Itad-Law-Blog

Itad-Law-Blog

Share

It should not be considered as a legal advice and readers are warned to take their own due-diligence!

20/08/2020

The government of Ethiopia has to stop using lethal force against peaceful demonstrators that are exercising their constitutional right to protest. Every extrajudicial killing by law enforcement authorities shall be swiftly investigated, deligently prosecuted and the offenders should be convicted based on law.
#

26/06/2020

በወንጀል ምርመራ ዉስጥ የተጎጂ ቤተሰቦች ሊኖራቸዉ የሚገባ ሚናና መብቶች
በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 15 መሠረት ማንኛዉም ሰዉ በሕይወት የመኖር መብት አለዉ፡፡ ይህ መብት በሕግ በግልጽ በተደነገገ ጊዜ ሊገደብ የሚችል መብት ነዉ (ኢትዮጽያ የሞት ቅጣትን ስላላስወገደች በሕግ አግባብ ለከባድ ወንጀሎች እንደ ቅጣት ተደንግጎ ሲገኝ፤ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ሲወስንና በርዕሰ ብሔሩ ይሁንታ ሲያገኝ ግለሰቡ በሕይወት የመኖር መብቱን ሊያጣ ይችላል)፡፡ ይህንን የሕገ መንግስት ድንገጋጌን በተሟላ መልክ ስራ ላይ ለማዋል ሰዉን መግደል በወንጀል የተፈረጀ ድርጊት ሆኖ እናገኛለን፡፡ በዚህም መሠረት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 538-545 ማንኛዉም ሰዉ በነዚህ አንቀጾች ከተደነገጉ መንገዶች (አደራረጎች) በአንዱ ክቡር የሆነዉን የሰዉ ሕይወት ያጠፋ እንደሆነ የወንጀል ኃላፍነትን እንደሚያስከትል በሕግ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጽያ ባጸደቀቻቸዉ ዓለም አቀፍና አህጉራቀፍ ስምምነቶች መሠረት ግለሰቦች በሕይወት የመኖር መብት አላቸዉ፡፡ ኢትዮጽያ በነዚህ ስምምነቶች የተቀበለቻቸዉን ግዴታዎች ለመፈጸም ሰዉን መግደል ወንጀል ነዉ በማለት በወንጀል ሕጉ መፈረጅ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ መንግስት የሰዉን ሕይወት ከፍርድ ዉጭ ከማጥፋት መቆጠብ ይነኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የሰዉ ሕይወት በሌሎች ግለሰቦች ድርጊት እንዳይጠፋ የመጠበቅና ወንጀልን የመከላከል ግዴታ አለበት፡፡ በዋናነት ደግሞ የሰዉ ሕይወት በመንግሰትም ይሁን በሌሎች ግለሰቦች ድርጊት ሲጠፋ ዉጤታማ የሆነ ምርመራ (effective investigation) በማድረግ ወንጀለኞችን ለሕግ አቅርቦ ተጠያቂነትን ማስፈንና የተጎጂዎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ምርመራ ዓለም አቀፋዊ መለኪያዎችንና ስነስርዓቶችን ለማሟላት ፈጣን (prompt)፤ ገለልተኛ (impartial)፤ የተጎጂዎችን ተሳትፎ ያረጋገጠ (victims participation) እንድዉም ጥልቅ፤ በትኩረትና በዝርዝር የሚከናወን መሆን አለበት (thoroughness)፡፡
ከጅምሩ የወንጀል ጉዳይ ሲፈጸም፤ የተጎጂ ቤተሰቦች ተገቢ በሆነ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ምርመራ እንዲጀመርና የፍርድ ሂደቱ እንዲጠናቀቅ የመጠየቅ መብት አላቸዉ:: በሁለተኛ ደረጃ የተጎጂ ቤተሰቦች የወንጀል ምርመራ በጥብቅ ትኩረትና በዝርዝር እንዲደረግ (Thoroughness) የመጠየቅ መብት አላቸዉ፡፡ በዚህም መሠረት ምርመራዉ ሲጠናቀቅ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች ማንነት የምርመራ ሂደቱን ሳይገድበዉ ላይ ላዩን ብቻ ሳይሆን በጥልቀት ተጠርጣሪዉ ወንጀሉን ለመፈጸም ያነሳሳዉ ምክንያት ምን እንደሆነ፤ በወንጀሉ ዉስጥ በዋና ወንጀል አድራጊነት፤ በማነሳሳት ወይም በአባሪነት የተሳተፉ እነማን እንደሆኑ ማረገገጥ መቻል አለበት፡፡ በተጨማሪም የወንጀል ምርመራ ግለሰባዊና ተቋማዊ ነጻነትን (operational and institutional impartiality and indipendence) በማረጋገጥ መከናወን አለበት፡፡ በወንጀሉ ዉስጥ የተሳተፉ ወይም ተሳትፎ ሊኖራቸዉ ይችላል ተብሎ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በመርማሪነት፤ በተቆጣጣሪነት ወይም ምርመራዉን በመምራት ረገድ ምንም ዓይነት ተሳትፎ ሊሰጣቸዉ አይገባም፡፡ ምናልባትም በምርመራ ተቋም ዉስጥ በኃላፍነትም ይሁን በፈጻሚነት የሚያገለግሉ ግለሰቦች፤ በወንጀል ድርጊቱ ዉስጥ ተሳትፎ ይኖራቸዋል ተብሎ ከተጠረጠሩ የምርመራ ሂደቱን ሊያስተጓጉሉ ሲለሚችሊ ለጊዜ ከኃላፍነታቸዉ ሊታገዱ ይገባል፡፡ ይህ ገለልተኛ መርማሪ ምርመራዉን እሱ/እሷ ወደፈለገበት/ችበት መምራት ሳይሆን ማስረጃዉ ወደሚመራበት ትኩረት በማድረግ ሊከናወን ይገባል፡፡

Want your practice to be the top-listed Law Practice in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Old Ambo Road
Addis Ababa
1000