Tibeb Media.com
15/02/2026
ይድረስ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ውስጥ የምርጫውን ተአማኒነትና ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚፈጥሩ የመንግስት ህገወጥ ጣልቃ ገብነት ጎልቶ ስለ ወጣ ቦርዱ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ለማሳሰብ የተላለፈ መልእክት ነው ።
ገዢው ፓርቲ የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በርካታ የህግ ጥሰቶች ተፈፅመዋል ።
ፓርቲው የምርጫ ምልክቱን ይፋ ባደረገበት ቅፅበት በስልጤ ዞን በህዝብና በመንግሥት ገንዘብ የሚንቀሳቀሱ ሁሉንም ፓርቲዎች በገለልተኝነት ማገልገል የነበረባቸው የሚዲያ ተቋማት የፓርቲውን መፈክር በማስተጋባት የምርጫውን ሚዛን ለማሳት ሞክረዋል ።
የስልጤ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ፤ የማህበረሰብ ሬዲዮ የሆነው የስልጤ FM 92.6 ሬዲዮ ተጠቃሽናቸው ።
"ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር " በሚል መሪህ ቃል ከብልፅግና ህብረት አባላት የምርጫ ምልክት ማስተዋወቅ ባሉት ፕሮግራም ላይ ።
በርካታ የመንግስት እና የህዝብ ንብረት እና ገንዘብ በመጠቀም የመንግስት በጀትና ንብረት ለምርጫ ቅስቀሳ መጠቀም የሚከለክለው የምርጫ ስነስርዓት አዋጅ ተጥሷል ።
ከዞን ወደ ወረዳ ለመደገፍ የሄዱ የዞን የመንግስት ባለ ስልጣናት በመንግሥት ተሽከርካሪዎች ለምርጫ ቅስቀሳ በብዛት ተጠቅመዋል ፤ ከመንግሥት በጀት ነዳጅ ሞልተዋል ።
የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ብቻ መምራት የነበረበትን ጉዳይ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ወለላ ፤ የዞኑ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ሀላፊ አቶ አብዱራህማን ወርቂቾ ፤ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መመሪያ ሀላፊ አቶ ሙበራ የዞኑ ምክርቤት አፈ ጉባኤ ክብርት መህዲያ ወዘተ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የተቋሞቹን ንብረቶች ለዚህ የቅስቀሳ አላማ አውለዋል ።
የዞኑ መንግስት በግልፅ በአደባባይ በገለልተኛነት ምርጫ ማስተናገድ የማይችል መሆኑን አረጋግጧል ፤ በዚህም ሁሉም የመንግስት መስሪያቤቶች በግልፅ ለአንድ ፓርቲ በወገኑበት ሁኔታ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ ሊደረግ አይችልም ።
ዞኑ ውስጥ የምርጫው ደህንነት ያስጠብቃሉ ተብለው አደራ የተጣለባቸው የፀጥታ መዋቅር በግልፅ የፓርቲውን ፕሮግራም እስከ መምራት ደርሰዋል ።
በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች በሚሰሩባቸው ተቋማት ከወዲሁ የተለያዩ ጫናዎች እየተፈጠረባቸው
ይገኛል ።
የመንግስት ሰራተኞች ህገወጥ በሆነ ሁኔታ የፓርቲው አባል እንዲሆኑ እየተገደዱ ሲሆን አባል ሆኑም አልሆኑም የፓርቲ መዋጮ በየወሩ በደምወዛቸው ይቆረጣል ።
ምርጫ ቦርድ በእነዚህ የምርጫውን ተአማኒነት ና ገለልተኛነት አደጋ ላይ የሚጥል ግልፅ የህግ ጥሰቶች ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ለማሳሰብ እንወዳለን ።
ከተፎካካሪ ፓርቲዎች የተላለፈ መልእክት ☝️☝️
Click here to claim your Sponsored Listing.