MaBizplus

MaBizplus

Share

​🏦 Banking | Economy | Entrepreneurship on the Ethiopian , African & global markets.
💡 Building a digital mindset for leaders.
👇 Follow for the latest financial news and growth strategies. MaBizPlus shares quick and reliable updates on global, African, and Ethiopian finance, banking, the economy, digital finance, and investment trends.

29/06/2026

የምረቃዋ ዕለት ቤተሰብ ያልመጣላትን ተመራቂ በደስታ እንባ ያራጩት የባህርዳር ልጆች🔥

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከትናንት ወዲያ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በይፋ አስመርቋል። ከነዚህ አንዷ ይህቺ የህግ ትምህርት ቤት ምሩቅ ነች።

ምሩቋ የተመራቂዎች ቤተሰቦች ተሰባስበው በሚመጡበት ዕለት ቤተሰቦቿ አልመጡም (የአቅም ጉዳይም ሊሆን ይችላል)። በዚህም በጣም የተከፋችው ተመራቂ በዶርም ስታለቅስ ቆይታ ተጣጥባ ወደ ከተማ ታመራለች። ከአንድ ካፌም ትቀመጣለች።

በካፌ ተቀምጣ ምግብ በልታና ጠጥታ በዚያ ተክዛ ሳለች፣ ድንገት በቤቱ ያለ ሙዚቃ ወደ ሌላ ይቀየራል። "እንኳን ደስ አላችሁ" ሲል በካፌው ምን መጣ አልኩ ትላለች።

በድንገት ዞር ስትልም ታስቦ እንደተዘጋጀ 4 የባህርዳር ልጆች 'እንኳን ደስ አለሽ" የሚል ፅሁፍ ያረፈበትን ኬክ ከሻማው ጋር እንድትቆርሰው ጋብዘው በእንባ አራጭተዋታል።

ይህንን ያልጠበቀችው ተማሪ በብዙ እንባ ደስታዋን የገለፀች ሲሆን 'እስከ ዛሬ ብቻዬን ነበርኩ። የቅርብ ጓደኛ እንኳን የለኝም። የሚከፋኝም አይመስለኝም ነበር። ነገርግን በእለቱ ከፋኝ። አለቀስኩ። ስወጣም ይህ ሆነ ስትል" ደስታዋን ገልጻለች።

29/06/2026

አባይ ባንክ አ.ማ 'ABAYB' በሚል መለያ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና ገበያ ላይ አክሲዮኖቹን በይፋ አቅርቧል። በዚህ ታሪካዊ እርምጃውም ከጥር 2025 የግብይት ጅምር ወዲህ ገበያውን የተቀላቀለ አምስተኛው ኩባንያ፣ እንዲሁም አራተኛው የግል ንግድ ባንክ ለመሆን በቅቷል።

ባንኩ ገበያውን የተቀላቀለው ከተለመደው የአዲስ አክሲዮን ሽያጭ (IPO) በተለየ መልኩ ሲሆን፣ ይህም ነባር ባለአክሲዮኖች ብቻ ድርሻቸውን በህጋዊ የግብይት ገበያው ላይ እንዲገበያዩ የሚያስችል አሰራር (Listing by introduction) ነው። ምንም እንኳን በዚህ ሂደት በአፋጣኝ አዲስ የካፒታል ማሰባሰብ ባይካሄድም፣ ይህ እርምጃ የዋጋ ትክክለኛነትን ለማወቅ፣ የተቋሙን አስተዳደራዊ ግልጽነት ለማሳደግ፣ የገበያውን የገንዘብ ዝውውር (Liquidity) ለማሻሻል እና ለቀጣይ የካፒታል ማሰባሰብ ጠንካራ መሰረት ለመጣል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ የቆየውን ክፍተት በመዝጋት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አካል ሆኖ ከተቋቋመ ወዲህ ታላላቅ የፋይናንስ ተቋማትን እየሳበ ይገኛል። እስካሁን ባለው ሂደት ወጋገን ባንክ፣ ገዳ ባንክ፣ እና የሀገሪቱ ትልቁ የግል ባንክ የሆነው አዋሽ ባንክ ገበያውን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ በግንቦት 2026 ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም ከፋይናንስ ዘርፍ ውጪ የመጀመሪያው ኩባንያ በመሆን መቀላቀሉ ይታወሳል። የባንኮቹ የገበያ ተሳትፎ አሁንም የሚቀጥል ሲሆን፣ ዳሽን፣ አቢሲንያ፣ አንበሳ እና አማራ ባንኮች የህግ ቅድመ-ዝግጅታቸውን አጠናቀው በቅርቡ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ተከታታይ እርምጃ የኢትዮጵያ ንግድ ተቋማት ለስራ ማስፋፊያ በዋናነት በባንክ ብድር ላይ ብቻ ጥገኛ ከሚሆኑበት አሰራር በመላቀቅ፣ ዘመናዊ እና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አማራጭ ወደሚያገኙበት አዲስ ምዕራፍ መሸጋገራቸውን የሚያሳይ ነው። ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያውም በ2025/26 የበጀት ዓመት መጨረሻ የተመዘገቡ ኩባንያዎችን ቁጥር ዘጠኝ ለማድረስ፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2030 ይህን ቁጥር አምሳ ለማድረስ ትልቅ ግብ ሰንቆ በፈጣን እመርታ ላይ ይገኛል።

Photos from MaBizplus's post 29/06/2026

የኮሞቦልቻ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዓለማቀፍ ዕውቅና አገኘ።
በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓረኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የተቀናጀ ሥራ አመራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ ጥራት ላይ ትኩረት በመስጠቱ በዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶች በብቃት በማለፍ የዓለም አቀፍ ሰርትፍኬት(አይኤስኦ) ማግኘቱ ተመላክቷል።

የኮሞቦልቻ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ከአካባቢ ጋር ተስማሚነት ያላቸው ተግባራትን ማከናወኑ ለዕውቅና እንዳበቃው የኮምቦልቻ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽዳት እና ውበት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደሳለኝ እጅጉ ተናግረዋል። ሌሎቹም ተቋማት የኢኮኖሚክ ዞኑን ተሞክሮ መውሰድ እና መተግበር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የኮሞቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዓለም አቀፍ ሰርትፍኬት ያገኘው በጥራት ሥራ አመራር፤ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሥራ ላይ የጤና እና ደኅንነት በፈፀማቸው ቁልፍ ተግባራት መኾኑን በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮር ፖሬሽን የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ሥራ አሥኪያጅ አህመድ ሰይድ ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ ዞኑ ሲቋቋም የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዕውቀት ሽግግር ማድረግ የተቋቋመባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው ብለዋል።

በቀጣይም በሁሉም መመዘኛ መስፈርቶች ጠንክሮ በመሥራት ከውጭ ምንዛሬ የሚገኝ ገቢን ለማሳደግ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

ዓለምአቀፍ መስፈርቶችን በብቃት በማለፍ የተገኙ ሰርትፍኬቶች የተሻለ አቅም ያላቸው እና ዓለምአቀፍ ባለሃብቶችን ለመሳብ ሚናቸው የላቀ መኾኑን አስረድተዋል።

በኢትዮጲየያ የተስማሚነት ኤጀንሲ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሚሻሞ ዋካሶ የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ያገኛቸው ሰርትፍኬቶች የሚያመርታቸውን ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ተመራጭ እንደሚያደርጉትም ተናግረዋል።

የተገኙ ወጤቶች ብዙ የተደከመባቸው መኾናቸውን አመላክተዋል።

የኮሞቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዓለምአቀፍ ሰርትፍኬቶችን አንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሠራተኞች ማበረታቻ እና ዕውቅና ተሰጥቷል።

#ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ደምስ አረጋ

Want your business to be the top-listed Media Company in Debra Markos?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Sudan Street
Debra Markos