Koki mela
29/08/2022
15/07/2022
13/06/2022
"አባዲናዎች ሶስት፣ አራት ቀን የቻሉትን ያህል ፈልገዋል፣ አሁን ግን የሉም። ህዝቡ ግን ፍለጋውን ቀጥሏል"--- የማርኮን አባት አቶ ይገረም ማምሻውን በስልክ ከነገሩኝ
ከአራት ወር በፊት ራያን የተባለ የ5 አመት ህፃን ሞሮኮ ውስጥ ሲጫወት በድንገት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ነበር፣ ፍፃሜው አሳዛኝ ቢሆንም አካሉን ማግኘት ተችሎ ነበር። ይህንን ጉዳይ አለም አቀፍ ሚድያዎች በቀጥታ ጭምር ሲዘግቡት ነበር፣ የሀገራችን ሚድያዎችም እንዲሁ።
ከስድስት ቀን በፊት በውሀ ስለተወሰደው የአራት አመት ህፃን ማርኮን ግን ከአንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ መረጃዎች ውጪ ብዘዎቹ ሚድያዎች ችላ ብለዋል። ራስ ያቀለለውን...!
ማምሻውን አባት የሆኑትን አቶ ይገረምን በስልክ አውርቼ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት: "አባዲናዎች ሶስት፣ አራት ቀን የቻሉትን ያህል ፈልገዋል፣ አሁን ግን የሉም። ህዝቡ ግን ፍለጋውን ቀጥሏል። ተስፋችንን በእግዚአብሄር ላይ ጥለን ቁጭ ብለናል።"
ፍለጋው እስከ መጨረሻው በአባዲናዎች እንዲከናወን፣ እንዲሁም ህዝቡ ተደራጅቶ ፍለጋው ላይ እንዲሳተፍ ድምፅ እናሰማ። የሚዘንበው ሀይለኛ ዝናብ ጭራሽ ሳይገፋው ህዝቡ ከመንግስት አካላት ጋር በቅንጅት እንዲረባረብ እናድርግ።
"አይተውት ያልጠገቡትን፣ ስመውት ያልሰለቹትን ህፃን መሞቱን ተረድተው አስክሬኑን እየጠበቁ ውሎ ማደር የህመሙን ጥግ፣ ስቃይ እና ጭንቀቱን እንዴት ችለውት ይሆን?"
19/02/2022
11/05/2021
አሁን ባለንበት ዓለም አብዛኛዎቹ ሰዎች እውነትን መናገር እየከበዳቸው ውሸትን መናገር ደግሞ እንደ ቀላልና የተለመደ አድርገው እየወሰዱ ነው። ታዋቂው የሬጌ ዘፋኝ ቦብ ማርሌይ በአንድ ወቅት "ችግሩ ሰዎች እውነተኛ ሲሆኑ መጠላታቸው፣ ሀሰተኛ ሲሆኑ ደግሞ መወደዳቸው ነው" ብሎ ነበር። ይህም የሚያሳየው በዓለም ላይ ሰዎች ከእውነተኝነት ይልቅ ውሸታምነትን እንዴት የጎላና በብዙ ሰዎች ዘንድ እየተተገበረ እንደሆነ ነው። በጥንት ጊዜም ፕሌቶ የተባለ ፈላስፋ እውነተኛ ሰው እንደማይወደድና ጓደኛ እንደሌለው ተናግሯል።
በሥነ-ልቦና ሳይንስ አንድን ባህርይ መማር ወይም አለመማር ይቻላል። እንደ ባህርያዊ የሥነ-ልቦና ጠበብቶች ሁሉም የሰው ልጅ ባህርይ በመማር የመጣ ነው። ለዚህም ማሳያ ሕጻናት ሲወለዱ "ባዶ ወረቀት" መሆናቸውንና አካባቢ [እኛ] እንደምንጽፋባቸው፣ በዚህም ልጆቻችንን እኛ እንደምንፈልገው አድርገን ማሳደግ እንደምንችል አስረግጠው ይነግሩናል።
ልጆቻችንን ለመቅረጽ ደግሞ የኛ የወላጆች ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ባለሙያዎቹ በጥናት አስደግፈው ይናገራሉ። እነርሱ እንደሚሉት ወላጆች የልጆች የመጀመሪያ የቅርብ ሰዎች በመሆናቸው ልጆች እነርሱን በማየት ወደፊት ምን አይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ማወቅ ይቻላል። በመሆኑም ወላጆች መልካም የአስተዳደግ ዘይቤን መከተል እንዳለባቸው ይመከራል። ለምሳሌም ወግ አጥባቂና ጨቋኝ ወላጆች የልጆችን የወደፊት ባህርይ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ፈሪ፣ በራሳቸው የማይተማመኑ፣ ኃላፊነትን የማይወስዱ፣ ጥገኛ እንዲሁም ነውጠኛ የመሆን እድላቸው የሰፋ ሲሆን ውሸታምና አጭበርባሪ ሊሆኑ ይችላሉ።
ቻናሎቻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ: https://youtu.be/flghfRbyGVE
ቴሌግራም: https://t.me/psychforlife
Click here to claim your Sponsored Listing.