FM Gadaa Gujii
30/09/2022
የኢቢሲ የመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች
**********************
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።
• ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመላው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የዕርቅ፣ የሰላም የወንድማማችነት እና የአንድነት ባህል ለሆነው የኢሬቻ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ ሲል መልእክት አስተላልፏል።
• የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅነት የሚንፀባረቅበት የሰላም እና የወንድማማችነት አርማ ነው ሲሉ ገለጹ።
• የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
• በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።
• የመከላከያ ሠራዊት በሲቪሎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄና የዒላማ ጥራት የወታደራዊ አቅሞችን ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
• ከባድ የግድያ፣ የውንብድና እና የዘረፋ ወንጀልን ሲፈጽሙ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር መዋላቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገለፀ።
• የትምህርት ሚኒስቴር እና ሰላም ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ተስማሙ።
• በአማራ ክልል አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ከመመከት ጎን ለጎን ለወጣቶች ሥራ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የተቀናጀ ድጋፍ ያስፈልጋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ።
• በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ በ1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባ እና በወር ከ125 ሺህ ኩንታል በላይ የእንሰሳት መኖ ማምረት የሚችል ፋብሪካ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለጸ።
• ዐቃቤ ሕግ የሐሰት ወሬን ነዝተዋል፣ በውጊያ ውስጥ የወገን ጦር አሰላልፍ እና ቦታን ለጠላት እና ለሕዝብ አሳውቀዋል በሚል እና በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ጎበዜ ሲሳይ፣ አሳየ ደርቤ እና መዓዛ መሐመድ የተባሉ ግለሰቦች ላይ በዛሬው ዕለት ክስ መመሥረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።
• የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Awassa
WET555