Ethio Times
14/08/2024
የብልፅግና ፓርቲ ሕዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ "የብሔራዊነት ትርክት ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል ለፌደራል ተቋማት የኮሚኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ ፡፡
በስልጠና መድረኩ የማጠቃለያና ሀሳብና የስራ መመሪያ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት አስተባባሪና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ለተጀመረው የአገር ግንባታ ሒደት በጠንካራ ኮሚኬሽን መደገፍ በማስፈለጉ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡
ትርክት በአግባቡ በመጠቀም የብልጽግና ማማ ላይ የደረሱ አገሮች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ደግሞ በተዛባ ትርክት ምክንያት ከፈረሱ አገራት ማየት እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡
ብዙሃነትን ማስተናገድ የሚችል ጠንካራ ሀገረመንግስትን ለመገንባት ሚዲያ ትልቁን ድርሻ የሚወጣ በመሆኑም አሰባሳቢ ትርክቶችን ዕለታዊ አጀንዳ በማድረግ የአስተሳሰብና ተሻጋሪ የትውልድ ቀረጻ ላይ ትኩረት መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡
ፓርቲያች ካስቀመጠው ራዕይ እና ከህዝባችን አዳጊ ፍላጎት አንፃር ካስመዘገበው አመርቂ ስኬት ከፍ ያለ ድል ማስመዝገብ እንዲቻል የአመለካከትና የተግባር አንድነታችንን ማጎልበት ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአኗኗራችን የሚገለጡ የመተባበርና አብሮነት እሴቶችቻችንን በማጉላት ለሕብረ ብሄራዊ ትርክት ግንባታ አቅም አድርጎ መጠቀም አፍሪካዊ እንዲሁም ዓለማቀፋዊ የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች አገርን እውን ማድረግ እንደሚቻል ተጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብዙሃ ማንነት ያላት አገር መሆኗን የማይካድ ሀቅ መሆኑን ያነሱት ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ከሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች በተጨማሪም በተቋም ደረጃ አሰባሳቢ ትርክትን በቃል ከማቀንቀን ባለፈ በየለትዕለት ስራዎች በተግባር የተገለጠ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡
መንግስት ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመከላከል እየሰራ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን የኮሚኬሽን ባለሙያዎች ሰፊ ስራዎች መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
በሀገራችን ጽንፍና ጽንፍ ያሉ የፍፁማዊ አንድነት እና የፍፁማዊ ልዩነት ትርክቶች ዋጋ እያስከፈሉ በመሆናቸው የብሔራዊነት ገዥ ትርክት በሕዝብ ዘንድ እንዲሰርጽ ማድረግ የኮሚኬሽን ባለሙያዎች አበርክቶ ከፍ ያሉ መሆኑን በመረዳት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
https://t.me/GonderTimes
Click here to claim your Sponsored Listing.