Tesfa
28/05/2026
እውነተኛ እረፍትና እፎይታ የሚገኘው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
በሀጢያት ወይም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ደክመሀል? ኢየሱስ ወደ እኔ ና፤ እረፍት እሰጥሃለሁ ብሎ ይጠራሀል።
እርሱ የሚሰጠው እረፍት: ከሀጢዓተኝነት እና ከበድለኝነት ነፃ የሚያወጣ እረፍት፣ ከጭንቀትና ከፍርሃት ነፃ የሚያወጣ እረፍት፣ በልብ ውስጥ የተረጋጋ ሰላምና እፎይታ የሚሰጥ እረፍት፣ የዘላለም ሕይወት የሚገኝበት እውነተኛ እረፍት ነው።
ዛሬ ወደዚህ እረፍት ተጠርተሀል!
ማቴዎስ 11:28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
15/05/2026
እግዚአብሔር በሰው ህይወት ውስጥ የሚፈቅደውን ሁሉ ነገር ለበጎ ይለውጠዋል። ዛሬ የምታልፍበትን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይቀይረዋል።
አንዳንድ ጊዜ የምታልፍበት ነገር ለምን እንደሚሆን ላይገባህ ይችላል፤ ህመም፣ መዘግየት፣ ችግር ወይም ውድቀት ቢኖርም በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን እግዚአብሔር እየሠራ ነው።
እርሱ ከባድ ነገሮችን እንኳ ለመልካም ያደርጋቸዋል።
ዛሬ ያልገባህ ሁኔታ ቢኖርም ተስፋ አትቁረጥ። እግዚአብሔር ከህይወትህ አንድም ክፍል አይለይም። እርሱ እያንዳንዱን ነገር ለመልካም ፍጻሜ እያዘጋጀህ ነው።
ሮሜ 8:28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Click here to claim your Sponsored Listing.