ክርስቲያን ዜና

ክርስቲያን ዜና

Share

Photos from ክርስቲያን ዜና's post 03/07/2026

ለዘማሪ ፓ/ር ሸዋዬ ዳምጤ ባለ 3 መኝታ አፓርታማ የቤት ስጦታ ተበረከተ

ዘማሪ ፓ/ር ሸዋዬ ዳምጤ ከ52 ዓመታት በላይ በዝማሬ አገልግሎት በገጠር፣ በከተማ እና ከሀገር ውጭ በትህትና ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ “ኑሮ ከጌታ ከኢየሱስ ጋር”፣ “በውቢቱ ኢየሩሳሌም” እና “አይቀደምም እግዚአብሔር” የተሰኙ ተወዳጅ መዝሙሮችን ጨምሮ በብዙ የአማኞች ልብ ውስጥ የተቀመጡ መዝሙሮችን አበርክተዋል።

የቤት ስጦታውን ያበረከቱት እህት “ለእኔ አስራት ነው፤ ለአንተ ደግሞ ደመወዝ ነው” በማለት ዘማሪ ፓ/ር ሸዋዬ ለአገልግሎት ላደረጉት ትጋት እና ዘመናት አመስግነዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከአዳማ ጀምሮ ከፓ/ር ሸዋዬ ጎን በመቆም እና የጎፈንድሚ ድጋፍን በማስተባበር ያገለገለው ዘማሪ ፓ/ር ያሬድ ማሩ “እግዚአብሔር የጸሎታችንን መልስ ሰጥቷል” በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ዘማሪ ጆይስም በወንጌላውያን የዘማሪዎች ህብረት ስም ደስታውን እና አድናቆቱን ገልጿል። በስነ ሥርዓቱ ላይም አሜን ቲቪ ተገኝቶ የዘገበም ሲሆን፣ የአሜን ቲቪ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሪት ሰብለ በቀለ በዚህ የአገልግሎት ጉዞ ውስጥ አብሮ እንደነበረ ሰው የተሰማትን ደስታ ገልጻለች።

Amen Tv Ethiopia

01/07/2026

ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተላለፈ አስቸኳይ የጸሎት ጥሪ!
"መከራ በሚደርስብህ ቀን ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ ፤ አንተም ታከብረኛለህ።" (መዝሙር 50:15)
በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ውድ ወገኖቻችን በምድሪቱ ላይ ሰላም ይሆን ዘንድ ካውንስሉ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወንጌላውያን አማኞችን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንዲማልዱ ጥሪውን ያቀርባል።
የምንጸልይ፣ የምንተባበር እና እርስ በእርስ የምንደጋገፍ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን፣ ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራት (Share በማድረግ) ለጸሎት ጥሪው እንዲቀላቀሉ አድርጉ።
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

20/06/2026

ገና LinkedIn እንደገባህ በ24 ዓመቱ የcompany CEO ስለሆነ አንድ ወጣት ታነባለህ

ቲክቶክ ላይ ደሞ የ19 ዓመት ሚሊየነር ታያለህ

ከዛ ስልክህን አጥፍተህ ኪስህ ውስጥ ያለውን 100 ብር እያየህ ትደነግጣለህ... "ጌታ ሆይ ምን በደልኩህ..እኔ ምን እየሰራሁ ነው? ጌታ ሆይይይ" የሚል ሽብር ውስጥህ ይፈጠራል

አይዞን!.. the overnight success illusion ይለዋል ሳይኮሎጂው

አላሸነፍክ ወይ አልተሸነፍክ.. ገና ስልክህን ከፍተህ ትንሽ scroll እንዳደረክ brain ሽብር በሽብር

by the way, አሁኑኑ ካልነቃህ ህይወትህን ወደ ገደል የሚመራው ትልቁ ስነ-ልቦናዊ ወጥመድ ይህ ነው

የ27 ዓመት ልምድ ያለውን ሰው ዛሬ ካንተ ጀማሪ ህይወት ጋር ታወዳድራለህ.. ያኔ በየቀኑ ምታደርገው natural growth ያስጠላሀል

መደበኛው ስራ ሰልችቶህ ቶሎ ለመበልጸግ ትጣደፋለህ... ይሄ ደግሞ ጤነኛ አእምሮህን ነጥቆ ለጭንቀት ለስርቆትና ለቁማር አሳልፎ ይሰጥሃል

"እነ እገሌ በቅጽበት ሚልየነር ሆኑ" የሚለው ውሸት ስለሚናፍቅህ ትኩረት ሰጥተህ ለዓመታት የሚገነባ ትልቅ ነገር መፍጠር ያቅትሃል

ግን psychology ፈጣን ስኬት አብዛኛው ጊዜ የፊልም ስክሪፕት ነው (የሆነ ያላየኸው የተቀባባ part or advantage ይኖራል እንደማለት ነው)

ኢንተርኔት ላይ በየቀኑ የምታያቸው ወጣቶች 1% ብቻ ናቸው (good luck for them) አንተ ግን ያንን አይተህ የራስህን 99% እውነተኛና ተፈጥሯዊ ዕድገት ትረግማለህ

Look, የበረሃ ዛፍ በአንድ ጀምበር አያድግም

የሰዎችን ፍጥነት አይተህ የራስህን ጉዞ አታበላሽ.. ዛሬ የምትሰራትን ትንሿን ስራ በፅናት ስራ then trust the process🫡

Photos from ክርስቲያን ዜና's post 17/06/2026

✍️christ Army church

የምረቃ ግብዣ መልዕክት
የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች መሥራችና ፕሬዝዳንት የሆኑት ነቢይ ኢዩ ጩፋ በሥነ-መለኮት (Theology) የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚቀበሉ በታላቅ ደስታ እናሳውቃለን።

ይህ የማስተርስ ምረቃ በመጀመሪያ በ2017 ዓ.ም. መግቢያ ላይ የታቀደ ቢሆንም፣ በእናታቸው ህልፈት ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ለኮሌጁ ጥያቄ በማቅረባቸው ፈቃድ እንደተሰጣቸው የኮሌጁ ምክትል ፕሮፌሰር ገልጸዋል።

በተጨማሪም ነቢይ ኢዩ ጩፋ የዶክትሬት (PhD) ጥናታቸውን በትጋት እየቀጠሉ ሲሆን፣ ለማጠናቀቅም በመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደደረሱ ፕሮፌሰሩ አስታውቀዋል። በመሆኑም በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እንደሚቀበሉ በይፋ ተረጋግጧል።
ስለዚህ በመጪው ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በመገኘት፣ ከነቢይ ኢዩ ጩፋ ጋር በመሆን ለእግዚአብሔር ምስጋና እንድታቀርቡ ሲሉ በአክብሮት ግብዣቸውን አቅርበዋል።ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ የጀመረውን ያጠናቅቃል።
**በአክብሮት፣** ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ጽሕፈት ቤት

Graduation Invitation Message
The Office of Christ Army International Church is pleased to announce with great joy that Prophet Eyu Chufa, Founder and President of Christ Army International Church, will receive his Master's Degree in Theology on June 21, 2026 (Sene 14, 2018 E.C.).
Although this Master's graduation was originally scheduled for the beginning of 2017 E.C., it was postponed for a period of time due to the passing of his beloved mother. According to the College's Vice President, Prophet Eyu Chufa formally requested an extension, which was graciously approved by the institution.
Furthermore, the Vice President stated that Prophet Eyu Chufa has continued his PhD studies with diligence and dedication and has now reached the final stage of completion. It has also been officially confirmed that he is expected to receive his Doctoral Degree (PhD) within the coming months.
Therefore, Prophet Eyu Chufa cordially invites you to attend the graduation ceremony to be held on June 21, 2026 (Sene 14, 2018 E.C.), and to join him in giving thanks and glory to God for this significant achievement.
“To God be the glory; He who began the good work is faithful to complete it.”
Respectfully,
Office of Christ Army International Church

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa