ASCHO Mng

ASCHO Mng

Share

22/01/2026
Photos from ASCHO Mng's post 30/01/2024

ዓድዋ ኢትዮጵያዊያን በብሔራዊ ገዥ ሀሳብ ሲሰባሰቡ ጠንካራ የማስተባበር፤ የመምራት፤ የመደማመጥና ፈተናዎችን በአብሮነት የመሻገር ችሎታ እንዳላቸዉ ያስመሰከሩበት ታላቅ ታሪክ ነው!

Photos from ASCHO Mng's post 28/01/2024

ሚዲያዎች በመንግስት አሰራር ውስጥ ግድፈቶች እንዲታረሙ የማሳየት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል - የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ

ሚዲያዎች በመንግስት አሰራር ውስጥ ግድፈቶች እንዲታረሙ የማሳየት እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የማገዝ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ አሳሰቡ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያስገነባውን የፋና ላምሮት ስቱዲዮ እያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ቦርድ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ መገናኛ ብዙኃን በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ማኖር እንዲችሉ ሁነቶችን ከመዘገብ አልፈው ትኩረታቸውን በአሰባሳቢ ትርክት እና በትውልድ ግንባታ ስራ ላይ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ባለብዝሃ መልክ በሆነችው ኢትዮጵያ ህዝቦችን ከሀገራቸውም ሆነ እርስ በእርስ የሚያስተዋውቁ ይዘቶች ላይ በማተኮር የስነ ልቦና መቀራረብ መፍጠር እንዲሁም አብሮነትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር የሚዲያዎች ዋና ትኩረት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ሚዲያዎች እርስ በእርሳቸውም ሆነ ከሲቪል ማህበራት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸውን ድርሻ በሚገባ መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉም ጠቁመዋል።

በተለይም በተልዕኮ፣ በይዘት እና በአሰራር ተቀራራቢ የሆኑ ሚዲያዎች ተገቢነት ከሌለው ፉክክር ወጥተው ትብብርን፣ ተቀራርቦ ተሞክሮ መለዋወጥን በማዳበር እና ለበለጠ ውጤታማነት ሰብሰብ ብለው በመቀናጀት የሀገሪቱን ገጽታ በተሻለ መልኩ መገንባት አለባቸው ብለዋል።

ስቱዲዮው በዋናነት የመዝናኛ ፕሮግራሞችን እና አሳታፊ መድረኮችን እንዲያስተናግድ ታስቦ የተገነባ ነው ተብሏል።

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa