Ethio Times

Ethio Times

Share

19/05/2026

አክራሪ ክርስቲያኖች በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሳንዲያጎ በሚገኝ መስጂድ ላይ በተከፈተ የተኩስ እሩምታ 3 ሰዎች ተገደሉ!

• ​ሀሩን ሚዲያ | ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ል

​በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሳንዲያጎ ከተማ በሚገኝ መስጂድ እና ኢስላማዊ ማዕከል ላይ ትላንት ሜይ 18 ቀን 2026 ቀትር አካባቢ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት፣ የመስጂዱን ጥበቃ ጨምሮ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸው እና ሌሎች በርካቶች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገለጸ።

​ጥቃቱ የተፈጸመው ዕድሜያቸው ከ17 እስከ 19 በሚገመት ሁለት ወጣቶች ሲሆን፤ በመስጂዱ አቅራቢያ ተኩስ በመክፈት ጥቃት ለማድረስ በሞከሩበት ወቅት የመስጂዱ ጥበቃ የነበረው አሚን አብዱላሂ ከፍተኛ የመከላከል ስራ በመስራት የብዙዎችን ህይወት ካተረፈ በኋላ በተኩሱ ህይወቱ አልፏል። የ8 ልጆች አባት የሆነው አሚን አብዱላሂ የህጻናቱን ህይወት ጨምሮ በርካታ ሰዎችን ከሞት መታደጉን የአካባቢው ፖሊስ በይፋ ገልጿል።

​ጥቃት በተፈጸመበት በዚህ የኢስላማዊ ማዕከል ውስጥ በአልረሺድ ትምህርት ቤት የመድረሳ ትምህርት የሚማሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት የነበሩ ቢሆንም፤ በህጻናቱ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስ በፍጥነት ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ እንዲዛወሩ ተደርጓል።

​የአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ (FBI) እና የአካባቢው ፖሊስ የተፈጸመውን ጥቃት "ሊኖር የሚችል የጥላቻ ወንጀል" (Possible Hate Crime) በሚል መነሻነት ጥልቅ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን፤ በጥቃት አድራሾቹ ቁሳቁሶች ላይ ፀረ-እስልምና ጽሑፎች እና የናዚ ምልክቶች መገኘታቸው ጥቃቱ ከእስልምና ጥላቻ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ለመሆኑ ማሳያ እየሆነ ይገኛል።

​ክስተቱን ተከትሎ የአሜሪካ-ኢስላማዊ ግንኙነት ምክር ቤት (CAIR) ባወጣው መግለጫ፤ በሀገሪቱ የዕምነት እና የጸሎት ቦታዎች ደህንነት አለመጠበቅ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት ከጥቃቱ በኋላ በመስጂዱ ዙሪያ የፖሊስ ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚገኝ ተነግሯል።

​📅 ዙል-ሒጃ 2 ቀን 1447 ዓ.ሂ

​© ሀሩን ሚዲያ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa