MELA AI

MELA AI

Share

02/08/2025

የተመረጡ የሰው-ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎቶች

ምስል የሚያመነጩ )Image generators).... የቀጠለ

Midjourney

Midjourney የAI ምስል ማመንጨት አለቃ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከ 2022 መጀመሪያ ጀምሮ የነበረና አሁንም ለሥዓላዊ ውበት እንዲሁም ለምስል-ወደ-ቪዲዮ ማመንጫነት መጠቀሚያ የሚሆኑ ምስሎችን ለመፍጠር አሁንም ተወዳጅ ነው።

እውነቱን ለመናገር፣ እኔ በአብዛኛው አብሮ የተሰራውን የምስል መሳሪያዎች እንደ ChatGPT ወይም Gemini ባሉ AI ረዳቶቼ ውስጥ እጠቀማለሁ። ነገር ግን በእውነት የሚያምር ነገር ማመንጨት ስፈልግ ወደ Midjourney እዞራለሁ።

አንዱ የMidjourney ጉዳቱ ነፃ እቅድ ከዚህ በዃላ አለመስጠቱ ነው። አንድ ምስል እንኳን ለማመንጨት ወደሚከፈልበት ደረጃ መመዝገብ አለቦት። ከ10 ዶላር በወር ጀምሮ አራት ዕቅዶች አሉ ከፍተኛ ደረጃዎች ተጨማሪ የማመንጫ ጊዜ(generation time) እና እንደ የቪዲዮ ድጋፍ እና የድብቅ ሁነታ(stealth mode) ያሉ የላቀ ባህሪያትን ይሰጣሉ።

ይቀጥላል.....⁣
ሰላማችሁ ብዝት ይበልልኝ።

ፔጃችንን መቀላቀል እንዳይረሱ!⁣
🄵🄰🄲🄴🄱🄾🄾🄺⁣
https://www.facebook.com/share/199EosEc3D/

🅃🄴🄻🄴🄶🅁🄰🄼⁣
https://t.me/mella_AI

🅈🄾🅄t🅄🄱🄴⁣
http://youtube.com/channel/UCBNrn1lTcxKbAKgh9OZ62gw?view_as=subscriber

02/08/2025

የተመረጡ የሰው-ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎቶች

ተንቀሳቃሽ ምስል የሚያመነጩ )video generators).... የቀጠለ

OpusClip

OpusClip ረዣዥም ቪዲዮዎችን ወደ አጭር በመቀየርና በመከፋፈል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሊጋሩ ወደሚችሉ ክሊፖች የሚቀይር ጥሩ መሳሪያ ነው። ለመጠቀም ቀላል ሲሆን ለቪዲዮ ኤዲተሮች ትልቅ ሸክም የሚያቀል ነው።

የ AI ፊቸሮች በሚያስደንቅ ሁኔታ የቪዲዮውን ምርጥ ክፍሎች ለማግኘት ውጤታማ ናቸው። ስለዚህ ቀረጻዎችን በማጽዳት ዕድሜ ማሳለፍ አያስፈልገንም። እንዲሁም እንደ TikTok እና Instagram ካሉ መድረኮች ጋር እንዲስማማ የሆኑ ክሊፖችን ይሰጠናል።

የመግለጫ ፅሁፎችን(captions) ለማከል ፈጣን እና ቀላል ነው። እና ስሜት ገላጭ ምስሎችን ጣል የማድርረግ አማራጭ ክሊፖችን የበለጠ ተለዋዋጭ(dynamic) ያደርገዋል። በተለይ scroll የማድረግ አባዜ ያለብን ሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ጠቃሚ ነው። ክሊፑን በጠንካራ ሁኔታ ለመጀመር ቁልፍ ክንውኖችን የሚመርጥ የ "hook" ባህሪውን በጣም ወድጄዋለሁ።

Opus Clip ቀደም ሲል ከሰራኋቸው ቪዲዮዎች ቀልብን የሚስብ ይዘቶች መፍጠር ቀላል ያደርገዋል። ተግባራዊ ፣ ቀልጣፋ እና አንዳንድ ጣጣዎችን ከማህበራዊ ሚዲያ አርትዖት ያስወጣል።

ምንጭ

ይቀጥላል.....
ፔጃችንን መቀላቀል እንዳይረሱ!
Facebook
Telegram
YouTube

MELA AI 30/07/2025

📖ዕለታዊ ትምህርት📖
ከሰው-ሰራሽ አስተውሎት አግልግሎቶች ገንዘባችንን ማዳን....የቀጠለ
👇👇👇👇👇👇
Avoid running up bills with our cost-saving tips

የAI አገልግሎት አማራጮች ብዙ ናቸው ። ነገር ግን ብዙዎቹ ከመሠረታዊ አግልግሎቶች በላይ የምንጠቀም ከሆነ ክፍያ ይጠይቁናል። በሐገራችን የውጭ ኦንላይን ክፍያ አማራጮች ስለሌሉ አብዛኛዎቻችንን ላይመለከት ይችላል። ይሁን እንጁ ኦንላይን ክፍያ አማራጭ ላለን ሰዎች ግን ሳይታወቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያዎችን በማውጣት ራሳችንን ልናገኝ እንችላለን። ታድያ ወጪዎችን ለመቀነስ መንገዶች አሉ ወይም ፣ የአጠቃቀም ልምድዎ በአንጻራዊ ሁኔታ ከፍ ያለ ከሆነና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመሞከር ከተዘጋጁ ፣ ሙሉ በሙሉ ከመክፈል መቆጠብ ይችላሉ። የAI አብዮት ኪስዎን እንዳያራቁቶት ለማረጋገጥ የተወሰነ ነገር እንበላችሁ

ነፃ አግልግሎቶችን ማሳደድ
ሁሉም የAI አገልግሎት ማለት ይቻላል ነፃ መጠቀሚያ ደረጃ ይኖራቸዋል። እነዚህ ግን አንዳንድ የቅርብ ጊዜ Features / AI models ላይ የአጠቃቀም ገደብ ሊኖራቸው ይችላሉ ነገር ግን በአንፃራዊነት ተራ የAI አግልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ ፣ የክሬዲት ካርድ መረጃዎን ሳይሰጡ ማግኘት መቻል አለብዎት። የአጠቃቀም ገደቦች ብዙውን ጊዜ በግልጽ አይገለፁም። ለምሳሌ AI አገልግሎት ላይ እንደ "በነጻ 10 መጠየቂያዎችን ብቻ ነው የሚያገኙት" ብሎ ማሳወቅ ያልተለመደ ነው። የ AI አገልግሎቶች ከፍተኛ ፍላጎት በሚኖርበት ጊዜ ነፃ የአጠቃቀም ገደቦችን ማየት ይጀምራል ፣ እና ገደቦች በምላሹ ርዝመት ሊወሰኑ ይችላሉ። አንድ AI የአንድ አንቀጽ ምላሽ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎችን ከጠየቁት ይልቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮምፒዩተር ኮድ መስመሮችን እንዲጽፍ ሲጠየቁ ቶሎ ነፃ አግልግሎቶችን ያነሳሉ። በአንድ አገልግሎት ላይ ነፃ ክሬዲቶች ቢያጡም ፣ ወደ ሌላ መሄድ ይችላሉ። ChatGPT እና Microsoft copilot assistant ብዙ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን ይጋራሉ ፣ ስለዚህ በአንዱ ላይ ገደብ ላይ ከደረሱ ሁል ጊዜ ሌላውን መጠቀም እና ተመሳሳይ ጥራት ያለው ምላሽ ማግኘት ይችላሉ። የአጠቃቀም ገደቦች በመደበኛነት በየቀኑ / በየሳምንቱ / በየወሩ አይደሉም። ከገደበን ከጥቂት ሰአታት በኋላ እንድንመለስ ይነግረናል።

የሚያስገቡትን Prompt በጥንቃቄ ያስቡበት

በነጻ ወይም ደግሞ የአጠቃቀም ገደብ ኖሮት በሚከፈል አግልግሎት ላይ ከሆኑ፣ ጥያቄዎን(Prompt) በሚጽፉበት ጊዜ ይጠንቀቁ። በቂ ዝርዝር እያቀረቡ መሆንዎን ለማረጋገጥ እና ለሚጠብቁት አይነት/የምላሽ ፎርማት የሚጠበቁ ነገሮችን ለማዘጋጀት ከዚህ ቀደም ያዘጋጀንላችሁን ምክሮች ይጠቀሙ። በሚቀጥሉት Prompts ላይ Alን የበለጠ የምንደጋግም ከሆነ የበለጠ ነፃ ክሬዲት እናቃጥላለን። በጥያቄዎቹ ላይ ጊዜን መውሰድና እና በመጀመሪያው ሙከራ በተቻለን መጠን ለመጨረስ መሞከር ይመከራል።

ይቀጥላል.....⁣
ሰላማችሁ ብዝት ይበልልኝ።

ፔጃችንን መቀላቀል እንዳይረሱ!⁣
🄵🄰🄲🄴🄱🄾🄾🄺⁣
https://www.facebook.com/share/199EosEc3D/

🅃🄴🄻🄴🄶🅁🄰🄼⁣
https://t.me/mella_AI

🅈🄾🅄t🅄🄱🄴⁣
http://youtube.com/channel/UCBNrn1lTcxKbAKgh9OZ62gw?view_as=subscriber

MELA AI

29/07/2025

📖ዕለታዊ ትምህርት📖
ከሰው-ሰራሽ አስተውሎት አሪፍ ውጤት ለማግኘት የሚጠቅሙን 10 ብልህቶች
.....የቀጠለ
👇👇👇👇👇👇

ከሰው-ሰራሽ አስተውሎት አሪፍ ውጤት ለማግኘት የሚጠቅሙን 10 ብልህቶች

Find out how to prompt your way to success
ሰው ሰራሽ አስተውሎት አግልግሎቶች ላይ የምንሰጠው ትዕዛዝ ፣ጥያቄዎች ወይም prompt ለምናገኘው ውጤት በጣም ወሳኝ ናቸው። ደካማ መጠየቂያዎች ብዙ ጊዜ አሳፋሪ ውጤቶችን ይሰጡናል ወይም ደግሞ የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ለማባከን ልንገደድ እንችላለን። ከዚህ በታች በቀረቡት የተመረጡ 10 ምክሮች በመጠቀም ከAI መገልገያዎች ጋር ያለንን ልምምድ በተሻለ ማሳደግ እንችላለን።

1. ገላጭ መሆን (BE SPECIFIC )
ትዕዛዞቻችን የበለጠ ግልጽ በሆነ መጠን የተፈለገውን ውጤት የማግኘት ዕድሉ ከፍ ያለ ነው። ለምሳሌ ፣ ሞናሊዛን የመሰለኝ እንስት ምስል ፈለግን እንበል፣ ምስል ማመንጨት አገልግሎት የሚሰጥ AI ጋር ሔደን የሚከተለውን የወረደ Prompt ብናስገባለት

Woman with a half-smile on her face.

የምናገኘውም ውጤት የወረደ ይሆናል።
ስለ ሴትየዋ ገጽታ ፣ እድሜዋ ፣ በምስሉ ጀርባ(Background) ስላለው እና ስለመሳሰሉት ለAIዩ ምንም አልነገርነውም።
የተሻለ Prompt የበለጠ ዝርዝርን መግለጫዎችን ያካትታል -

Oil painting of a white, young woman. The subject has dark brown, straight, shoulder- length hair and is wearing a flowing black dress with golden-brown sleeves. She has soft skin, a peaceful expression, and a mysterious half-smile. The full-body portrait features a beautiful landscape in the background
በሁለተኛው prompt ያገኘነው ምስል ከሞናሊዛ ምስል ጋር በፍፁማዊነት የሚመሳሰል ላይሆን ይችላል።ነገር ግን ከመጀመሪያው በተሻለ የቀረበ ነው። የተጠቀምነውም prompt አጭር መሆኑ ሳይዘነጋ
ሁለቱም ምስሎች በMidjourney የመነጩ ናቸው።(ስለ Midjourney ወደፊት በስፋት የምናይ ይሆናል)

2.ውጤቱን እንዲቀርብ የምንፈልግበትን መንገድ መግለጽ ( DESCRIBE THE DESIRED OUTPUT)
ሰው-ሰራሽ አስተውሎቱ ውጤቱን እንዴት እንደሚያቀርብልን የምንፈልግበት መንገድ በአእምሮዓችን ውስጥ ሀሳብ ካልን መግለፅ። ለምሳሌ:-

Summarise this email in five bullet points.

Generate an image of a cat lying in the sunshine in 4:3 aspect ratio.
3. ዓውድ ማቅረብ (PROVIDE CONTEXT)
ውጤቱን ስለምትፈልጉት ነገር ለAI የበለጠ መንገር በቻልን መጠን የተሻለ ይሆናል። ለምሳሌ ፣ ከዚህ በታች ከቀረቡት ትዕዛዞች ሁለተኛው Prompt ከመጀመሪያው የበለጠ ዓውዱን ይገልፃል።

Explain how a catalytic converter works.
Explain how a catalytic converter works to someone with no mechanical experience.
4. ውጤቶችን መደጋገም (ITERATE RESULTS)
በአንፃራዊነት ውስብስብ የሆኑ ሐሳቦችን AIን እየጠየቅን ከሆነ፣ በመጀመሪያው ጥያቄ የፈለግነውን የማግኘት እድላችን አነስተኛ ነው። በአንፃራዊነት ቀላል በሆነ ጥያቄ በመጀመር እና የምንፈልገውን ውጤት እስክናገኝ መደጋገም። ለምሳሌ፡-

Write a 500-word summary of the Falklands War and its impact on the relationship between Britain and Argentinaቀጥለን ደሞ ይህንን መጠየቅ እንችላለን
Focus more on the will of the Falkland islanders and their attitude to the conflict.
ይቀጥላል.....⁣
ሰላማችሁ ብዝት ይበልልኝ።

ፔጃችንን መቀላቀል እንዳይረሱ!⁣
🄵🄰🄲🄴🄱🄾🄾🄺⁣
https://www.facebook.com/share/199EosEc3D/

🅃🄴🄻🄴🄶🅁🄰🄼⁣
https://t.me/mella_AI

🅈🄾🅄t🅄🄱🄴⁣
http://youtube.com/channel/UCBNrn1lTcxKbAKgh9OZ62gw?view_as=subscriber

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa
1000