጣቸው......ካደጉ በኃላም ልጅ ሆኖ ለመታየት መሮጣቸው
3:ገንዘብ ለማካበት ጤንነታቸውን ማጣታቸውን.....ጤናቸውን ለመመለስ እንደገና ያንኑ ገንዘብ ማፍሰሳቸው
4:ልክ እንደማይሞት ሰው መኖራቸውና ልክ እንዳልኖረ ሰው ተፅዕኖ ቢስ ሆነው መሞታቸው
ያስገርሙኛል።
Click here to claim your Sponsored Listing.