R.I.P
This page allow each Associates valued to post stories about their relatives and friends who passed away to stay our memories.
የዚህ ገጽ ዓላማ በህይወት የሌሉ ወገኖችን በዘላቂ ሁኔታ ለማሰብ ነው ፡፡
ይህ ገጽ እያንዳንዱ ተጓዳኝ ትዝታዎቻችንን ለማቆየትና የሟች ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው ታሪኮችን ለማስቀመጥ እንዲሁም ታሪኮችን ለማቆየት ያስችላቸዋል።
04/07/2021
ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ዜና 😭
እናታችን ዶክተር አበበች ጎበና አረፉ
አዳዬ - ነብስ ይማር
The extraordinary women of our planet, Mother Tesesa of Africa, Dr Abebech Gobena passed away today this morning.
ላደረጉት መልካምነት ወደር ለሌለው ደግነት
እናመሰግናለን 🙏
15/04/2021
የቀድሞው የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ የነበሩትአቶ ጸጋዬ ሃይለማሪያም ዛሬ በሞት ተለይተዋል።
Via ሽዋዬ ከፍያለው
07/04/2021
የማንዶሊኑ ተጫዋቹ - ወይ ካሊብሶ አርፈዋል
🎼 🎻
አንጋፋው ድምፃዊ፣ የዜማ እና የግጥም ደራሲ፣ እንዲሁም የማንዶሊኑ ንጉስ አየለ ማሞ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ነገ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ይፈፀማል ተብሏል።
... በሃገራችን ኢትዮጵያ በሙዚቃው ዘርፍ ታላቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ ካሉት የሙዚቃ ስዎች አንዱ የግጥምና የዜማ ደራሲ ፣እንዲሁም ብቸኛው የማንዶሊን ተጫዋች አርቲስት አየለ ማሞ ናቸው።
አርቲስቱ የተወለዱት ጥር 12 ቀን 1934 ዓ.ም ሲሆን ወደ ሙዚቃው ዓለም ከመግባታቸው በፊት አዲስ አበባ ደብር አሜን ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በድቁንና ሙያ አገልግለዋል።
ከጥር 1 ቀን 1949 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ የክብር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍል በመቀጠር የተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦችን ዘፈን በመዝፈን ይጀምሩና በመቀጠልም በዘመናዊና ባህላዊ ተወዛዋዥነት በመስራት እስከ አስልጣኝነት ተጉዘዋል።
አርቲስቱ በነበራቸው ሁለገብ እንቅስቃሴ ድምፃዊ ደስአለኝ መላኩ (ባላገሩ) ፤ አቦነሽ አድነው ፤ ኃይልዬ ታደሰን ያፈሩ አንጋፋ ባለሙያ ናቸው።
በተለይ አርቲስቱን ልዩ በሚያደርጋቸው የማንዶሊን የሙዚቃ መሳርያ "ወይ ካሊብሶ" በሚለው ዘፈናቸው የሚታወቁ ሲሆን በመጀመሪያ የተጫወቱት ዜማ ግን "የኔውብ አይናማ "የሚል ሲሆን ወዲያው በማከታተል "ያለሰለሴ ባዬቲ" ኦሮምኛ ፣ በመቀጠልም " እማማ ድንብሎ" የሚል ጉራጊኛ መድረክ ላይ ተጫውተዋል።
በውጭ ሃገራትም ኩባ፣ ስውዲን፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን በመሄድ ሙያውን በተግባር ያስመሰከሩ ፣ የጥበብን ፀጋ የተላበሱ ሁለገብ አርቲስት ናቸው።
አርቲስት አየለ ማሞ ክብር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍልን ለ 34 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን ክፍሉ ከፈረሰ በኋላ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1998 ዓ.ም ለ10 ዓመት "በክስታኒ ባንድ" በኃላፊነትና በሙያቸው አገልግለዋል።
ክስታኒ ባንድ ካፈራቻቸው ወጣት አርቲስቶችም መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ አብነት አጎናፍር፣ ፀጋዬ ስሜ (ኦሴ ባሳ) ፣ሙዚቀኛ ደስአለኝ ታደሰ ፣ ሙዚቃ አቀናባሪው መሐመድ ኑር ሁሴን የሚጠቀሱ ናቸው።
አርቲስቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሩት ዜማ "አሸብርቆ ደምቆ እንደፀሐይ"የሚለው ሲሆን ይህንንም ጥሩ አድርጋ የተጫወተችው ብዙነሽ በቀለ ናት።
አርቲስት አየለ ማሞ በግጥምና በዜማ ስራቸው ከሰጣቸው አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን መካከልም ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ፣ መሐሙድ አህመድ ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ኩኩ ሰብስቤ ፣ኤፍሬም ታምሩ ፣ሀመልማል አባተ ፣ብፅአት ስዩም ፣ ወረታው ውበት ፣ አስቴር ከበደ ፣ እያዩ ማንያዘዋል ፣ ሻምበል በላይነህ፣ ደረጀ ደገፋው ፣ጌታቸው ጋዲሳ ፣ ህብስት ጥሩነህ፣ ምንያህል ጥላሁን ገሠሠ ፣ውብሻው ስለሺ፣ መንበረ በየነ ፣ ትዕግስት ይልማ ፣ከበቡሽ ነጋሽ (ሚሚ) ፣ ገነነ ኃይሌ፣ ጌታቸው ተካ ፣ ዓለማየሁ ግዛው...የሚያስታውሳቸው የስራቸው ተቃዳሾች ሲሆኑ አሁንም ለወጣት አርቲስቶች የግጥምና የዜማ ሥራቸውን ሰጥተዋል።
አርቲስቱ በአሁኑ ሰዓት ከግጥምና ዜማ ስራቸው ጎን ለጎን "አዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክት"በማንዶሊን ተጫዋችነት አገልግለዋል።
አርቲስት አየለ ማሞ ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ ለ64 ዓመት በሙዚቃ ህይወት ተጉዘዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
251