Selam

Selam

Share

ጡት ማጥባት የሚሰጣቸው የጤና ጥቅሞች - Benefits of breastfeeding 02/08/2022

📆 የአለም ጡት የማጥባት ሳምንት(ሐምሌ 25- ነሀሴ 1)-World breast feeding week(August 1-7)

✍ጡት ማጥባት የሚሰጣቸው ጥቅሞች

የእናት ጡት ወተት ለጨቅላ ህፃናት ከተወለዱ ጊዜ ጀምሮ ተፈጥሯዊ ምግባቸው ሲሆን በተለይም በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ለሰውነታቸው የሚያስፈልገውን ሀይልና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች አካቶ የያዘ ነው፡፡በተጨማሪም ህፃኑ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃና ከስድስት ወር በኋላ እስከ ሁለት አመት ድረስ ከተጨማሪ ምግብ ጋር የእናት ጡት ወተትን እንዲጠቀም ይመከራል፡፡ይህም ለልጁ ጤናማ እድገትና ለውጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

📌ጡት ማጥባት ለልጁ የሚሰጣቸው ጠቀሜታዎች

የጡት ወተት ለህፃኑ ሰዉነት የሚስፈልጉትን አብዛኞቹን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችና በቂ ፈሳሽ አሟልቶ መያዙ

በእናት ጡት ወተት ውስጥ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች በቀላሉ በህፃኑ ኢንዛየሞች መፈጨት የሚችሉ መሆናቸው

በሽታን ሊያመጡ ከሚችሉ በአይን የማይታዩ ጎጂ ተዋስያን ነፃ መሆኑ

ከሌሎች የጡት ወተትን በመተካት ከምንጠቀባቸዉ አማራጮች አንፃር ሲታይ የእናት ጡት ወተት ህፃናት በተለያዩ ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የመያዝ እድላቸውን መቀነሱ

የእናት ጡት ወተት ይዘት ከህፃኑ የሰውነት ለውጥና እድገት ጋር አብሮ የሚቀየር መሆኑ

📌ጡት ማጥባት ለእናቶች የሚሰጠው ጥቅም

ጡት ማጥባት ለህፃናት ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ ለእናቶችም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን ይሰጣል፡፡

1. ማህፀንን ከእርግዝና በፊት ወደነበረበት መጠን መመለስ

2. ከወሊድ በኋላ የሚፈጠር ከፍተኛ የደም መፍሰስን መከላከል

3.የወር አበባ መመለሻ ጊዜን በማዘግየት ተፈጥሮአዊ የእርግዝና መከላከያ መንገድ በመሆን ማገልገል

📌 በዚህ ፅሁፍ ስር ተጨማሪ ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇

ጡት ማጥባት የሚሰጣቸው የጤና ጥቅሞች - Benefits of breastfeeding ከእናት ጡት ወተት አንድ ህፃን የሚያገኛቸው ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች

ቫይታሚን ዲና የፀሀይ ብርሃን ያላቸው ግንኙነት - Vitamin D and Sunlight 19/07/2022

✍ # ቫይታሚን ዲና # የፀሀይ ብርሃን ያላቸው # ግንኙነት #

👉 የቫይታሚን ዲ ምንነትና ጥቅም

ቫይታሚን ዲ ለሰዉነታችን እድገትና ጤናማ ስራ አስፈላጊ ከሆኑት ንጥረ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የምናገኘዉም በተወሰነ መጠን ከምንበላው ምግብና በዋነኝነት በፀሀይ ብርሃን ተጠቅሞ ሰውነታችን በሚያመርተው ሆርሞን አማካኝነት ነው።ይህ ንጥረ ነገር ከሚሰጣቸው ጠቀሜታዎች ውስጥ ሰውነታችን ጤናማ የሆነ የካልሺየምና ፎስፈረስ ዝዉዉር እንዲኖረው ማድረጉና ለአንጥት እድገትና ጥንካሬ ያለው ሚና በዋነኝነት ይጠቀሳል።

👉 የቫይታሚን ዲ ምንጮች

📌 እንጉዳይ፣ወተት፣የእንቁላል አስኳል፣ጉበትና ስብ ያለው አሳ(fatty fish) ቫይታሚን ዲን ከሚይዙ የምግብ አይነቶች የሚጠቀሱ ሲሆን በዋነኝነት ግን ቫይታሚን ዲን የምናገኘው የፀሀይ ብርሀን ከሰውነታችን ጋር በሚፈጥረው መስተጋብር ሰውነታችን ቫይታሚን ዲን ማምረት ሲጀምር ነው።

👉 ቫይታሚን ዲ ከፀሀይ ብርሃን ጋር ያለው ግንኙነት

ቫይታሚን ዲ ከፀሀይ ብርሃን ጋር ባለው ጠንካራ ግንኙነት ምክንያት በተለምዶ ከፀሀይ የሚገኘው ቫይታሚን(Sunshine vitamin) በሚል አጠራር ይታወቃል ።ነገር ግን በተለምዶ እንደሚባለው ቫይታሚን ዲ የሚገኘው በቀጥታ ከፀሀይ ብርሃን ሳይሆን የፀሀይ ብርሃን በቆዳችን ላይ ከሚገኘዉና ሰውነታችን ቫይታሚን ዲ የማምረት ሂደቱን እንዲጀመር በማድረግ የሆርሞንን ሚና ከሚጫወተው ኮሌስትሮል(Vitamin D3 ) ጋር በሚፈጥረው መስተጋብር አማካኝነት ነው።

📌በዚህ ርዕስ ስር ተጨማሪ ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ቫይታሚን ዲና የፀሀይ ብርሃን ያላቸው ግንኙነት - Vitamin D and Sunlight

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa