LuLu Holistic Development

LuLu Holistic Development

Share

My services would be provided both in face to face or in video conferencing (through Google Meet or Zoom) in accordance with the preference and convenience of my clients.

31/03/2022

እኔ በሚል የምንጠራው የማንነታችን ክፍል በዋናነት አራት ነገሮችን ያመለክታል፦ አካላችንን ፣ ስሜታችንን ፣ አእምሯችንን እና መንፈሳዊ ማንነታችንን።
በእያንዳንዳቸው ላይ ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎችን በቀጣዮቹ ሳምንታት የማቀርብላችሁ ሲሆን ለዛሬ ግን ጠቅለል ያለ አጭር ማብራሪያ በሁሉም ላይ እሰጣለሁ።
አካላችን እና ስሜታችን ላይ የሚፈጠሩብን የእኔነት ስሜቶች በአብዛኛው አስበን እንዲከሰቱ የምናደርጋቸው ሳይሆኑ ስሜቶቹ ሲፈጠሩ የምናስተውላቸው ናቸው። ከዚህ አኳያ ይህ ስሜት መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል ፤ ዝም ካልኩትስ ወደየት ሊያመራ ይችላል ፤ ወደምፈልገው አቅጣጫ እንዲለወጥ ምን ላድርግ ፤ ወዘተ አይነት ጥያቄዎችን ለአእምሯችን ጠይቀን በአግባቡ ማስተናገድ ይጠበቅብናል። ከዚህ በተረፈ ለምን እንዲህ አይነት አካላዊ ስሜት ተፈጠረብኝ ፣ ለምን ይሄ ስሜት ተሰማኝ በሚል የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማንም ሆነ ማብቂያ የሌለው ፍለጋ ውስጥ መግባት አይጠበቅብንም። በማህበረሰባችን ውስጥ አንዳንድ ስሜቶች ፈጽሞ ተቀባይነት የሌላቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በግልጽ በምንናገርበት ወቅት "እንዴያው ምን ስትል አሰብከው?" አይነት ውግዘት ሊገጥመን ይችላል። እንደ እውነቱ ከሆነ ለስሜታዊ ማንነት የሚሰጠው ቦታና ግምት በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ ስሜታችንን ገልጦ መናገር ይቅርና እኛው እራሳችንም እውቅና ላንሰጠው እንችላለን - ምክንያቱም ማህበረሰቡ ውጉዝ የሚያደርገው ስለሆነ። ነገር ግን የሚሰሙንን ስሜቶች መቆጣጠር የማንችል መሆናችንና ምንም አይነት ቢሆኑ ጥቅም እንጅ ጉዳት የሌላቸው መሆኑን መረዳቱ ላይ ነው። ምክንያቱም ስሜቱ ተሰማን ማለት ድርጊት ይሆናል ማለት አይደለም!
አእምሮ የምንለው የእኔነት ክፍል ዋነኛው ስራው ማሰብና የምናባዊ እይታ ሲሆን ከአካላዊና ስሜታዊ ማንነታችን በተለዬ በቁጥጥራችን ውስጥ ያለ ነው። ስለዚህ በምንፈልገውና ገንቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ በአካላዊና ስሜታዊ የማንነታችን ክፍሎች የሚመጡ አሉታዊና አፍራሽ ግፊቶችን መቋቋም እንችላለን።
በመጨረሻም መንፈሳዊ የምንለው የማንነታችን ክፍል በተለምዶ ሃይማኖት 😂ከምንለው የህይወታችን ክፍል ጋር የሚገናኝ ሳይሆን ከሶስቱ የማንነታችን ክፍሎች መስተጋብር በሚመነጭ ሁኔታ በራሳችን ላይ ያለንን እምነት ፣ እሴት (በህይወታችን የላቀ ዋጋ የምንሰጠው እሳቤ) እና የመነቃቃታችን ምክንያት ተደርጎ የሚወሰድ የማንነታችን ክፍል ነው።

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Ayat
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 03:00 - 10:30
Tuesday 03:00 - 10:30
Wednesday 03:00 - 10:30
Thursday 03:00 - 10:30
Friday 03:00 - 10:30
Saturday 03:00 - 10:30