RODAS Agency

RODAS Agency

Share

Photos from RODAS Agency's post 02/01/2023

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለታት ዓመት የሽሬ በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል

>>> "ወደ ሽሬ በረራ መጀመሩ ስንፈልገው የነበረው ሰላም ማረጋገጫ ነው - መንገደኞች

ታኅሣሥ 24/2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ በረራ መጀመሩ ስንፈልገው የነበረው ሰላም ስለመምጣቱ ማረጋገጫ ነው ሲሉ መንገደኞች ገለፁ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለታት ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረውን የሽሬ በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

የሽሬ መንገደኞች ለኢዜአ እንዳሉት፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የነበረው ግንኙነት ከሁለት ዓመታት በላይ ተቋርጦ ነበር።

ይሁን እንጂ መንግስት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ወደ ሽሬ የሚያደረገውን በረራ ዛሬ አስጀምሯል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽሬ የሚያደርገው በረራ ስንፈልገው የነበረው ሰላም ስለመምጣቱ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

አሁን በተፈጠረው ነገር ደስ ብሎናል ያሉት መንገደኞቹ፣ ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ አሁን የሰፈነው ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረውም ጠይቀዋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Addis Ababa