Yami Media

Yami Media

Share

So like,share and invite.

07/07/2022
23/03/2022

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ!

ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከጤናቸው ጋር በተገናኘ በይፋዊ መንገድ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ዘግቧል።
ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም አቶ ተወልድ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ላለፉት 11 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 ዓመታት አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡

22/03/2022

በኢትዮጵያ ላይ ከተጣሉት ማዕቀቦች ሁሉ እጅግ የከፋው ማዕቀብ ነው። ይህ ረቂቅ ህግ በአንድ በኩል ባለፈው አመት እንዳደረጉት በሰብዓዊ እርዳታ ስም ለህወሓት የጦር መሣሪያ ለማቅረብ ያለመ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በእርዳታ አቅርቦቱ ዙሪያ አንዳች ጥያቄ ቢያነሳ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉሎአል በሚል ማዕቀብ ይጣልበታል።
በዚህ መልኩ ያለ በቂ ምክንያት የሚጣለው ማዕቀብ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ እንዳይገዛ ለማድረግ፣ እንደ ሩሲያ፥ ቻይና፥ ቱርክ፥ የተባበሩት አረብ ኢሜሬት፥ ኢራን እና ኤርትራ ከመሳሰሉት ወዳጅ ሀገራት ምንም ዓንነት ድጋፍ እንዳያገኝ ማድረግ፣ እንዲሁም ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፥ የዓለም ባንክ፣ ከአሜሪካ ልማት ባንክ፣ ከአውሮፓ ልማት ባንክ፣ ከኢሲያ ልማት ባንክ፣ ከአረብ ልማት ባንክ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ምንም ዓይነት ብድር እንዳያገኝ ማድረግ እና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ፈንድን ማቋረጥ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
ይህ ሁሉን አቀፍ የሆነ ማዕቀብ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪ የፀጥታው ምክርቤት አባል ሀገራት፣ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት፣ የNATO አባል ሀገራት እና ሌሎች የአሜሪካ ወዳጅ ሀገራት ተሳታፊ ይሆናሉ ይላል። በአጠቃላይ የHR6600 የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን እንደ ሰሜን ኮሪያ፥ ኩባ፥ ኢራን ወይም ዝምባዋብዌ በማዕቀብ ማቆራመድ አሊያም ሀገራችንን እንደ ዩጎዝላቪያ፥ ሊቢያ፥ ኢራቅ፥ ሲሪያ ወይም የመን ማፈራረስ ነው።
ይህ ረቂቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊንታገለው የሚገባ የባርነት ቀንበር ነው። በሴራ እና ጦርነት ያልቻሉትን ነገር በማዕቀብ ኢትዮጵያን እንዲያፈርሱ መፍቀድ የለብንም

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

4kilo
Addis Ababa