Beri

Beri

Share

09/05/2026

"በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት በሴላረስ ፓርክ ከአርሰናል ጋር የምናደርገው ጫወታ ለክሪስታል ፓላስ ይህ ጫወታ ትኩረት የምንሰጠው ጫወታ አይደለም።"

🗣የክሪስታል ፓላስ ኣሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል ጋር የሚያደርገው የመጨረሻ የሊግ ጨዋታ የእቅዳችን አካል አይደለም በማለት ተናግሯል፦

🎙"እኛ አሁን ትልቁ ትኩረታችን የኮንፍረን ሊግ የፍጻሜ ጫወታ ላይ ነው ያለው ይህ በመጨረሻ ሳምንት በሊጉ ከአርሰናል ጋር የምናደርገው የሊግ ጫወታ የእቅዳችን አካል አይደለም እና ትኩረታችን ሙሉ በሙሉ ለመጨረሻው የዋንጫ ጫወታ ዝግጅት ላይ ስለሆነ ሰዎች የዚያን ጨዋታ ውጤት ቢተቹ ለእኔ ግድ አይሰጠ ኝም።"

👀ተጨማሪ ቀልብ የሚስበው ነገር ደሞ ይህ ነው ....
⚠ክሪስታል ፓላስ ኢዜን ለአርሰናል ሲሸጠው ሁለቱ ክለቦች በኢዜ ዝውውር ስምምነት ላይ ያስቀመጡት ውል አርሰናል የሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ አርሰናል ለ ፓላስ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ተጨማሪ ክፍያ ለመክፈል ስምምነት አላቸው።

🤝ሁለቱ ክለቦች የሊጉ የመጨረሻ 38ኛው ሳምንት ላይ በሴላረስ ፓርክ ስታድየም ፓላስ ከአርሰናል ይጫወታል🔺

⌛በዚህ ሰዓት እንደው ዋንጫው ቀድሞ ይወሰናል እንጂ ይህ የመጨረሻ የፓላስ ጫወታ ዋንጫውን የሚወስን ከሆነ ፓላሶች ሁለት አማራጮች ብቻ ይኖራቸዋል

✔️አርሰናል ዋንጫውን እንዲያሸንፍ በመፍቀድ በውላቸው መሠረት 10 ሚሊዮን ፓውንድ ማግኘት።

✔️አርሰናልን ዋንጫ አግዶ ዋንጫውን በማሳጣት ያንኑ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ማጣት😳

🎙የክሪስታል ፓላስ ሊቀመንበሩ ስቲቭ ፓሪሽ ደግሞ ቀደም ሲል ስለ አርሰናል የተናገሩት ... " ለአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ያላቸውን አድናቆት በይፋ ተናግረዋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa