Oromo unity

Oromo unity

Share

20/06/2026

Yaa oromoo dhimma ummata keenya arsii kana maaf calliftan!!

16/06/2026

የ28ቱ ኢማሞች ግድያ እና የተገላቢጦሽ ፍረጃ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በአሕመዲን ጀበል፣ክፍል አንድ
✅✅✅✅✅✅✅✅✅

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላለፉት በርካታ ዓመታት በአካላቸው፣ በእምነት ተቋማቶቻቸውና በማንነታቸው ላይ የሚፈጸሙትን ሁሉን አቀፍ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና መዋቅራዊ በደሎች በሆደ-ሰፊነትና ለሀገር ሰላም ቅድሚያ በመስጠት በትዕግስት ሲያሳልፉ ቆይተዋል።

በደል አድራሾቹን በጅምላ ከመክሰስና ወንጀሉን ማህበረሰባዊ መልክ ከመስጠት ይልቅ፣ ድምፃቸውን ለፍትህ ብቻ በማሰማት የበኩላቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ተወጥተዋል። ሆኖም ግን፣ ከእነዚህ አሰቃቂ ጥቃቶች ጀርባ ያሉና ለሙስሊሙ መከራ ዋና ተጠያቂ የሆኑ የጥላቻ ልሳናት፤ በተደራጀ የሚዲያ ዘመቻ እውነተኛውን ተበዳይ መልሰው አጥቂና ወንጀለኛ አድርገው የሚፈርጁበትን የተገላቢጦሽ የፕሮፓጋንዳ ስልት በስፋት እየተገበሩ ይገኛሉ።

በተለይ በቅርቡ በአርሲ ከተፈጸመው ጥቃት ማግስት የታየው ጸረ-ሙስሊም የሚዲያ ትንኮሳና የሀሰት መቀናበር፤ እነዚህ ፅንፈኛ አካላት በሀገሪቱ ውስጥ መጠነ-ሰፊ የሃይማኖት ግጭት ለመጫርና በሙስሊሙ ላይ የተቀነባበረ የኢስላሞፎቢያ (Islamophobia) ንፋስ ለማንፈስ እንደሚፈልጉ በግልጽ ያሳየ ክስተት ነው።

ይህ ጽሑፍ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በትናንትናውም ሆነ በዛሬው ሥርዓት ውስጥ ማቆሚያ ያላገኙትንና ማህበረሰቡን ዘወትር እሳት በማጥፋት ላይ ብቻ እንዲጠመድ አድርገው የተተዉትን እረፍት የነሱ የመብት ጥሰቶች፣ ጥቃቶችና ግድያዎች በዝርዝር ያሳያል። ከእነዚህም መካከል የመስጂዶች መፍረስና ቃጠሎ፣ እንደ አክሱምና ላሊበላ ባሉ አካባቢዎች መሠረታዊ የእምነት ነጻነቶችን እንኳ ማጣት፣ እንዲሁም እዚሁ አዲስ አበባን ጨምሮ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉ ሀገራዊ ስመ-ጥር ተቋማት ውስጥ በውስጣዊ መመሪያ የሙስሊሞች የእምነት ነጻነት ተጥሶ መቀጠሉ የዚሁ ዘላቂ መከራ ማሳያዎች ናቸው።

ለቅሶን የመቀማት ስልት እና የተገላቢጦሽ ፍረጃ
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

እነዚህና በርካታ የመብት ጥሰቶች እያሉበትም እንኳ፣ እንደ ሌላው ማህበረሰብ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚንቀሳቀስ የሙስሊሞች የተደራጀና የታጠቀ ኃይል በሌለበት ሁኔታ፤ የማህበረሰቡን የትዕግስት ልክ የሚያሳየው ይህ እውነታ ራሱ በተገላቢጦሽ ተጠቂውን ማህበረሰብ በፍረጃ ኢላማ ያደረጉ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን እያስተናገደ ይገኛል።

የሚገርመው ደግሞ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻው መሪዎችና ተሳታፊዎች፤ ራሳቸው ለአብዛኛዎቹ የሙስሊሞች ጥቃቶች አቀናባሪዎችና ተዋናዮች መሆናቸው ነው። እነዚህ አካላት በኦርቶዶክስ ክርስትና ‘ሞዓ ተዋሕዶ’ እና ‘ፋኖ’ የርዕዮተ-ዓለም ጥምረትና ቁርኝት የተደራጁ፣ እንዲሁም በሃይማኖት ጥላቻ ተነሳስተው ሙስሊሞችን እያጠቁ ያሉ አካላት ደጋፊዎች ናቸው።

የእነዚሁ አካላት የማህበራዊ ሚዲያ ክንፎች በተደራጀ መልኩ ከአካባቢያዊ ይዘት ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ያሳደጓቸው ለጥቃት የማመቻቸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች፤ ከዓመታት በፊት በአማራ ክልል በጥላቻ በተሞላ ቅስቀሳ ምክንያት የክልሉ ሙስሊሞች ጥቃቶችን ያስተናገዱባቸው ክስተቶች ሀገር አቀፍ ቅጂዎች ናቸው።

ይህ ሁኔታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሃይማኖት ግጭት በመፍጠር ሀገሪቱን ለማተራመስና ሕዝበ ክርስቲያኑን በሃይማኖት ጎራ በማሰለፍ ‘በዚያ ውስጥ እናተርፋለን’ ብለው ያቀዱት የተሳሳተ ዕቅድ አካል ነው። መስሏቸው ነው እንጂ በዚህ አካሄድ የኢትዮጵያ ጠላቶች ካልሆኑ በቀር ሀገሩንና ሕዝቡን የሚወድ፥ የሀገሩ ሁኔታ ግድ የሚለው ሁሉ ፈጽሞ ከሀገራችን መተራመስ የሚያተርፈው አይኖርም።

የሚዲያዎችንና የፖለቲካ ልሳናትን ዘገባዎች ስንታዘብ፤ እውነታውን የማድበስበስና ‘የቅኝት ልወጣ’ (Framing) የማድረግ ስልታዊ አካሄድ በጉልህ ይታያል። አብዛኛው ተጠቂ ሙስሊም በሆነበት ክስተት ላይ-የማህበረሰቡ ሃይማኖታዊ መታወቂያ እንዲደበቅና ጥቃቱ እንዲቃለል-ብሔራቸው ብቻ እንዲጎላ ተደርጎ «አማራ ተጠቃ» ይባላል።

በተቃራኒው ደግሞ የተጠቂዎቹ እምነት ክርስቲያን ሲሆን፣ ብሔራቸው ታልፎ «ኦርቶዶክስ ተገደለ» በሚል ሃይማኖታዊ መልክ እንዲይዝ ይደረጋል።
ይህ የተገላቢጦሽ አካሄድ በተቋማትና በሃይማኖት መሪዎች ላይም ይደገማል፤ ታዋቂ ሼኽና ኢማም ሲጠቁ ማንነታቸውን ለመሰወርና የጥቃቱን ባህሪ ለመደበቅ ሲባል «አንድ የሃይማኖት አባት» በሚል በደፍኑ ይጠቀሳል። ቤተ-ክርስቲያን ሲጠቃ «ቤተ-ክርስቲያን ተቃጠለ/ተደፈረ» ተብሎ ቀጥተኛ ስሙ የሚጠራ ሲሆን፥ መስጂድ ሲፈርስ ወይንም ሲቃጠል ግን ስሙ ተለዝቦ «የእምነት ተቋም ተጠቃ» በሚል አጠቃላይ አገላለጽ ይሸፈናል።

ይህ ሁሉ የሙስሊሙን ተበዳይነት የመሰወርና ‘የሙስሊሞችን ለቅሶ የመቀማት’ ስልት ነው። ለቅሶን መቀማት ደግሞ ተራ ነገር አይደለም፤ ልክ ታሪክን እንደ መቀማት ይቆጠራል። ታሪክና ለቅሶ ሲቀሙ፣ በአሁኑም ሆነ በቀጣዩ ትውልድ ዘንድ የማንነትና የክስተቶች ግንዛቤ መዛባት (Cognitive Distortion) እንዲፈጠር ስለሚያደርግ፣ ተበዳዩን ማህበረሰብ ድምፅ አልባ የማድረግ ዘላቂ ሂደት አካል ነው።

የእነዚህ አካላት አውዳሚ አካሄድ ግን በዚህ ብቻ አልተገደበም። ይልቁኑ እጅግ ርቀው በመጓዝ፣ እውነተኛውን ተበዳይ ሕዝበ-ሙስሊም መልሶ ወደ መወንጀል ደረጃ ደርሰዋል። በደል አድራሾቹ ሰለባውን መልሰው በወንጀለኛነት የሚፈርጁት፣ የራሳቸውን ታሪካዊና መዋቅራዊ ጥቃት ለመሸፈን በሚቀይሱት ስልታዊ የፕሮፓጋንዳ ማጭበርበር ነው።

ይህ የተገላቢጦሽ ፍረጃ ተበዳዩ ማህበረሰብ ለፍትህ የሚያሰማውን ድምፅ በማንኳሰስ፣ በጥቃቱ ላይ ሕጋዊና ተገቢነት ያለው አስመስሎ ለማቅረብ የሚተገበር አደገኛ የሚዲያ ዘመቻ ነው። በዚህም ምክንያት እውነተኛዎቹ ሰለባዎች ከደረሰባቸው ሁለንተናዊ መከራ በተጨማሪ፣ በዓለም ፊት ጥፋተኛ ተደርገው እንዲታዩ በመደረጉ ሁለተኛ ዙር የስነ-ልቦና እና የማንነት ጥቃት የማመቻቸት ሂደት ነው።

«ስለኦርቶዶክ ዝም አንልም!»
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸

በእርግጥ እንደ ሕዝበ-ሙስሊሙ ሁሉ፣ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የጥቃት ሰለባ መሆናቸው የማይካድ ሀቅ ነው። በዚህም ምክንያት ድምፃቸውን ቢያሰሙ፣ ፍትህ ቢጠይቁና ለእምነት ወገናቸው አጋርነታቸውን ቢገልጹ ተፈጥሯዊና ተገቢ መብታቸው ነው። ሆኖም ግን፣ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን መብትና ማንነት ለማስከበር የሚደረገው የፍትህ ፍለጋ ሂደት፤ ማህበረሰቡን ለማደራጀትና ለማሰባሰብ ሲባል ብቻ፣ በክስተቶቹ ውስጥ ምንም ዓይነት ሚና የሌላቸውን ሙስሊሞች ዋና ኢላማ ባደረገ መልኩ ማቅረብና ትግሉ እንዲጓዝ መጣር ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ከጥቃቱ የከፋ ሌላ የበደል ተግባር ነው።

እንበልና በተፈጸሙት የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ጥቃቶች ጀርባ ሙስሊም የሆኑ ግለሰቦች ተሳትፈው ቢገኝ እንኳ፣ ተጠያቂነቱ ሕግን መሠረት ባደረገ መልኩ በግለሰቦቹ ላይ ብቻ ሊያርፍ ይገባል እንጂ፣ በጉዳዩ ላይ አንዳች እውቅናም ሆነ ተሳትፎ የሌለውን በሚሊዮኖች የሚቆጠርን አጠቃላይ የሙስሊም ማህበረሰብ በሚያካትት መልኩ በጥላቻ አጉልቶና ለጥጦ ማቅረብ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው።

የጽሑፉ ዓላማ፣ መነሻዎችና የማስረጃ ምንጮች
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

ይህ ጽሑፍ ከጥቃቶቹ ዘርፎች አንዱ የሆነውን የኢማሞች ግድያ ለናሙናነት ብቻ በማንሳት፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን መከራና የትዕግስት ልክ በተግባር ለማሳየት ይሞክራል። በተመሳሳይ መልኩ፣ እኔ በየካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ል. ከእስር ቤት ከተፈታሁ ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ብቻ ያስተናገድናቸውን የመስጂዶች ቃጠሎና መፍረስ፣ የአማንያን ጥቃትና ግድያ፣ በየስድስት ወሩ የሚለኮሰውን የሙስሊም ተማሪዎች መከራ ወዘተ እያልን በየዘርፉ የሆነውንና እየሆነብን ያለውን ብናነሳ፤ ከዚህ ጽሑፍ በብዙ እጥፍ የሚበልጡ ዘለግ ያሉ በርካታ ጽሑፎች ወይም መጻሕፍት ይወጣቸዋል።

በእርግጥ እንደ ማህበረሰብ የታገስነው ጨለምተኛ ስላልሆንንና ሀገሪቱ ያለችበትን ፈታኝ ሁኔታ ከመረዳት በመነጨ እንጂ፣ በማንኛውም አጀንዳ ዙሪያ ተደራጅተው ከሚታገሉት ሁሉ የላቁ በርካታ ማታገያ አጀንዳዎችም ሆነ የትግል ልምድ አጥተን አይደለም።

ሆኖም ይህንን ሁኔታ በጥልቀት እያወቁና ራሳቸው የብዙዎቹ ጥቃቶች ጠንሳሾች ሆነው ሳለ፣ «ወሃቢያ» እና «ስልጤ» በሚሉ የፍረጃ ታፔላዎች «የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ማህበረሰብ፣ የችግሮቹና የጥቃቶቹ ምንጭ ሁሉ ሙስሊሞች ናቸው» የሚል እምነትና ምስል ለመፍጠር እየሄዱበት ያለውን ርቀት ስናይ፤ የጸረ-ሙስሊም ዘመቻ አድራጊዎች እውነትን ከመቅበር ጀምሮ እስከ ተገላቢጦሽ ፍረጃ ድረስ ምን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ ግልጽ ሆኖ ይታያል።

ከ2010 ጀምሮ ለማሳየት የተሞከረው ጥቃቶቹ የግድ አሁን በስልጣን ላይ ካለው መንግስት ጋር ስለሚያያዝ ሳይሆን እኔ አሁን ባለኝ የፌስቡክ ገጼ መጻፍ ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ በቀጥታ ያወቅናቸውና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድምጽ ለመሆንም ሆነ ለማገዝ ጥረት ያደረግንባቸው ስለሆነና በቂ መረጃዎች ስላሉን ጭምር።

በተጨማሪም ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ስነሳ ስህተት እንዳልሰራ የራሴን የቀድሞ የፌስቡክ ጽሁፎችን፥ የሃሩን ሚዲያ ዘገባዎችን፥ የመጅሊስ መግለጫዎችን ፥ የዩቲዩብ ቪዲዮዎችንና የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶችን ዳግም ተመልክቻለሁ።

እነዚህ ንጹሐን የሃይማኖት አባቶች ናሕይወታቸውን ያጡት በወቅቱ እንደተዘገበው በጽንፈኛ የፋኖ ታጣቂዎች፣ በትግራይ ኃይሎች (ሕወሓት)፥ በኦነግ ሸኔ፥ በኦሮሚያ ፖሊስ፥ በአማራ ክልል ልዩ ኃይል፥ ወዘተ በተፈጸሙ ዘግናኝ ጥቃቶች፣ የጅምላ ድብደባዎችና የአፈና ድርጊቶች ነው።

ጥቃቶቹ የተፈጸሙት መስጂዶች ውስጥ፣ በመኖሪያ ቤቶቻቸው ኸልዋ፣ በአምቡላንስ ጉዞ ላይ ወይም ከሰላት መልስ ወደ ቤታቸው ሲያቀኑ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ድርጊቶች ከታቀደ የጥላቻ ዘመቻ ዉጤት ናቸው።

ይህ ጽሑፍ ከጥላቻው ዘመቻ መፋፋም በኋላ በዚህ ሳምንት የተገደሉትን ሁለት ደረሶችን ጨምሮ የ28 ኢማሞችን፥ ሼኮችን፥ኡስታዞችንና የዑለሞነን ግድያ የሚያትት ነው።

ጽሑፉ አልበዛምን?
🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ይህ ባለ 8 ገጽ ጽሑፍ በሁለት ክፍል ተቀረበ፤ ከ2010 ዓ.ል. ጀምሮ እያወቅናቸው፣ እዚሁ የፌስቡክ ገጻችን ላይ ስለ እነርሱ እየጻፍንና «ፍትህ!» እያልን የጮህንላቸውን፣ ነገር ግን ተራ በተራ ያጣናቸውንና እስካሁንም ፍትህ ያጡትን ኢማሞች፣ ዓሊሞች፣ ኡስታዞች፣ ዳኢዎችና ደረሶች በየዓመቱ የደረሰባቸውን ጥቃትና ግድያ ከነቀኑና ከነቦታው በዝርዝር የሚያብራራ ነው።

እዚህ ላይ የተጠቀሱት በሙሉ እያንዳንዳችን በማህበራዊ ሚዲያችን የጮህንላቸው፣ እንደ ‘ሃሩን ሚዲያ’ ያሉ የሙስሊሙ ባለውለታ ሚዲያዎች ሳይሰለቹና ዋጋ ከፍለው የዘገቡልን፣ እንዲሁም የእያንዳንዳቸው ምስልና ቪዲዮ ዛሬም ድረስ በዩቲዩብ (YouTube) ላይ የሚገኝና ተመልሶ ማመሳከር የሚቻልባቸው እውነታዎች ናቸው።

ከፊሎቹ ደግሞ የፌዴራልና የክልል መጅሊሶች በይፋ መግለጫ ያወጡባቸው ክስተቶች ናቸው።
ይህንን ሁሉ ለመገንዘብና ለማንበብ ሞራሉ ከሌለህ፤ ስለ ዲኔ፣ ስለ ኢማሜ፣ ስለ ዓሊሜና ስለ ሙስሊሙ መብት የመቆርቆር መብት የለህም! ምክንያቱም አንተ በዚህ በተደራጀ መልኩ ቀስ በቀስ እየተገዘገዝክ ለመጠቃት ራስህን አመቻችተህ የተኛህ ነህና።

ስለዚህ፦ አንብብ፤ ለሌሎች አጋራ፤ አስተያየትህንም ስጥበት! በአንተ አካባቢ ተገድለው በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያልተካተቱ ኢማሞችና ዓሊሞች ካሉ በአስተያየት መስጫው (Comment section) ላይ አካትታቸው። እንዲሁም በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስማቸው ተነስቶ ፎቶግራፋቸው ያልተካተተላቸው ሰማዕታት ካሉ ፎቶግራፋቸውን ከሥር ለጥፍ።
ነቃ በል! መልካም ንባብ።

በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2010 ዓመተ ልደት
📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶

1ኛ) ኡስታዝ ጣሂር አወል፦ ሳጃ ከተማ - ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ል.
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

በወቅቱ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል በነበረው የየም ልዩ ወረዳ፣ ሳጃ ከተማ ውስጥ ለመስጂድና ለመድረሳ መገንቢያ የሚሆን ቦታ መጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ.ል. በሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት በይፋ ተሰጥቶ መሠረት ተጥሎበት ነበር።

ሆኖም የነዋሪውን መብት የረገጡት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ይሁን አሰፋ፣ በሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ል. «መድረሳው ሕገ-ወጥ ነው፤ መቼም ሊከፈት አይችልም» በማለት ለመድረሳውና ለመስጂዱ የተሰጠውን ይዞታ ቆርጠው ለግለሰቦች ለማከፋፈል ተነሱ፤ በሕዝቡ ላይም ዛቱ። ይህንን ተከትሎ ማህበረሰቡ መብቱን ለማስከበር ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ አደረገ። በዚህ ወቅት ፖሊስ በሰላማዊው ሕዝብ ላይ ድብደባና ተኩስ በመክፈቱ፣ ኡስታዝ ጣሂር አወልን ጨምሮ በርካታ አማኞች ተገድለዋል፤ ሌሎች በርካቶችም ቆስለዋል።

ከግድያው በኋላ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ይሁን አሰፋ ተጠያቂነትን ለማምለጥ፤ «ማንም ፖሊስ ሰውን አልገደለም፤ የሞተው ልጅ (ኡስታዝ ጣሂር) በድንጋይ ተደብድቦ ነው የሞተው» በማለት በሕዝብ ፊት የሐሰት ክህደት ሰነዘሩ። የወንጀል አሻራቸውን ለመቀየርና እውነታውን ለማስቀልበስም፣ የተፈጠረውን ግጭት በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል እንደተደረገ አስመስለው ለክልሉ መንግሥት የሐሰት ሪፖርት አቀረቡ።

የኡስታዝ ጣሂርን መገደል ተከትሎ የተነሳውን ሕዝባዊ ቁጣ ለመቆጣጠር ከወልቂጤ ከተማ የደረሰው ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል ከተማዋን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን፤ በርካታ ንጹሐን ሙስሊሞችን በጅምላ እየለቀሙ ‘ፎፋ’ ወደተባለችው ከተማ በመውሰድ አሰቃቂ እስራት፣ እገታና እንግልት ፈጽመውባቸዋል።

2011 ዓመተ ልደት
💢💢💢💢💢💢

2ኛ) ሼኽ አህመድ አብዱል፦ ጅግጅጋ -ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ል.
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ውስጥ፣ ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ል. በድንገት ባገረሸው መጠነ-ሰፊ ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ፤ ታዋቂው የሃይማኖት አባት ሼኽ አህመድ አብዱል በጸጥታ ኃይሎች በተከፈተ አሰቃቂ የተኩስ እርምጃ ሕይወታቸውን በግፍ አጥተዋል።

ግጭቱ ሊቀሰቀስ የቻለው በከተማዋ ቀበሌ 04 ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በቁጥጥር ሥር ውለው በታሰሩ ወጣቶች ምክንያት በተነሳ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲሆን፤ በዕለቱ የጸጥታ ኃይሎች ሁኔታውን ለመቆጣጠር በከፈቱት በራሪ ጥይት ሼኽ አህመድ አብዱል እና ሌላ ሰላማዊ ግለሰቦች ተመተው ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጸመው፣ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ከሥልጣን መነሳት ማግስት በክልሉ ተከስቶ በነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ሽግግር፣ የኃይል ክፍተትና አጠቃላይ የጸጥታ መቃወስ ወቅት ነበር።

በበጎ ተግባራቸው ትልቅ ዕውቅናና ተሰሚነት የነበራቸው የእኝህ ታላቅ ሼኽ በሁከት ውስጥ መገደል በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘን የፈጠረ ሲሆን፤ ግድያውን በተመለከተም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እና የተለያዩ የሀገር ውስጥ የዜና አውታሮች ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥተውበታል።

2012 ዓመተ ልደት
⭕⭕⭕⭕⭕⭕

3ኛ) ኡስታዝ ሐምዛ፦ አዲስ አበባ -ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ል.
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

በወቅቱ በጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ል. አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን መርከዝ የዲን ተማሪ የሆኑ አምስት ደረሶች፤ የዶክተር ጄይላንን ደርስ (ሃይማኖታዊ ትምህርት) ለመካፈል ወደ አየር ጤና አቅንተው ነበር። ትምህርታቸውን አጠናቀው በእግር ሲመለሱም፣ በጀሞ መስታወት ፋብሪካ ‘ቻይና ካምፕ ማርያም ቤተክርስቲያን’ አካባቢ ዘግናኝ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ወጣቶቹ በመንገድ ላይ እያለፉ በኦሮምኛ ቋንቋ በመነጋገራቸው ብቻ፣ በዚያ አካባቢ የነበሩ ከ50 በላይ የሚሆኑ የጋሞ እንደሆኑ በንግግራቸው የተገመቱ ወጣቶች በጋራ ከበው በዱላና በተለያዩ መሣሪያዎች በጭካኔ ደብድበዋቸዋል።

በዚህ የጅምላ ድብደባ ምክንያት ከተማሪዎቹ መካከል ኡስታዝ ሐምዛ ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ አስክሬኑም በክብር ተሸኝቶ ወደ ትውልድ ስፍራው ወደ ጅማ ተልኳል።

በወቅቱ ከሰማዕቱ ኡስታዝ ሐምዛ ጋር የነበሩት አራት ወንድሞች ማለትም፦ አብዱልከሪም፣ አሚን ሷፊይ፣ ኢብራሂም ሲራጅ እና ኡስታዝ ሁሴን ክፉኛ ቆስለው በሕክምና ላይ ቆይተዋል። በወቅቱ በጉዳዩ ላይ ሃሩን ሚዱያና ራዲዪ ነጋሺን ጨምሮ ሙስሊም አክቲቪስቶች ዘገባ ሰርተው ነበር።

4ኛ) ሼኽ ኡመር ሱለይማን፦ አሳሳ ከተማ -ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ል.
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አሳሳ ከተማ፣ ሼኽ ኡመር ሱለይማን የተባሉ ኢማም በነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ል. የአስር ሰላት አሰግደው ወደ ቤታቸው እንዳቀኑ፤ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አካላት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ በተከፈተ የጥይት እሩምታ ከነአራስ ባለቤታቸውና ከሦስት ወር ሕጻን ልጃቸው ጋር በግፍ ተገደሉ።

በወቅቱ የኢማሙ መኖሪያ ቤት ቆርቆሮ በ28 ጥይቶች ተበሳስቶ ተገኝቷል። በስፍራው የነበሩት ሼኽ ቃሲም አብዱረሺድ የተባሉት ዓሊም ደግሞ እግራቸውን ተመተው ቆስለዋል።

በያኔው የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዝዳንትና በአሁኑ የፌዴራል መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም የተመራና ዶ/ር ጄይላን ከድር፣ ሼኽ ሱልጣን ሐጂ አማን እንዲሁም የመጅሊስ የቦርድ አባላት የተካተቱበት ልዑክ በነሐሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ል. ወደ ስፍራው አቅንቷል። ልዑኩ የኢማሙን ቤተሰቦች ድንገተኛ ለቅሶ ከደረሰ በኋላ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማናገር ጥቃቱን የፈጸሙት ስምንት የክልሉ ፖሊሶች መሆናቸውን በቦታው አረጋግጧል።

የልዑካን ቡድኑ ከስፍራው ሲመለስም በጉዳዩ ላይ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ በወቅቱ ስለ ግድያው የሚያጣራ አካል ተቋቁሞ እንደሚመረመር ቢገለጽም፣ ጉዳዩ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። እኔም ይህንን ዘገንን ክስተት በወቅቱ በዚሁ የፌስቡክ ገጼ ላይ ለጥፌው ነበር። ስለ ጉዳዩ ‘ሃሩን ቲዩብ’ የልዑካኑን ቡድንና የሟች ቤተሰቦችን ጭምር ቃለ-መጠይቅ አድርጎ የሠራቸው እውነታውን የሚያጋልጡ ቪዲዮዎች ዛሬም ድረስ በዩቲዩብ (YouTube) ላይ ይገኛሉ።

5ኛ) ሸይኽ አብዱላሂ ከቢራ ፦ ሀረርጌ በዴሳ-ነሐሴ 16 ቀን 2012
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በደሳ ከተማ የተቅዋ መስጂድ ኢማም የነበሩት ሸይኽ አብዱላሂ ካቢራ ነሐሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ል አብዱልሀሚድ በተባለ የ10 ዓመት ታዳጊ ቀብር ሲመለሱ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትተው ተገደለዋል። በወቅቱ አብሯቸው የነበረው ቱራ መሐመድ የተባለ ወጣትም ቆስሎ ነበር።

በወቅቱ በነሐሴ 18 ቀን 2012 የኦሮሚያ መጅሊስ በሰጠው መግለጫ ግድያውን አውግዞ ጉዳዩ እንዲጣራና ገዳዮቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቆ እኔም በዚሁ የፌስቡክ ገጼ ላይ አጋርቼው ነበር።ዜናውን ሃሩን ቲዩብ ዘግቦት የነበር ሲሆን አሁንም ቪዲዮውም በዩቲዩብ ላይ ይገኛል።እኔም በጊዜው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለሆኑት ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ በመደወል ስለጉዳዩ አናግሬያቸው ነበር።"ጉዳዩን አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን" የሚል ምላሽ ሰጥተውኝ ነበር።ይህም የዉሃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

6ኛ) ኡስታዝ አብዱልከሪም አሚን፦ አሳሳ ከተማ-12/12/2012
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

ኡስታዝ አብዱልከሪም አሚን የተገደለው በአሳሳ ከተማ በነሐሴ 12 ቀን 2012 ነበር። በግድያው የተፈጸመው በቤታቸው ውስጥ ከነባለቤታቸውና አራስ ልጃቸው ከተገደሉት ኢማም ሼህ ዑመር ሱለይማን ጠዊል በተጨማሪ የአስር ሰላት አሰግደው ሲወጡ መስጅዳቸው በራፍ ላይ በወታደሮች በጥይት የተመቱት ሼህ ቃሲም ረሻድ የተሰኙት የጃሚዓልከቢር ምክትል ኢማም በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በጥይት ሲመቱ እርሳቸውን ከወደቁበት ለማንሳት በሞከረበት ጊዜ በርሰ ላይ በተከፈተበት የተኩስ እሩምታ ነበር።

በጊዜው የሃሩን ሚዲያ እንደዘገበውና የኦሮሚያ መጅሊስ እንዳረጋገጠው ኡስታዝ አብዱልከሪም ወዲያው ሕይወቱ ሲያልፍ ሼህ ቃሲም ረሻድ በሕክምና ሲረዱ ነበር።ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ስነሳ ወደ አሳሳ በመደወል እንዳረጋገጥኩት ሼህ ቃሲም ረሻድ ድነው በህይወት ይገኛሉ።

2013 ዓመተ ልደት
🔴🔴🔴🔴🔴🔴

7ኛ) ኢማም ሸህ ሰዒድ ፦ ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ሹቢ ቀበሌ-ጥቅምት 14 ቀን 2013
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ሹቢ ቀበሌ ውስጥ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ል.ምሽት "ማንነታቸው ባልታወቀ" በተባሉ ታጣቂዎች በድንገት በተከፈተ የተኩስ እሩምታ የመስጂድ ኢማም የነበሩት ሸህ ሰዒድ በመኖሪያ ቤታቸው ኸልዋ ውስጥ ሳሉ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ከርሳቸው ጋር ነፍሰጡር ባለቤታቸው ወ/ሮ ፉጡሬም በስለት አንገቷ ታርዶ በልቧ ተደፍታ ሞታ ተገኘች።ከነርሱ በተጨማሪም አንድ ህጻንን ጨምሮ 12 ንጹሃን አርሶ አደሮች በየቤታቸው ባሉበት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

8ኛ) ደረሳ ሰዒድ ኢብራሂም ፦ ወረዳ ጃራገዶ ከተማ - ጥር 16 ቀን 2013
⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ምዕራብ እስቴ (አዳቤት) ወረዳ ጃራገዶ ከተማ አጠገብ፣ ከጦላይ ተነስቶ ከ1000 ኪሎ ሜትር በላይ በስደት የተጓዘውና ዕድሜው ከ15 ዓመት የማይበልጠው ታዳጊ ሙሳፊር ደረሳ ሰዒድ ኢብራሂም ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ልበደረሰበት አሰቃቂ የጅምላ ድብደባ ሕይወቱ አልፏል።

ታዳጊውና ጓደኞቹ መንገድ ላይ በሰዎች ታፍነው ወደ አቅራቢያ ቤተ-ክርስቲያን እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ በተፈጸመባቸው አረመኔያዊ ድብደባ ሰዒድ ወዲያውኑ ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ሁለተኛው ደረሳ በከባድ ጉዳት ሆስፒታል ገብቷል፤ ሌሎቹ 15 ደረሳዎችም ከፍተኛ ድብደባ አስተናግደዋል። ሃሩን ሚዲያ በጊዜው እንደዘገበው ይህንን ግድያ ተከትሎ በጥሩንባ ጭምር ሰዎችን በመቀስቀስ በንጹሐን ሙስሊሞች መኖሪያ ቤቶች፣ መስጂዶችና የንግድ ሱቆች ላይ መጠነ-ሰፊ ቃጠሎና ዘረፋ ተፈጽሟል።

የሟቹ ደረሳ አስክሬን ወደ ጅማ ዞን ጦላይ ወረዳ ወደ ቤተሰቡ ተወስዶ ተቀብሯል።ሃሩን ሚዲያ የቀብር ስነስርዓቱን ከመዘገብ በተጨማሪ፣
ቤተሰቦቹን ቃለመጠይቅ አድርጓል።ገንዘብ በማሰባሰብም እንዲረዱ አድርጓል።

9ኛ) ሼህ አሊዩ መሀመድ አህመድ ፦ አጣዬ ከተማ- መጋቢት 10 ቀን 2013
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

በአጣዬ ከተማ የአንሷር መስጂድ ኢማም የነበሩት ሼህ አሊዩ መሀመድ አህመድ (ሌሎች ሃፊዝ ሼህ ዘይኑ በማለጥ የጠቀሱም አሉ) እለተ አርብ መጋቢት 10 ቀን 2013 ከምሽቱ በ2፡00 ላይ የኢሻ ሰላትን አሰግደው ከአራት ደረሶቻቸው ጋር ወደ ቤት በመመለስ ላይ ሳሉ በአማራ ክልል ልዩ ኃይል ተገደሉ። ይህ ግድያ አሰቃቂ ድርጊት በአካባቢው ለተቀሰቀሰው መጠነ-ሰፊ ቀውስ ዋነኛ መነሻ ሆኗል።

የግድያውን ዜና ተከትሎ የኢማሙን አስክሬን ለማንሳት የሞከሩ የከተማው ነዋሪዎች እና ወደ ስፍራው የተሰባሰቡ የገጠር የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ተኩስ መክፈታቸው ግጭቱን ይበልጥ አባባሰው። ሂዩማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) በ2022 ዓለም አቀፍ ሪፖርቱ ላይ እንዳረጋገጠው፣ የጸጥታ አካላቱ በህዝቡ ላይ የወሰዱት የኃይል እርምጃ ውጥረቱን ወደ ታጠቀ የእርስ በርስ ጥቃት የለወጠው ሲሆን፣ ለቀናት በቀጠለው በዚህ አውዳሚ ግጭት ከተሞችና መንደሮች ወድመዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል፣ እንዲሁም ከ200,000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ሆኖም ይህ ሁሉ ጥፋት የደረሰ ቢሆንም፣ በወቅቱ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው የተዛባ ትርክት እውነተኛውን የግጭት መነሻ በመደብቅ፣ የሟቹን ኢማም ማንነት «አንድ ግለሰብ» በሚል በመደበቅ ጥቃቱ ሙሉ በሙሉ በ"ኦነግ ሸኔ" እንደተፈጸመ አስመስሎ በማቅረብ ሀቁን ለማድበስበስ የሞከረ ነበር። ሆኖም ግጭቱን ለማረጋጋት መከላከያ ከገባ በኋላ ጄነራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ መነሻው የኢማም መገደል መሆኑን በመግለጫቸው ላይ አንስተዋል።

10ኛ) ሼህ ኡመር ሀጂ ሀሰን፦ ሸዋ ሮቢት- መጋቢት 12 ቀን 2013
📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕

ሼህ ኡመር ሀጂ ሀሰን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጋንጋሃ ቀበሌ በተባለ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ የ40 ዓመት እድሜ ላይ ይገኙ የነበሩ ዓሊም ሲሆኑ በመጋቢት 12 ቀን 2013 በቀይ መስቀል አምቡላንስ በመጓዝ ላይ እያሉ በሸዋ ሮቢት ከተማ ውስጥ በአማራ ልዩ ሃይል አባላት እና የፋኖ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ከሌሎች ታካሚዎች ጋር በጥይትና በስለት ተደብድበው ተገድለዋል።

ስለጉዳዩ «ዘ ሂዩማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ሆርን ኦፍ አፍሪካ» በአፕሪል 6 ቀን 2021 «Ethiopia: Appeal for Urgent Independent Investigation into Shewa Robit Massacre of March 21, 2021!» በሚል ባወጣው መግለጫ ላይ የሼህ ኡመርን ሞት ጠቅሷል።

11ኛ) ሼይኽ አሊይ ሀሰን፦በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰንበቴ ከተማ-ሚያዚያ 9 ቀን 2013
🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የቢላል መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼይኽ አሊይ ሀሰን ሚያዚያ 9 ቀን 2013 መገደላቸውን የሃሩን ሚዲያ በአፕሪል 18 ቀን 2021 እንዲህ በማለት ዘግቦ ነበር፦ «በሰንበቴ ከተማ የቢላል መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼይኽ አሊይ ሀሰን በትላንትናው ዕለት መገደላቸውን የሀሩን ምንጮች አሳውቀውናል። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን»። የሃሩን ሚዲያ የፌስቡክ ዘገባ በማንና እንዴት እንደተገደሉ የማያብራራ ሲሆን በኦሮምኛ ስለጉዳዩ የጻፉ ጥቂቶች ግን በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸው ጠቅሰው ነበር።

ሌሎች የአይን እማኞች ደግሞ ገዳዮቹ የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ የልዩ ሃይል አባላት እንደሆኑ ገልጸው ኢማሙ በረመዳን ወር የመግሪብ ሶላትን አሰግደው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ፣ በመስጂዱ በር ላይ ህይወታቸው መቀጠፊን ጽፈዋል።

ሃሩን ሚዲያም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በለጠፈው ተጨማሪ ጽሑፍ «ኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ቤተ-ክርስቲያናት ፣የግለሰቦች ቤቶች ፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቃት እንዳይደርስባቸው በሚል ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ስለመስጅድ ግን ምንም ያለው ነገር የለም። በነበረው ግጭት መስጅድ እንደተቃጠለ ኢማም እንደተገደለ እንኳን እየታወቀ ሙስሊሙ ላይ የሚደርስ በደል ግን እምብዛም ትኩረት ተሰጥቶት በመንግስት ደረጃ አልተገለፀም።

የመስጅድ ኢማምን መገደል ስንዘግብ የተቃወማችሁ ሙስሊሞች መልዕክቱ ከማንም በላይ ለናንተ ነው። ቢያንስ ግራ በሚያጋባው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምንም ማለት ባንችል ከበደሎች መሀል የማናቸውም የሙስሊሞች በደል ተሸሽጎ እንዳይቀር በማሰብ ነው የደረሰንን የተጣራ መረጃ መሠረት አድርገን ዘገባውን የሰራነው።

በየትኛውም አካባቢ የሚደርሱ የሙስሊሙ በደሎች አሁንም ወደፊትም ያሳስቡናል፤ እንደ ሚዲያ ዋነኛ የትኩረት አጀንዳዎቻችንም ናቸው። በዚህ ስራ ላይ ሁሉንም አካል ማስደሰት አይቻልም። የደረሰንን ከዚያም ያረጋገጥነውን መረጃ ግን ወደናንተው እናደርሳለን።»

12ኛ) ሼህ አዱላይ፦አፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ- 2013 መጨረሻ
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው የ80 ዓመት አዛውንት የነበሩት ሼህ አዱላይ የተገደሉት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት በ2013 መጨረሻ ወይም 2014 መግቢያ ላይ በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ ጎቢዶራ ከተማ ውስጥ በነበሩ የትግራይ ኃይሎች(ሕወሃት) ታጣቂዎች መስጂድ ውስጥ እንዳሉ ነበር በጥይት የተገደሉት።

(Report on Violations of Human Rights and International Humanitarian Law in Afar and Amhara Regions of Ethiopia)

13ኛ) ሼህ ሰማን አደም፦ ሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ-ከሐምሌ 17 ቀን 2013 በኋላ
❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗

ከሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ል. ጀምሮ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የምትገኘውን የአደርቃይ ወረዳን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር።

ሕወሓት በአካባቢው ላይ በቆዩባቸው ወራት ውስጥ በንጹሃን ዜጎች ላይ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና የታገቱ ግድያዎችን ፈጽመዋል። በዚህ የጥፋት ዘመቻ ከተገደሉ በርካታ ንጹሃን መካከል ዕድሜያቸው 54 ዓመት የነበሩት ታዋቂው የሃይማኖት አባት ሼህ ሰማን አደም አንዱ ነበሩ።

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ (AAA) ባጠናቀረው ሪፖርት መሠረት፥ ሼህ ሰማን አደም በሕወሓት ታጣቂዎች አማካኝነት በግፍ እንዲገደሉ የተደረገው በሃውዛ ቀበሌ ውስጥ ነበር።

ይቀጥላል...

Photos from Etika Teferi's post 15/06/2026
28/02/2026

Arjooma isaatiin ,
Nu badhaasee Ne'eemaa..
Miidhagsee bareechee,
Kan nu godhe nama..
Rabbi keenya guddaa ,
Hundaan qulqullaa'e
Aangoon gooftummaasaa,
Kan hundaa olta'e...

Warri isatti amannu..
Warri isa sodaannu,
warri isaaf owwaannu,
warri isaaf sagadnu
Tika isaatu nu eega ,
Yoomuu badnee hin badnu..
Yoo hin qabaannes qabna,
Isa waamnee hin dhabnu..

Anis isan qaba ,
Hirkoo fi gaachana kanan ittiin kooruu..
Rabbi keenya Jabaa,
Gooftaa gabrootasaa gatii malee sooru..!!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Finfinnee Oromia
Addis Ababa