Hab Studio

Hab Studio

Share

19/06/2026

እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ እንዴት ከባድ ግዜያችሁን አለፈላቹ ?
እንዴት የተሰበረ ልባችሁን ጠገናችሁ? የአፈሰ እጃችሁ ባዶ ሆኖ ስታገኙት ..... ድንጋጤ እንዴት አደረጋቹ ?
.
.
እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ

ስትታመሙ ስታጡ ቤት ስትውሉ መረሳት እንዴት ሳይሰብራችሁ ቀረ ? ....

ያልፍልኛል ብላችሁ የሄዳችሁበት መንገድ አባጣው ጎርባጣው አተርፍ ባይ አጉዳይ ሲደርጋቹ ምን አላችሁ??
.
.

እናንተ የበረታችሁ

ድንገተኛ ሃዘን ጎጃቹ ሲገባ፣ ያተርፋል ያላችሁት ሲያከስር ፣ መከዳት ልባችሁን ሲያርደው ......እንዴት ጨለማው ነጋላችሁ?

ተስፋችሁ የተሟጠጠ ማድጋችሁ የጎደለ ኪሳቹ የተራቆተ እለት ........ ጭንቀት እንዴት ድል ሆነላቹ
.
.

እናንተ የበረታቹ ሆይ

መውለድ እምቢ ሲላችሁ ፣ ልጃችሁ ሲታመም፣ ጤናችሁ ሲጓደል .....ተስፋ የለም ስትባሉ ልባቹ እንዴት ተስፋ አየ ???
.
.

መፅሃፍ ቅዱስ የበረቱ ሰዎችን

የአንበሳን አፍ ከዘጉ ፣ከሰይፍ ስለት ካመለጡ፣ የእሳትን ሃይል ካጠፉ፣ የባእድ ጭፍሮችን ካባረሩ ፣በጦርነት ሃይለኛ ከሆኑ ሰዎች እኩል ከድካማቸው የበረቱትን ያወሳል

ከድካም መበርታት ቀላል አይደለም !

ቅዱስ ዳዊት ልጁ አቤሰሎም ሲያሳድደው
የሚያስጨንቁኝ እንዴት በዙ!
ብዙዎች በእኔ ላይ ተነሡ። ብሏል

ትግስተኛው እዮብ መከራ ሲሸከም ድካሙ ሲበረታበት ስለ ምን ከማህፀን አልሞትሁም ብሏል
.
.

የሰው ልጅ ሃያል ነው ከድካሙ ይበረታል
አይነጋም ያለው ይነጋል
.
.

እናንተ የበረታችሁ ሆይ እናንተ ግን እንዴት እንዴት በረታቹ ???
Via : Adhanom Mitiku
Hab Studio

19/06/2026

ከወራት በፊት በቀላሉ ከሀገር ለመውጣት እያለ ቪዲዮ ሲሰራ ነበር
አሁን ደግሞ...
ከሀገር ለመውጣት መንገዱን አሳዩኝ እያለ ነው🤔

13/06/2026

#መደበኛ በረራ ተጀመረ
አየር መንገዱ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ መደበኛ በረራ ይጀምራል‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ደብረማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራዎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
መንገደኞች የበረራ ቲኬቶችን በሁሉም የቲኬት መሸጫ ቢሮዎች ማግኘት እንደሚችሉ የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

13/06/2026

አሳዛኝ መረጃ💔

የአርቲስቷ አሳዛኙ ዜና እረፍት😭
በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽና በራስ ቴአትር እንዲሁም በህጻናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት ለረጅም ዓመታት በተዋናይነት ስታገለግል የቆየችው አርቲስት ሰላማዊት ደስታ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ይታወሳል፡፡ አርቲስቷ ለረጅም ጊዜያት ታማ በህክምና ስትረዳ የቆየች ሲሆን እንደ መንግስት ቅጥር አርቲስትነቷ ደሞዟ ህክምናውን ለመከታታል በቂ ስላልነበረ የሰዎችን እጅ ለማየት ተገዳ እንደነበር የቅርብ ጓደኞቿ ይናገራሉ፡፡

አርቲስቷ ሰላማዊት ደስታ ለረጀም ዓመታት አብሯት የቆየ በሽታ ሳቢያ አልጋ ከያዘች በርካታ ጊዜያት የሆናት ሲሆን ከአንድ ኣመት በፊት ደግሞ የቀኝ ጡቷ መቆረጡን የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ በዚህም ሳቢያ በሽታው እያመረቀዘባት የተሻለ ህክምና ለማግኘት የህዝቡንና የአርቲስቱን ድጋፋ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ሰሚ እንዳላገኘችና በባዶ ቤት እረፍቷ መሰማቱ ታውቋል፡፡

በአርቲስቷ አሟሟት ምክንያትም በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በኩል ከፍተኛ የተባለ አለመግባባት ነግሷል፡፡ በጣም ጥቂት ባለሙያዎች ብቻ ከአርቲስቷ ጎን እስከ መጨረሻው ነበሩ የተባለ ሲሆን፤የተቀሩት ግን ሞቷን ለማርዳት ብቻ ቀደሚዎች ነበሩ ተብሏል፡፡

የአርቲስት ሰላማዊት ህልፈት ግንቦት 21/2018 ዓ.ም በተሰማ ጊዜ ግን በህመሟ እና በችግሯ ጊዜ አብረዋት ያልነበሩት የሙያ አጋሮቿ በፌስቡክ ማዘናቸውን ለመግጽ ግን የቀደማቸው አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታቸውም ብዙዎችን አስቆጥቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አርቲስት ሰላማዊት ካረፈች በኋላ የተወሰኑ የሙያ ጓደኞቿ የመታሰቢያ ዝግጅት በማለት ሰሞኑን አንድ ፕሮግራም ልማቅረብ ሽር ጉድ እያሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
ለመሆኑ ለአርቲስት ሰላማዊት ደስታ ምደረግ የነበረበት ድጋፍና የአርቲስቱን ዝምታ እንዴት አያችሁት? አስተያየት ስጡበት?
©ዋልያ ሚዲያ

Photos from Hab Studio's post 08/06/2026

ነውረኞቹን_ተጠንቀቁ ! ያሳዝናል

ይህ ወንድማችን ሚኒሊክብርሀኑ ይባላል፣ከቤተሰቡ ከጠፋ 2ዓመት አልፎታል!የተጨነቀች እህቱ "እባካችሁን ወንድሜ ጠፍቶ ቀረብኝ ዛሬ ደግሞ ልደቱ ነበር እናት አባቱም እያለቀሱ ነው አግዙኝ"ብላ በፌስቡክ ለጥፈነው እናንተ ደጋጎችን አስቸግረን ነበር፣

ትላንት አንድ ኮማንደር ነኝ የሚል ሰው በተቀመጠው የእህቱ ስልክ ደውሎ" ትክክለኛ እህቱ ነሽ?እስካሁንስ የት ሄዳችሁ ነው?ልጁ እኮ ጭንቅላቱን በጥይት ተመቶ በአፋር ክልል ወታደራዊ ካምፕ ተኝቶ ነው የሚገኘው፣ፎቶውን እልክልሻለሁ፣ብታይው ታውቂዋለሽ ወይ?ብሎ ጠየቃት!አዎ ወንድሜ አደል አለችው!

በፍጥነት Edit ተደርጎ የታመመ ሰው ፎቶ ልኮላት የተጨነቀች እህት ስታየው እውነትም ወንድሟ ሚኒሊክ መስሏት እንኳን በህይወት ኖረልኝ"ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?"ብላ ጠየቀችው፣

አንቺ ተረጋጊ መቀበል ከቻልሽ ሹፌር አመቻችና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እልክልሻለሁ፣ብሎ የተባባሪውን የሹፌር ስልክ ላከላት!

ምስኪን እህት ፅዮን ሹፌሩ የተባለው ጋር ደውላ አወሩ፣አይዞሸ እኔም ወንድ ልጅ አይደለሁ፣መውደቂያዬን አላውቅም፣ለራሴ ስል ነው መልካም ማደርገው፣አላት፣የነዳጅ 8000ብር ላከችለት፣ወደ አዲስ አበባ እስኪመጣ ኦክስጅኑ መነቀል ስለማይችል ተመላሽ የሚሆን ማስያዣ 23500 ይፈልጋሉ ብሏት በድጋሚ ላከችለት፣አድራሻዋን ጠየቃት ስደርስ እደውላለው አላት፣

ትላንት ቀኑን ሙሉ በጉጉትና በተስፋ ጠበቀችው፣በየመሀሉ ስትደወልለት እዚህ ደርሻለው እያለ ተስፋ ሰጥቷታል፣ ሲመሽ አሁንስ ወንድሜ የት ደረስክ ስትለው መተሀራ ነኝ ተዘጋጂ ብሏታል!

ቶሎ በመድረሱ ገርሟታል፣ቀኑን ሙሉ እያለቀሰች ለአመታት ድምፁ እንኳ የናፈቃት ወንድሟን ለማየት ጓጉታለች፣ "አይኑ ግን ያያል?ብላ ደጋግማ ጠይቃለች!እስክትዳብሰው ጓጉታለች!!

ሰዓታት ሄዱ ቀኑን ሙሉ ስትደውልለት የነበረው ሹፌር ስልኩ ዝግ ሆነ፣ኮማንደር የተባለው ጋርም ስትደውል "ጥሪ አይቀበልም" አላት፣ ደነገጠች ስታሰላስል እንደተጫወቱባት ተረዳች፣ወደ ፖሊስ አመራች፣ "ሸውደውሻል ሌቦች ናቸው" አመልክቺ አሏት!!

በሰው ህይወት የሚጫወቱ አረ መ ኔዎችን ህጉ እንዴት ይሆን የሚቀጣቸው?ከመስረቃቸው የሚሄዱበት የወንጀሉ ርቀት አስቡት እስኪ😭 በውሸት በተቀነባበረ ፎቶ እንዲህ ሆኖ ሲያዩ ሌላ የሚጎዳ እናት አባት ቤተሰብ አለ እኮ፣ እንዴትስ ነው የሚያስችላችሁ? እባካችሁን ሌሎቻትሁ ተጠንቀቁ‼️

እህቱ ፅዮን "ከኔ ተማሩ ከወንጀለኞች ራሳችሁን ጠብቁ🙏 "ብላችኋለች!እናንተም መረጃው ለብዙዎች እንዲደርስ ሌላ ሰው እንዳይሸወድ #ሼር አድርጉ🙏 ለምታውቁት ሁሉ አሳውቁ‼️
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa