Binyam
"ከረፈደ ቢሆንም..."
አንዳንድ ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ለመረዳት የግድ መጎዳት፣ መልፋት ወይም ጊዜ ማባከን ይኖርብን ይሆናል::
እኔም "ረፈደ" የምለው ጊዜ አልፎ ሊሆን ይችላል፤ ግን በፍጹም አልመሸም!
ጊዜው ቢረፍድም፣ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍልም.
ዛሬ ላይ ቆም ብዬ ሳስበው አንድ ትልቅ እውነት በራሰኝ፡ ለማን፣ ምን መሆን እንዳለብኝ አሁን በሚገባ ገብቶኛል!.....
ለሚገባው ሰው ቦታ መስጠት፣ ለማይገባው ደግሞ መስመር ማበጀት መቻል ትልቅ የውስጥ ሰላም ነው::
ሰው ሁሉ በህይወታችን ውስጥ እኩል ቦታ ሊኖረው አይችልም:: ቦታን ለሚገባው ሰው ብቻ መስጠት መቻል የብስለት መጨረሻ ነውና ከአሁን በኋላ ራሴን ለማያስፈልግ ቦታና ሰው አላባክንም::
ስለዚህ፡
▹▹.... ለሚያከብሩኝና ለሚወዱኝ፡ ሙሉ ልቤን፣ ታማኝነቴንና ፍቅሬን እሰጣለሁ::
▹▹.... ለሚያልፉኝና ዋጋዬን ለማያውቁ፡ ፈገግታዬንና ርቀቴን እሸልማቸዋለሁ::
▹▹... ለራሴ፡ ደግሞ ሙሉ ትኩረቴን፣ ሰላሜንና እንክብካቤዬን እሰጣለሁ::
"ስለረፈደ አንቆጭም፤ ዋናው መባነኑ ነው!"
ረፈደ ብዬማ ተስፋ አልቆርጥም ዛሬ፣
በሚገባ ገብቶኛል የት እንደሆን ኖሮዬ::
ለማን ምን መሆን እንዳለብኝ አውቂያለሁ፣
ራሴን ለሰላም፣ መስመሬን አስምሬያለሁ!
●ሁሉንም ሰው ለማስደሰት አትጣር!
●እመነኝ ከአጉል መጋጋጥና መሰባበር ውጪ ምታተርፈው ነገር የለም
እዚህ ምድር ላይ ምንም ነገር ብታደርግ ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም!
ነብስህን እንኳን አሳልፈህ ብትሰጥ ሁሉም ሰው በአንተ ሊደሰት አይችልም!
በህይወት ስትኖር በሁሉም ሰው ልትጠላ በሁሉም ሰው ልትወደደት አትችልም
✅ በልብህ ያለውን ማድረግ ያለብህን እውነት ብቻ እያደረክ ቀጥል በአንተ የሚደሰተውም ይደሰት በአንተ የሚያዝነውም ይዘን
አንተ ብቻ #ትክክል የሆነውን ነገር ብቻ አድርግ ምርጫውን ለመራጩ ብቻ ተውለት!
እመነኝ ምንም ነገር ብታደርግ ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም!
#"ጀግና ወንድ ዝም የሚልበት 3ት, ነገሮች
1: ስያበሳጩሁ/ ስፈትኑህ ዝም በል።*
አንገትህን የሚያስደፋ ክርክር ውስጥ አትግባ። እውነተኛ ሃይል በቃላት ሳይሆን በድርጊት ይታያል። ንዴትህን ዋጥ።
2: ሲሰድቡህ ዝም በል።*
አንበሳ ከውሻ ጋር አይጫወትም። ዋጋህን የማያውቅ ሰው ላይ ጊዜህን አታባክን። ዝምታህ መልስህ ነው።
3: ሲያወዳድሩህ ዝም በል።*
ሩጫህ ከራስህ ጋር ነው። የሌላውን ሰዓት ተመልክተህ የራስህን አታበላሽ። ንጉስ ነህ። የራስህን ዙፋን ስራ።
አስታውስ: የወንድ ዝምታ ፍርሃት አይደለም። ቁጥጥር ነው።
#1: ማንንም ጓደኛ ወይም ፍቅረኛ ልሁን ብለህ አትለምን። ለለማኝ ቁራሽ እንጂ ዙፋን አይሰጠውም!
2: በተቀመጥክበት የማንንም እጅ አትጨብጥ። ዝቅ ብለው እንዲያዩህ አትፍቀድ!
3: ስሜቶችህ የበላይ እንዲሆኑብህ አትፍቀድ! ስሜታዊነት ያስበላሀል!
4: የትም ስትሔድ ሽክ ብለህ ልበስ! በመንገድ ማን እንደሚያገኝህ አታውቅም።
5: ወንድን ወንድ የሚያሰኘው ስራው ነው። ታታሪ ሰራተኛ እንጂ ቀፋይ አትሁን!
#❤“ቦታህ ላይ ሁን!”
1. ራስን ማግኘትና ማንነትን ማወቅ
በዚህ ዓለም ላይ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ልዩ ድርሻና ቦታ አለው። “ቦታህ ላይ ሁን” ሲባል መጀመሪያ “ቦታዬ የት ነው?” ብሎ ከመጠየቅ ይጀምራል። የራስን ተሰጥኦ፣ እሴትና ማንነት አውቆ በዚያ መቆም ለሕይወት ትርጉም ይሰጣል። ሌላውን ለመምሰል ከመሮጥ ይልቅ፣ የራስን እውነተኛ ማንነት ይዞ መገኘት ትልቁ ድል ነው።
2. ኃላፊነትን መወጣት
በሥራ ገበታ፣ በቤተሰብም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነት ውስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ የሚጠበቅበት ኃላፊነት አለ። “ቦታህ ላይ ሁን” የሚለው ጥሪ፣ የተሰጠህን አደራ በታማኝነትና በብቃት ተወጣ እንደማለት ነው። አንድ ሰው ቦታው ላይ ሲገኝ የጎደለው ይሞላል፣ የተዛባው ይስተካከላል።
3. ለሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን
ቦታውን የሚያውቅ ሰው እንደ ብርሃን ነው። ለሌሎች መመሪያና ተምሳሌት ይሆናል። አንተ ቦታህ ላይ ስትገኝ፣ ሌሎችም የራሳቸውን ቦታ እንዲፈልጉና እንዲያከብሩ ታበረታታቸዋለህ። ጸጥታውና መረጋጋቱ የሚመጣው ሁሉም የራሱን ድርሻ በትክክል ሲያውቅ ነው።
4. በራስ መተማመንና ጽናት
ሁኔታዎችና ማዕበሎች ሲመጡ ቦታን አለመልቀቅ የጽናት መገለጫ ነው። “ቦታህ ላይ ሁን” ማለት በችግር ጊዜ አትሸሽ፣ በፈተና ወቅት አትናወጥ፣ ለቆምክለት ዓላማ ታገስ እንደማለት ነው። ይህ ደግሞ በውስጣችን የማይናወጥ በራስ መተማመንን ይፈጥራል።
ባጠቃላይ፦
ቦታ ላይ መሆን ማለት ዝም ብሎ መቆም ሳይሆን፣ በሕይወት መድረክ ላይ የሚገባህን ሚና በብቃት መጫወት ነው። አንተ ስትኖር ነው ዓለም የምትሞላው፤ አንተ ቦታህ ላይ ስትሆን ነው ታሪክህ የሚዋበው።
“ቦታህን እወቅ፣ ቦታህን ውደድ፣ በቦታህም ላይ ጽና!
#ትዕግስት በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ካሉ ታላላቅ እና ጠቃሚ እሴቶች አንዱ ነው። "በትዕግስት የሚጠባበቅ ፍሬውን ይበላል" እንደሚባለው ሁሉ፣ በትዕግስት ውስጥ ብዙ በረከቶችና ጥቅሞች አሉ።
ትዕግስት ሲኖር የሚገኙ ዋና ዋና ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ጥራት ያለው ውሳኔ ለመወሰን
በችኮላ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ብዙ ጊዜ ስህተት ይበዛባቸዋል። ትዕግስት ሲኖር ግን ሁኔታዎችን በረጋ መንፈስ ለማየት፣ መረጃዎችን ለማመዛዘንና ውጤታማ የሆነ ምርጫ ለማድረግ ፋታ ይሰጣል።
2. የአእምሮ ሰላምና ጤና
ትዕግስት የሌለው ሰው ዘወትር በጭንቀት፣ በንዴትና በውጥረት ውስጥ ይኖራል። ትዕግስት ግን የውስጥ መረጋጋትን ይሰጣል። ይህም የደም ግፊትን ከመቀነስ ጀምሮ ለአጠቃላይ የአእምሮ ጤና ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
3. ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነት
ከቤተሰብ፣ ከጓደኛም ሆነ ከስራ ባልደረቦች ጋር በሚኖር ግንኙነት ውስጥ አለመግባባቶች መፈጠራቸው አይቀሬ ነው። በትዕግስት ሰዎችን ማዳመጥና በልዩነቶች ላይ መቻቻል ሲኖር ግንኙነቶች አይበላሹም፤ ይልቁንም መከባበርና ፍቅር ይነግሳል።
4. ግብን ከዳር ለማድረስ (ጽናት)
ማንኛውም ትልቅ ስኬት በአንድ ጀምበር አይመጣም። በመንገድ ላይ የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን በትዕግስት ማለፍ መቻል ለስኬት ቁልፍ ነው። ትዕግስት ያለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም፤ ይልቁንም በሂደቱ እየተማረ ወደ ፊት ይገሰግሳል።
5. ለራስ የሚኖር ክብር
በተፈጠረ ነገር ሁሉ ስሜታዊ ሆኖ ከመጮህ ወይም ከመበሳጨት ይልቅ፣ በትዕግስት ነገሮችን መቆጣጠር መቻል ትልቅ ሰብዕና ነው። ይህም ሌሎች ሰዎች ለእርስዎ ያላቸውን አክብሮት ይጨምራል፤ እርስዎም በራስዎ እንዲተማመኑ ያደርጋል።
ባጭሩ፦ ትዕግስት ማለት ዝም ብሎ መቀመጥ ወይም መሸነፍ ሳይሆን፣ ትክክለኛውን ጊዜና ሁኔታ በትክክለኛው አመለካከት የመጠበቅ ጥበብ ነው። ትዕግስት የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም።
🖊የሕይወት ጉዞና የሰው ሎጅ ጽናት
ሕይወት በውጣ ውረድ የተሞላች ረጅም መንገድ ናት። በዚህ ጉዞ ውስጥ ደስታና ሐዘን፣ ስኬትና ውድቀት ተራ በተራ ይፈራረቃሉ። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ግለሰቦች፣ በፈተና ወቅት ተስፋ ሳይቆርጡ በጽናት መጓዝ የቻሉ ናቸው። እውነተኛ ጥንካሬ የሚለካው ከላይ በሚታይ ቁመና ሳይሆን፣ በውስጥ ባለው የማይበገረው የመንፈስ ኃይል ነው።
በዚህ ዓለም ላይ ማንም ሰው ቢሆን ካለፈተና አይኖርም። ነገር ግን በፈተናዎች ውስጥ አልፎ አዲስ ማንነትን መላበስ የሚቻለው፣ ካጋጠመው ስብራት ትምህርት መቅሰም ለቻለ አእምሮ ነው። ስኬት የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን፣ በትጋት ለሚሰሩና በራሳቸው ለሚታመኑ ሁሉ የምትሰጥ ሽልማት ናት። ማንኛውም ሰው በውስጡ ያለውን እምቅ አቅም አውጥቶ ከተጠቀመ፣ ለራሱም ሆነ ለወገኑ የሚተርፍ ትልቅ ብርሃን መሆን ይችላል።
በመሆኑም፣ ዛሬ የምናልፍበት መንገድ አስቸጋሪ ቢሆን እንኳ፣ ነገ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ ማመን ትልቅ ብልህነት ነው። እርስ በእርስ መደጋገፍ፣ መከባበርና በቅንነት አብሮ መጓዝ ለሁላችንም ሰላምን ያመጣል። ሕይወታችን ትርጉም የሚኖረው ለሌሎች በሚተርፍ በጎ ተግባርና በጽኑ አቋም ስንጓዝ ብቻ ነው። ከትናንት ስህተት ተምሮ ለዛሬ በትጋት መኖር፣ ነገን በኩራት ለመቀበል ዋስትና ይሆናል።
ወንድ ልጅ ጥንካሬውን የሚያሳየው ስለ ስኬቱ በማውራት ወይም ሰውን በማስፈራራት አይደለም። እውነተኛው ወንድነት የሚገለጠው በሶስት ነገሮች ነው፡
1.ስሜትን መቆጣጠር፦ በከባድ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ተረጋግቶ ማሰብ። ጩኸት ድክመት ነው፤ ዝምታ ግን ስልጣን ነው።
2. ለቃል ታማኝነት፦ የምትናገረው ነገር ጥቂት ይሁን፣ የገባኸው ቃል ግን እንደ አለት የጠነከረ ይሁን። ወንድ ልጅ በቃሉ ይታወቃል።
3. ውጤት ላይ ማተኮር፦ ስራህን በዝምታ ስራ፤ ስኬትህ ደግሞ በታላቅ ድምፅ እንዲናገር ፍቀድለት። ስለ እቅድህ አትናገር፣ ውጤትህን አሳይ።
አንበሳ ሲያደን አይጮህም። ስትራቴጂ ያወጣል፣ በትዕግስት ይጠብቃል፣ ከዚያም ውጤታማ ይሆናል። ዛሬ በዝምታህ ውስጥ ትልቅ ነገር እየገነባህ እንደሆነ አውቃለሁ። አትድከም!
አንተስ በዝምታ ውስጥ እየሰራህበት ያለኸው "ትልቅ አላማ" አለህ?
ክብርህን ዝቅ አታድርግ📃🖊
ክብርህን መጠበቅ ማለት ትዕቢተኛ መሆን ሳይሆን ለራስህ ያለህን ዋጋ ማወቅ ነው። በሕይወትህ ውስጥ ማንነትህንና ክብሬን ዝቅ እንዳታደርግ የሚረዱህ ጥቂት ነጥቦች እነሆ፦
1. የራስህ መርህ ይኑርህ
ሰው በሄደበት ሁሉ አትሂድ፤ የራሱ አቋም የሌለው ሰው የሌሎችን ፍላጎት አስፈጻሚ ይሆናል። "አይሆንም" ማለት ያለብህን ነገር በድፍረት ተናገር። ለሰው ደስታ ብለህ የራስህን ሰላም አትገብር።
2. ዝምታን ልመድ
ክብርህ ዝቅ የሚለው ብዙ ጊዜ በማያስፈልግ ንግግርና ክርክር ውስጥ ስትገባ ነው። ብልህ ሰው የሚናገረውን ያውቃል፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ማለት ያለበትን ጊዜ ያውቃል:: ዝምታህ ካልተገባ ንግግርና ከትንሽ ሰዎች ትንኮሳ ይጠብቅሃል።
3. ድካምህን ለሁሉም አትናገር
ውስጥህ ቢጎዳም፣ ኑሮ ቢከብድህም ለገጠመህ ችግር ሁሉ ለሰዎች አትማጸን። ሰዎች የዛሬ ድካምህን አይተው ነገ ሊንቁህ ይችላሉ። ብርታትን ከፈጣሪህ እንጂ ከሰው አትፈልግ። በጥንካሬህ እንጂ በድካምህ አትታወቅ።
4. ቦታህን እወቅ
ባልተጋበዝክበት ቦታ አትገኝ፣ በማይመለከትህ ጉዳይ ውስጥ አትግባ። ክብርህ የሚጨምረው በምትገኝባቸው ቦታዎች ሳይሆን በማትገኝባቸው ቦታዎች ጭምር ነው። ራስህን ዝቅ አድርገህ ካቀረብክ ሰዎች እንደ ተራ ነገር ሊያዩህ ይችላሉ።
5. ለራስህ ዋጋ ስጥ
አንተ ለራስህ ክብር ካልሰጠህ ዓለም ክብር አይሰጥህም። አለባበስህ፣ አረማመድህና አነጋገርህ የማንነትህ መግለጫዎች ናቸው። ሁልጊዜም በራስ መተማመን ይኑርህ፤ አንተ የምትኖረው ለራስህ እንጂ ሰዎችን ለማስደሰት እንዳልሆነ እወቅ።
"ክብር እንደ መስታወት ነው፤ አንዴ ካደፈ ወይም ከተሰበረ ለመጠገን ይከብዳል። ስለዚህ ዛሬ ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ጥንቁቅ ሁን።"
ብልህ ሁን!!
ናይጀሪያዊያን "ድንጋይ በእንቁላል ላይ ቢወድቅ ወይም እንቁላል በድንጋይ ላይ ቢወድቅ ምንጊዜም ጉዳቱ የእንቁላሉ ነው።" የሚሉት ድንቅ አባባል አላቸው። በዚህ ዓለም ላይ ሁልጊዜ 'እውነት' ብቻውን አያሸንፍም። አንዳንዴ አቅም እና ጉልበት ካላቸው አካላት ጋር ስትጋጭ ጥፋቱ የማንም ይሁን የማን ዋጋ የምትከፍለው አንተ ነህ። ስለዚህ በህይወትህ ውስጥ በምትገባባቸው ፍልሚያዎች ላይ ብልህ ሁን። ደካማ ሁን ለማለት ሳይሆን የትኛው ሜዳ ላይ መጫወት እንዳለብህ እወቅ ለማለት ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.