Tulumu Media
08/07/2026
የቤት ኪራይ ጭማሪ ይፋ ሆነ‼
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆነ፤ የውል ምዝገባ ተጀመረ‼
በአዲስ አበባ ከተማ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው የግል መኖሪያ ቤቶች የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መወሰኑን የከተማዋ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ውሳኔው የነዋሪውን የመክፈል አቅምና የወቅቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶበት የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ተከትሎም በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅሕፈት ቤቶች በይፋ መጀመሩን ቢሮው አስታውቋል
05/07/2026
ብራዚል ከ23ኛው ዓለም ዋንጫ ተሰናበተች
*****************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ብራዚል በኖርዌይ 2 ለ 1 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች። ኖርዌይም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ አልፋለች።
የኖርዌይን የማሸነፊያ ግቦች 79ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ኤርሊንግ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል። ለብራዚል ኔይማር ጁኒየር በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በጨዋታው በብራዚል በኩል ብሩኖ ጉማሬሽ 14ኛው ደቂቃ ላይ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ኖርዌይ በሩብ ፍፃሜው የሜክሲኮ እና እንግሊዝን አሸናፊ የምትገጥም ይሆናል።
04/07/2026
የጅማ ከተማ አስተዳደር 300 መኖሪያ ቤቶችን ለልማት ተነሺዎች አስረከበ
Click here to claim your Sponsored Listing.