Tadele Kasse

Tadele Kasse

Share

04/02/2023

ሰበር ዜና

የካቲት 5 መላው ህዝበ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኃላ ከአጥቢያው ወደ መስቀል አደባባይ ድረስ በሚሄድ ድምፁን እንዲያሰማ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል!

03/02/2023

#ሩሲያ!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሩስያን ፌዴሬሽን የፓርላማ አባል እና የሩስያ አምባሳደር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የጉብኝታቸው ዋና ዓለማ በተፈጠረው የቤተክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግር መፍትሔ ለማግኘትና ሓሳብ ለመለዋወጥ የጠቀሱት ሲሆን እንዲሁም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን አብሮነቻውና ድጋፋቸውን ለመግለጽ መሆኑን ገለፀዋል።

03/02/2023

ጾመ ነነዌን ምእመናን ጥቁር ልብስን ብቻ በመልበስ በጸሎትና በምሕላ እንዲጾሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!
ሙሉ መግለጫው ከታች ቀርቧል!
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።
በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡"

01/02/2023

"የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያደናቅፍ ነገር ሲገጥም መሞት ግዴታ ነው። ሌላ የምናድርገው ነገር ባይኖርም፤መሞት ግን እንችላለን!"
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa
1221