AYM MEDIA

AYM MEDIA

Share

14/06/2026

❝ ታላቅ ባንከር ማለት ገንዘብ የሚቆጥር ብቻ ሳይሆን፣ ለደንበኞች የንግድ ስኬት እና ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የፋይናንስ መፍትሄዎችን የሚያመነጭ ባለሙያ ነው ። ❞

13/06/2026

➲ እውነቱን ለመነጋገር፣ የኢትዮጵያ ባንኮች ከፊታቸው የመጣውን ዓለም አቀፍ ውድድር እና የፖሊሲ ለውጥ ለመቋቋም በዲጂታል ባንኪንግ እና በሰው ኃይል ልማት መካከል አንዱን መርጠው ሌላውን መተው አይችሉም፤ ምክንያቱም ሁለቱ እርስ በእርስ የተሳሰሩ ናቸው።

​ነገር ግን «ቅድሚያ» የሚለውን ስንመለከት፣ ባንኮች ስትራቴጂያቸውን በሚከተለው መልኩ ቅደም-ተከተል ቢያስይዙ ውጤታማ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ።

➊ የሰው ኃይል ልማት እና የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindset Shift) ​የቱንም ያህል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ቢገዛ፣ ቴክኖሎጂውን የሚመራውና ስትራቴጂ የሚያወጣው የሰው ኃይል ነው። የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ይዘውት የሚመጡት ትልቁ ጉልበት የላቀ የባንክ አገልግሎት ባህል (Service Culture) እና የተራቀቀ የአደጋ ስጋት አስተዳደር (Risk Management) ልምድ ነው። ​ስለዚህ የሀገር ውስጥ ባንኮች መጀመሪያ እዚህ ላይ መስራት አለባቸው።

➲ ​የክህሎት ማሻሻያ (Upskilling) ሰራተኞችን ከባህላዊው "የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ እና ወረፋ ማስተናገድ" አስተሳሰብ አውጥቶ፣ ወደ ዘመናዊ የደንበኛ አያያዝ፣ የኢንቨስትመንት ባንኪንግ እና የፎሬክስ ስጋት አስተዳደር ማሸጋገር።

➲ ​የችሎታ ጥበቃ (Talent Retention)፦ የውጭ ባንኮች በከፍተኛ ደሞዝ የሀገር ውስጥ ከፍተኛ ባለሙያዎችን (Expereinced Bankers) የመውሰድ ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ፣ ባንኮች ቁልፍ ሰራተኞቻቸውን የሚያቆዩበት ማበረታቻ መቅረጽ አለባቸው።

​➋ ትርጉም ያለው የዲጂታል ባንኪንግ ሽግግር
​አሁን ባለው ሁኔታ የዲጂታል ባንኪንግ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የውጭ ባንኮች በየቦታው ቅርንጫፍ በመክፈት ሳይሆን በዲጂታል አማራጮች አማካኝነት ነው ደንበኞችን በቀላሉ ሊቀሙ የሚችሉት። ​ከመተግበሪያ (App) ባለፈ ማሰብ፦ ዲጂታል ባንኪንግ ማለት የሞባይል መተግበሪያ መኖር ብቻ አይደለም። የባንኩ የውስጥ አሰራር (Core Banking እና Back-office) ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ መሆን አለበት። ይህም የውሳኔ አሰጣጥ ፍጥነትን ይጨምራል፣ ወጪን ይቀንሳል።
​መረጃን መሠረት ያደረገ አሰራር (Data-Driven Banking)፦ ባንኮች ያላቸውን የደንበኛ መረጃ (Data) በመተንተን፣ ለተለየ ደንበኛ የተለየ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ማቅረብ መቻል አለባቸው።

​➌ ስልታዊ ውህደት (Strategic Partnership) እና የደንበኛ ታማኝነት
​ባንኮች ሁሉንም ነገር ለብቻቸው ለመስራት መሞከር የለባቸውም። ከፊንቴክ (FinTech) ድርጅቶች ጋር በመተባበር አዳዲስ የክፍያ አማራጮችን በፍጥነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

​በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ባንኮች ያላቸው ትልቁ መከላከያ ከደንበኞች ጋር የቆየ ስር የሰደደ ትስስር እና የቅርንጫፎች ተደራሽነት ነው። ይህንን ጥንካሬ በቴክኖሎጂ በማገዝ የደንበኛን ታማኝነት (Customer Loyalty) ማፅናት ይቀድማል። ​

➲ ባጭሩ ለማጠቃለል፦ ​ቴክኖሎጂው ሞተሩ ሲሆን፣ የሰው ኃይሉ ደግሞ አሽከርካሪው ነው። ሞተሩ የቱንም ያህል ቢዘምን አሽከርካሪው የውድድሩን ፍጥነት መቋቋም ካልቻለ መኪናው መሸነፉ አይቀሬ ነው። ስለዚህ ባንኮች በሰው ኃይል ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የዲጂታል ሽግግሩን የሚመራ ብቁ ማህበረሰብ መፍጠር ቀዳሚ ስራቸው ሊሆን ይገባል እላለሁ።
✔️ ስለ ባንኮቻችን የፈለጋችሁትን ሀሳብ አስተያዬት ስጡኝ በደስታ እቀበላለሁ ።

11/06/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታይትል ስፖንሰር ያደረገው የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሀገሬ ቴቪ በቀጥታ ማስተላለፍ ጀመረ።
=================
የሀገራችን የኢኮኖሚ ምሰሶ እና የዲጂታል ባንኪንግ መሪ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀውን 23ኛውን የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን በስያሜ (ታይትል) ስፖንሰርነት ለሀገራችን ስፖርት አፍቃሪዎች በቀጥታ ማስተላለፍ መጀመሩን በደስታ ያበስራል።

ከሀገሬ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የሚቀርበው ይህ የቀጥታ ስርጭት፤ ዛሬ ሰኔ 4 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት 48ኛ ፎቅ ላይ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ስቱዲዮ የቀጥታ (Live) መርሐ-ግብሩን በይፋ ተጀምሯል።

ባንካችን የዚህ ታሪካዊ የስፖርት ሁነት ብቸኛ የስያሜ ስፖንሰር በመሆን መላው የባንኩ ደንበኞች እና የኳስ አፍቃሪዎች ጨዋታዎቹን ያለምንም እንግልት በቤታቸው ሆነው እንዲከታተሉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አዘጋጅነት እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየውን ይህንን እጅግ አስደሳች የዓለም ዋንጫ ውድድር፣ ዛሬ ምሽት ከሚደረገው የሜክሲኮ እና የደቡብ አፍሪካ የመክፈቻ ጨዋታ ጀምሮ በሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ በመከታተል እንዲዝናና የሚጋብዘው ባንካችን ፣ ለማንኛውም የባንክ አገልግሎት ፍላጎትዎ የባንካችንን ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ እንጋብዛለን።

10/06/2026

✌️

09/06/2026

የምትሰራበትን ተቋም ሶሻል ሚዲያ 𝙛𝙤𝙡𝙡𝙤𝙬 𝙡𝙞𝙠𝙚 እና 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 ማድረግ ማሽቃበጥ የሚመስላቸው ሰራተኞች ግን የሆነ ነገራቸው ትክክል አይደሉም እመኑኝ ለግላቸው ቢዝነስም አይሆኑም 𝙥𝙚𝙧𝙞𝙤𝙙 ‼️ I am proud to share every updated notifications from Commercial Bank of Ethiopia ✌️

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa