Maba Tech info
02/05/2024
የሚመስል ነገር
ፍቅር በሚመስል ዘረኝነት።
አንድነት በሚመስል አድመኝነት።
ሰላም በሚመስል መረጋጋት።
ደስታ በሚመስል ሣቅ።
የዋህነት በሚመስል ጅልነት።
ብልሃት በሚመስል ብልጠት።
ሴት መውደድ በሚመስል አመንዝራነት።
ቁጠባ በሚመስል ስስት።
ቸርነት በሚመስል መበተን።
መስጠት በሚመስል ብድር።
ምስጋና በሚመስል ስድብ።
ዲፕሎማሲ በሚመስል ውሸት።
ማዘን በሚመስል ከንፈር መምጠጥ።
እምነት በሚመስል ወገኛነት።
አክብሮት በሚመስል ማጎንበስ።
ምስጋና በሚመስል ምፀት።
ዓይናፋር በሚመስል መንጣሪነት።
ርኅራኄ በሚመስል ልፍስፍስነት።
ቆራጥነት በሚመስል ጭካኔ።
ዓላማ በሚመስል ሰው መፍጀት።
ትዕግስት በሚመስል ስንፍና።
ትጋት በሚመስል ችኰላ።
መዋደድ በሚመስል መላመድ።
ዝምታ በሚመስል ዱዳነት።
ግልጽነት በሚመሰል እብደት።
ምስጢር በሚመስል ባዶ ነገር።
እልልታ በሚመስል ኡኡታ።
ድጋፍ በሚመስል ፍርሃት።
ዘመናዊነት በሚመስል ወረት።
ሀገር ወዳድ በሚመስል ጥላቻ።
ራእይ በሚመስል ቅዠት........ነው።
ከዚህ ውስጥ እኛን ይገልጻል የምንለውን አንዱን እንውሰድና የሐሰት ከመራመድ የእውነት እንቁም።
ያኔ ሸክም ቀሎን የእውነት እንራመዳለን።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Telephone
Website
Address
Awassa
TRAININGCENTER