WMCC

WMCC

Share

(WMCC) is a broadcast media company based in Addis Ababa, the political capital of Africa. The company which owns TV and Radio Stations aspires to become a pan African media company currently disseminating information in local and international languages. Walta has built its reputation through covering all aspect of Ethiopia and beyond in its professional news, documentary and programs reporting.

13/04/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ አቀባበል አድርገዋል።

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ብለዋል።

‎በቆይታዎ እጅግ ፍሬያማ ወይይት እንደሚኖረን እምነቴ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

Photos from WMCC's post 13/04/2026

በጎሮ ጉቱ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በተከሰተው አደጋም እስካሁን የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡

Photos from WMCC's post 13/04/2026

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ያለው የመራጮች ምዝገባ በምስል፡-

Photos from FMC Sport's post 13/04/2026

ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ አቻ ተለያዩ

13/04/2026

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛው ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ቀን 7 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ የሚገናኙ ሲሆን÷ በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 9 ሰዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይገናኛል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

Photos from WMCC's post 13/04/2026

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንዱስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።

የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

https://www.fanamc.com/, https://x.com/fana_arabic

Address

Addis Ababa