Gebeya

Gebeya

Share

26/07/2020

ሰሜን ኮሪያ 'የመጀመሪያውን' የኮሮናቫይረስ ተጠርጣሪ ማግኘቷን አስታወቀች
*********************
ሰሜን ኮሪያ በአገሪቱ የመጀመሪያው የተባለውን በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች።
በሽታው እንዳለበት የተጠረጠረው ግለሰብ ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድቶ ሄዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በድንበር በኩል ወደ ሰሜን ኮሪያ ከተመለሰ በኋላ የወረርሽኙ ምልክቶች የታዩበት መሆኑን ቢቢሲ የአገሪቱን መንግሥት የዜና አገልግሎት ጠቅሶ ዘግቧል።
ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸውን ሰብስበው ከደቡብ ኮሪያ ጋር በምትዋሰነው የድንብር ከተማዋ ኬሶንግ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ማድረጋቸው ተገልጿል።
ለመረጃ ዝግ የሆነችው ሰሜን ቀደም ሲል በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው እንደሌለባት ስታሳውቅ ብትቆይም፣ ተንታኞች ግን ሊሆን እንደማይችል ሲገልጹ ቆይተዋል።
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አስቸኳይ ስብሰባ መሪው ኪም ጆንግ-ኡን የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር "ከፍተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ሥርዓት" እንዲዘረጋ ማዘዛቸው ተወስቷል።
መሪው ኪም ጆንግ-ኡን በበሽታው የተጠረጠረው ግለሰብ በከፍተኛ ጥበቃ ስር ባለው የድንበር አካባቢ ከደቡብ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዴት አልፎ ሊገባ እንደቻለ እንዲመረመር ያዘዙ ሲሆን፤ ተጠያቂ የሚሆኑ ሰዎች ላይ "ከባድ የቅጣት እርምጃ" እንዲወሰድባቸው ማዘዛቸውም ነው የተነገረው።
ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ በተመሳሳይ ጊዜ ምንም አይነት ሕገ ወጥ የድንበር ማቋረጥ ክስተት እንዳልነበረ ማስታወቋ ተገልጿል።
ከስድስት ወራት በፊት ቫይረሱ በዓለም ዙሪያ መስፋፋት በጀመረበት ጊዜ ሰሜን ኮሪያ ድንበሮቿን ዘግታ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቆያ ውስጥ አስገብታለች።
በዚህ ወር መጀመሪያ ገደማ ላይ መሪው ኪም ጆንግ-ኡን አገራቸው በኮሮናቫይረስ ላይ "አንጸባራቂ ስኬት" እንደተቀዳጀች አሳውቀው ነበር ነበር ብለዋል።

23/06/2020

Gebeya News 📰🗞

ከግብፅ የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን ኤጀንሲው አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14/2012 ዓ.ም መቀመጫቸዉን ግብፅ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል።
የሳይበር ጥቃት ሙከራው የተቃጣው ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች አማካይነት መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።
ወንጀለኞቹ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጁ የቆዩ እና ኤጀንሲው ሲከታተላችው የነበሩ ሲሆን፥ በይበልጥ አርብ ሰኔ 12/2012 እና ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ከፍተኛ የሚባል የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ማድረጋቸውን ኤጀንሲው ገልጿል።
በዚህ ጊዜ ዉስጥ የ13 የመንግስት፣ 4 መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የድረ-ገጽን የማስተጓጎል ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውቋል።
የሳይበር ጥቃት ሙከራው በሀገሪቱ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የደህንነት መስሪያ ቤቶች እና የግል ድርጅቶች ድረ-ገጽ ላይ ያነጣጠረ ነበር።
ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድኖች ሃላፊነቱን የወሰዱ ሲሆን፥ ዋና አላማቸዉም ከህዳሴው ግድብ ዙሪያ በተለይ በውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ሁሉን አቀፍ ተጽእኖ በሀገሪቱ ላይ ለመፍጠር በማሰብ እንደፈጸሙት ገልጸዋል።
የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት አብዛኛዎቹ በድረ-ገጽ ግንባታ ሂደት ደህንነታችው ታሳቢ ያላደረጉ ተቋማት፤ በቀጣይነት የደህንነት ፍተሻ ያላደረጉ እና ከፍተኛ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት የነበረባቸው መሆኑንም ኤጀንሲው አረጋግጧል።
ኤጀንሲው አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት በማድረጉ ምክንያት እና ይህን መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት መከላከል ባይችል ኖሮ ጥቃቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖሊቲካዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበርም ገልጿል።
በመከላከሉም ሊደርሱ የሚችሉ ከፍተኛ አደጋዎችን ማስወገድ መቻሉን እና ይህንንም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ማሳወቁንም ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በቀጣይም መሰል ጥቃቶች በስፋት፣ በረቀቀ መንገድ እና ከተለያዩ ስፍራ ሊሰነዘር እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት .et domain ከመጠቀማቸው በፊት የድረ-ገጻቸውን ደህንነት አረጋግጠው እንዲጠቀሙ፤ ራሳቸውን ከሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት ለመከላከል እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚኖርባቸው አሳስቧል።
ተቋማት ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ያለባቸውን የደህንነት ተጋላጭነት መድፈን እንዳለባችው እና የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥማቸውም ሆነ ሙያዊ ድጋፍ ሲያሻቸው ለኤጀንሲው በማሳወቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቋል።
ባለፉት ሁለት ቀናት ትብብር ላደረጉልን ተቋማት እና ግለሰቦች በተለይ ለኢትዮ ቴሌኮምና ለኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኤጀንሲው ምሰጋና አቅርቧል።

21/06/2020

Gebeya News 🗞📰

ዴክሳሜታሶንን በሚመለከት የተሰጠ ማሳሰቢያ!

(ዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር)

በቅርቡ የዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) መድሃኒት ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ቢያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን ዘንድ ሊከሰት የሚችለውን የሞት አደጋ መቀነስ እንዳስቻለ መገለፁ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር በሀገራችን ኦክሲጅን ወይም መተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሞያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታሶን እንደ ድንገተኛ ህክምና ጥቅም ላይ እንዲውል ተወስኗል።

ነገር ግን ዴክሳሜታሶን የኮቪድ-19 መድሃኒት ያለሆን እና ለመከላከል የማይጠቅም ሲሆን የራሱ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለው ግንዛቤ እንዲወሰድ እና ያልታመሙ ሰዎች ያለ ህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ ከወሰዱት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ሕብረተሰቡ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መድሃኒቱን እንዳይወስድ እንዲሁም የፋርማሲ እና ሌሎች የጤና ባለሞያዎችም የዴክሳሜታሶን መድሃኒትን ያለ ሃኪም ትዕዛዝ ለደንበኞቻቸው መሸጥ እንደሌለባቸው በአፅንኦት እናሳስባለን።

Want your business to be the top-listed Clothing Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
00251