Bini Reaction
እማማ ባልታዛር😂😂
01/11/2024
#ፓርላማ
አበባው ደሳለው (ዶ/ር) የጠየቁት ምን ነበር ?
➡ በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጹሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር፣እገታ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
➡ በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ።
➡ በአማራ ክልል ያለው ችግር አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።
➡ በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።
➡ አማራ ክልል ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው፣ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች፣ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።
➡ በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልልና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።
➡ ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞች፣አንቂዎች ለ2 ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።
➡ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ም/ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ አመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው።
➡ መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው?
➡ ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው?
➡ የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው ?
የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽ ምንድነው ?
🔵 ከኃይል ይልቅ ሰላም እጅግ በጣም አዋጭ ነው።
🔵 እኛ ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን።
🔵 ከልጅነት አንስቶ ክላሽ ተሸክመን ስለኖርን ጉዳቱ ይገባናል። ጦርነትን በወሬ ሳይሆን በተግባር እናውቀዋለንና አንፈልገውም። ብዙዎችን ቀጥፎብናል አንፈልገውም።
🔵 ህልም አለን በዚህ ሀገር የሚጨበጥ ለውጥ ለማምጣት ለዛ ሰላም ያስፈልጋል።
🔵 ' የሰላም አማራጭ አትመርጡም በግልጽ አታውጁም? ' ለተባለው በተደጋጋሚ ማወጃችንን እናተም ህዝቡም ያውቃል።
🔵 የሀገር ሽማግሌዎችን ልከን በእንብርክክ መመለሳቸውን እናተም እኛም እናውቃለን።
🔵 አሁንም ቢሆን በሰላም በኩል እርሶ (ዶ/ር አበባው) እኛንና የሚቃወሙትን ማቀራረብ ከቻሉ በሩ ክፍት ነው። የምንፈልገው ሰላም ነው። አነጋግረው ያምጧቸው።
🔵 በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር ንግግር አለ ግን ንግግር የሚያደርጉትን እና ሰላም የሚፈልጉትን ሰዎች ' እንዴት ትነጋገራለህ ከዚህ መንግስት ጋር? ' ብለው የሚወቅሱ ሰዎች አሉ። እዚህም አሉ፤ እዛም አሉ። በዚህም ምክንያት ሰላም ፈላጊዎቹ ደበቅ ይላሉ።
🔵 መጠየቅ ብቻ አይደለም ንግግርም ጀምረናል። ለቀረው እርስዎም (ዶ/ር አበባውን) ያግዙን።
🔵 የምንፈልገው ሰላም ነው። አንድ ወንድም ገለን ምን እናገኛለን ? በዚያ መንገድ ማንም እንደማያሸንፈን እናውቃለን። ምንም ! ስጋት ኖሮብን አይደለም። ግን መገዳደል ምን ፋይዳ አለው ? አይጠቅምም።
🔵 ' በ2 ወር እንቆጣጠራለን ብላችሁ ገብታችሁ ' የሚለው ምኑን እንቆጣጠራለን ክልሉን በህጋዊ መንገድ በምርጫ ያሸነፍንበት ክልል ነው። ምንድነው? ከማን ነው? የምንቆጣጠረው። በአንጻሩ ያልተሳካው " በሁለት ሳምንት ይሄን አረፋ መንግስት አባርሬ 4 ኪሎ የአባቶቼን ርዕስት እወርሳለሁ " ያለው አልተሳካለትም። እንጂ አማራ ክልል ክልላችን ነው የአማራ ህዝብ ህዝባችን ነው። ምንም የምንቆጣጠረው አብረን ነው የኖርነው አብረን ነው ያታገልነው አብረን እኖራለን። 2 ወር 3 ወር የሚል እቅድ ከኛ ሳይሆን እኛን በቀላሉ ለመገፍተር ካሰቡ ሰዎች የመጣ ነው።
🔵 የአማራ እስር፣ ጉዳት፣ ችግር የሚለው የቁጫም ችግር ነው፣ የኦሮሞም ሲጠየቅ ችግር ነው ይሄ የሰፈሩን ብቻ የሚያስብ ኃይል ሁል ጊዜ እንደዛ ነው። የራሱን ብቻ ነው የሚያየው።
🔵 አማራን ባለፉት 6 ዓመታት የኢንዱስትሪ ማዕከል አድርገናታል። የማያምን ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ባህር ዳር፣ ቡሬ ሄዶ ይቁጠር። ጨርቃ ጨርቅ፣ ሲሚንቶ፣ ማርብል፣ ግራናይት የዘይት ፋብሪካ ብዙ ብር አግዘን አማራ ክልል አቋቁመናል።
🔵 አማራ ክልል የብልጽግና መንግስት የፈጠረውን ኢንዱስትሪ በየትኛውም መንግስት አግኝቶ አያውቅም። በወሬ ስለተደባበቅ እንዳትሸወዱ።
🔵 ሁሉም ባይሟላም በመንገድ ዘርፍ ብዙ ስራ ተሰርቷል።
🔵 ባህር ዳር እኛን ሳይመርጠን በስራ ማስመስከር ስላለብን በኢትዮጵያ ሰርተን የማናቀውን ድልድይ ሰርተናል፣ መንገድ እየሰራን ነው፣ ኮሪደር ልማት፣ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለው ባህር ዳር ነው። ህዝባችን ሰርቪሱ ይገባዋል ብለን ስለምናስብ።
🔵 ጎንደር ቢሄዱ ያን ስልጡን ህዝብና ሀገር ከ70 እና 80 ዓመት በኃላ ዞር ብሎ የሚያየው መንግስት ያገኘው አሁን ነው። ፋሲል ቀንና ማታ እየተገነባ ነው፣ መስቀል አደባባይ የአዲስ አበባውን መስቀል አደባባይ በሚያክል መንገድ እየተገነባ ነው። ፓያሳ እያሸበረቀ ነው። መገጭን 18 ዓመት ከቆመ በኃላ 7 ቢሊዮን ብር መድበን ቀንና ማታ እየሰራን ነው።
🔵 ሃይቅን እየሰራን ነው፣ ጎርጎራን ሰርተናል።
🔵 ማዳበሪያ በከፍተኛ ሁኔታ በቀበሌው እያዳረስን ነው።
🔵 አማራ ክልል ልማት ነው እየሰራን ያለነው። እንደ ልብ እንዳንሰራ ግን የሚያደናቅፉን ሰዎች አሉ። እርሶ ያግዝኑንና ሰዎቹ ይመለሱ።
🔵 ፋሲልን የምንሰራው፣ ማዳበሪያ የምናዳርሰው በወታደራዊ እጀባ ነው። እንዴት ነው አሳሪ መንግስት የሚሆነው? ተቀናኛን የሚባለው ልማት የሚያደናቅፍ፣ ተማሪ የሚያደናቅፍ ነው።
🔵 ህዝቡ ማን እንደሚሰራ ማን እንደሚያወራ ያውቃል።
🔵 ሰላሙን እርሶም ጓደኞቾም ይሞክሩ፤ ይምጡ! ይመልሱ! ልማቱን ደግሞ ልክ እኛ ለምነን እንደምንሰራው (አዋሬ፣ ገበታ ለሀገር) እርሶም ፓርቲዎም ለምነው ተባብረን አማራን ወደ ልማት እናስገባው።
🔵 ጎርጎራን በወታደር ጠብቀን ነው የሰራነው ፣ ጎንደር ፒያሳን የምናድሰው ከኳሪ ሲሚንቶ ለማምጣት በወታደር አስጠብቀን ነው፤ ከየትኛው ወራሪ ሀገር ነው የምንጠብቀው ? ጎንደር እንዳይለማ፣ ባህር ዳር እንዳይለማ ፣ ወሎ እንዳይለማ የሚያደርገው የዚያው ሰፈር ሰው ነው።
🔵 አማራ ክልል እንዲቀየር እየሞከርን ነው።
🔵 ጋዜጠኛ አንቂ ለተባለው ጉዳይ አንድ እግር ሲኦል አንድ እግር ገነት አኑሮ መቀመጥ ሚቻል አይመስለኝም። ወይም የገነትን ፍሬ መብላት ወይም የሲኦልን እሳት መቅመስ ነው። አንዳንድ ሰዎች እዚህም ሰላም ውስጥ አሉ እዛም ጦርነት ውስጥ አሉ። የመረጃ ችግር ያለብን እንዳይመስላችሁ።
🔵 በጅምላ የፓርላማ አባላት፣ በጅምላ የፖለቲካ ሰዎችን የምናስር ከሆነ እርሶም ይታሰሩ ነበር። በጅምላ አይደለም በግብር ነው ሰው የሚታሰረው።
🔵 የግል ምርጫዬን ከጠየቁኝ እኔ ቢቀር ነው የምለው። ይቅር ተባብለን፣ ትተን፣ በደለኛ ካለ ክሰን በሰላም ሀገራችንን እናልማ። ከዚህም ይውጣ፣ ከዩኒቨርሲቲም ይውጣ ከከተማ እስር አይጠቅምም ግን መንግስት ነን፤ መኖሪያ ቤት እንገነባለን ማረሚያ ቤትም እንገነባለን።
🔵 "አሁንም ይናገሩ" ለተባለው ሁሌም በራችን ክፍት ነው። ሞከረናል የአማራ አካባቢ ሰዎችን አነጋግረናል፤ ሽማግሌ ልከናል። በአፍሪካ ህብረት፣ በኢጋድም ሙከራ ይደረጋል። እርሶም ቢያደርጉ በደስታ እንቀበላለን።
09/09/2024
ዘንድሮ 1,363 ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተማሪ አላሳለፉም።
በሌላ በኩል ፤ በኦላይን ከተፈተኑ ተማሪዎች 26.6 በመቶ የሚሆኑት አልፈዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa