Digital Hakim

Digital  Hakim

Share

21/05/2026

እኛ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል የምንገኝ ረዚደንት ሐኪሞች የመኖሪያ ዶርሚተሪ አትሰጡም ተባልን ።ምክንያቱ ደግሞ ትዳር መስርታችኋል:ልጅ ወልዳችኋል ህንጻው ይበላሻል ነው ።

እጥፍ ድርብ ኃላፊነት ያለብን ሐኪሞች መኖር አልቻልንም ።

ድምጽ ሁኑን።

18/05/2026

ህልመኛዋ ነርስ ሂንሴኔ ተፈሪ የገዛ ሕይወቷን አጠፋች!😭

ወጣቷ ሂንሴኔ ተፈሪ ፤ "ነርስ ሆኜ የሰዎችን ህይወት እታደጋለሁ" የሚል ትልቅ ህልም ነበራት። ለ4 ዓመታት ቀን ከሌሊት ደክማለች። በነቀምቴ ከተማ በሚገኘው የኒው ጀነሬሽን ኮሌጅ የ4ኛ ዓመት የቢኤስሲ ነርሲንግ (BSc Nursing) ተማሪ የነበረችው ሂንሴኔ ተፈሪ፣ በትምህርቷ ጎበዝ፣ በትጋቷ በጓደኞቿ ዘንድ የምትወደድና ነገ ትልቅ ደረጃ ትደርሳለች ተብሎ ተስፋ የተጣለባት ወጣት ነበረች።

ነገር ግን ፤ ያ ሁሉ የዓመታት ልፋቷና ያማረ ህልሟ በአንድ ጀምበር ጨለመ። ለብዙ ዓመታት ለፍታ እዚህ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰችው ሂንሴኔ፣ የኮሌጁን የ15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር የትምህርት ክፍያ መክፈል አልቻለችም።

በዚህም ምክንያት ለዓመታት የደከመችበትን ሀገር አቀፍ የብቃት መመዘኛ (Exit Exam) መፈተን እንደማትችል በኮሌጁ ይነገራታል። ያሳለፈችውን ውጣ ውረድ የምታውቀው ሂንሴኔ፣ በብር ምክንያት ህልሟ ሲቀጭባት መቋቋም አልቻለችም። ጓደኞቿ በሙሉ ወደ ፈተና አዳራሽ ሲገቡ፣ እሷ ግን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ብቻ ወደ ኋላ ቀረች።

ይህ ብቸኝነት፣ የደረሰባት ከባድ የሥነ-ልቦና ጫና እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ወደ ከፋ ውሳኔ መራት ፤ የገዛ ሕይወቷን አጠፋች። ታሪኳ ሲሰማ ልብ ይሰብራል፣ ሕሊናንም ያደማል።

በብርሃን ፍጥነት ተመርቃ፣ ነጭ ጋውን ለብሳ የሰዎችን ሕይወት ልትታደግ የነበረችው ውዷ እህታችን፣ ዛሬ በ15 ሺህ ብር ምክንያት ሕይወቷ እንዲህ መቅጠፉ እጅግ ያማል! እጅግ ያበሳጫል!

ይህ አሳዛኝ ክስተት ለአንድ ማህበረሰብ ትልቅ የቤት ሥራና የህሊና ጥያቄ ነው። ዛሬ ስንት ሂንሴኔዎች በውስጣቸው እየተቃጠሉ፣ የሚረዳቸው አጥተው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይኖሩ ይሆን?! ለሂንሴኔ ተፈሪ ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቿና ለወዳጆቿ በሙሉ ፈጣሪ መጽናናቱን ይስጥ።

ማለዳ መረጃ - Maleda Merja

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Kazanchis
Addis Ababa