Laangano Media

Laangano Media

Share

06/04/2025

አትድከም📍
በርታ በል ወዳጄ ፣ ለራስህ ከፈጣሪህ ጋር እራስህን አቁም ። ስትሞት ምን ይፈጠራል መሰለህ ? ዕድርተኛው ሰብሰብ ብሎ አለ የተባለ ትልቅ ድስት ይፈልግና ወጥ በየአይነቱ ሰርቶ ደግሶ ይቀብርሃል ። ለቀናቶች በስምህ ቆንጆ እራት ይበላል። የሀብታም ልጅ ከሆንክ ደግሞ በእነ ጆርዳና ወይም በእነ ሼፍ ዮሐንስ ቆንጆ ቡፌ ይዘጋጃል። ቀና ብለህ ብታይ '' ቆይ በጣም ነው እንዴ የሞትኩት '' ብለህ ትገረማለህ ። አብሮህ የሚቀበር ግን የለም ። ሁሉም የዕለት ተግባሩን ይጀምራል ። ህይወት ይቀጥላል ። ቀን ስራው ላይ ውሎ ማታ ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ቤተሰቦችህ ቤት ያመራል። ሶስት ደቂቃ ተቀምጦ ምስሯን ሰላም ካለ በኋላ ወደ ቤቱ ይመለሳል ። አሁን ግን አንተ ግን የለህም ።አንተ ትረሳለህ ። ለአንተ ግን ያለኸው አንተው ነህና ዕሩቅ ለመድረስ ብርቱ ወዳጅ ያዝ ። ቶሎ ለመድረስ ብቻህን ገስግስ ። በሁሉም ውስጥ አምላክህን አትርሳ። እሱን አስቀድም ።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Awassa
HAWASA