Fidel Tube
02/12/2020
በመቀሌ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኘ
የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት መቀሌ ላይ መከላከያ የማያወቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኝቷል።
የጁንታው ቡድን ውጊያውን መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እያራገፈ ፈርጥጧልም ብለዋል።
ከዚህ ውስጥ ሰራዊቱ የማያውቀው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ዲፖ ተገኝቷል ብለዋል
የሰሜን እዝ አመራሮችን ጠይቀን ስለዲፖው እንደማያውቁ ገልጸውልናል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፤ በቀጣይም ተመሳሳይ የመሳሪያ ማከማቻወችም ሊገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
በመሆኑም እነዚህ ከቀላል እስከ ቡድን መሳሪያዎች ወንጀል እዳይፈጸምባቸው የፍተሻ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢዜአ
27/05/2020
Ethiopian Body builder Tsega Worku Full Body at Home Workout ቤታችን ውሥጥ መስራት የምንችለው ቀለል ያለ እስፖርት
22/05/2020
በኢትዮጲያ 30 ተጨማሪ ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው‼️
በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 429 ደርሷል፡፡
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-⬇️
~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ3645 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 30 ኢትዮጲያዉያን ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡
~ 26ቱ ወንዶች ሲሆኑ 4ቱ ደግሞ ሴት ናቸው።እድሜያቸዉ ከ15 እስከ 60 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።
~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 18 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣4 ሰዉ ከአሮሚያ ክልል(ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ )፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል ፣3 ሰዉ ከትግራይ ክልል፣2 ሰዉ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ
~ 9 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡
~ 17 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡
~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 4 ሰዎች ናቸው።
ተጨማሪ መረጃ ፦
~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 73,164 ደርሷል።
~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5 ሰዎች አገግሟል።
~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 128 ደርሰዋል።
~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ ታማሚ የለም ፡፡
~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 294 ናቸው።
~ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
21/04/2020
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 745 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ42 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታው ሰበታ ዞን ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 2 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በስራው ባህሪ ለበሽታው ተጋላጭነት ያለው።
ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ ከሳዑዲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Opening Hours
| 00:00 - 12:00 |