Sbahe Tube
18/01/2026
እንኳን "ለከተራ" በዓል አደረሳችሁ!!
07/01/2026
አማን በአማን/፪/
መንክር ስብሐተ ልደቱ
‟ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ ዘይከውን ፍስሐ ለኲሉ
ለሁሉም ፍጥረት የደስታቸው ምንጭ የሚሆን የዓለሙ ቤዛ አማኑኤል ዛሬ በቤተልሔም ዋሻ ተወለደ❤❤❤
‟እሰይ እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት ❤❤❤
እንኳን አደረሳችሁ!!!
05/01/2026
❝ ❞
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከልዕልና ሥፍራህ ወርደህ እንደ ድኃ በከብቶች በረት መተኛትህ በጨርቅ መጠቅለልህ ሰውን ስለመውደድህ ነው።
◉.ልብስህ እሳት መጎናጸፊያህ እሳት የሆንክ ጌታ በብርዱ ወራት የእንስሳት እስትንፋስ መሻትህ ይኽ ሁሉ ሰውን ስለመውደድህ ነው።
◉.እንደ ሽፍታ ወንበዴ በሽፍቶች እጅ ተይዘህ ለፍርድ መቅረብህ ሰውን ስለመውደድህ ነው!!
◉.መላእክት ደፍረው ማየት የማይችሉት ፊትህ ላይ የመርገም ልጆች አይሁድ ምራቃቸውን ሲተፉብህ ዝም ማለትህ ይኽ ሁሉ ሰውን ስለመውደድህ ነው።
◉.ከሊቶስትራ እስከ ቀራንዮ እየወደቅክ እየተነሳህ መስቀሉን ተሸክመህ መጓዝህ ሰውን ስለመውደድህ ነው።
◉.በዕለተ ዓርብ ነፍስህን አሳልፈህ እስከመስጠት የተቀበልከው መከራ ይኽ ሁሉ ሰውን ስለመውደድህ ነው።
◉.ሙታንን ከመቃብር የምታነሣ አምላክ ወደ መቃብር መውረድህ ሰውን ስለመውደድህም አይደል?
◉.ጌታ ሆይ!! ሰው ግን ምን ቢያደርግልህ ነው እንዲህ መውደድህ?
◉.ሕግ ያፈረሰው ሰው፣ሆኖ ሳለ
◉.የምትወለድበት ሥፍራ የከለከለህ ሰው ሆኖ ሳለ
◉.ወደ ግብጽ በረኻ በሕጻንነትህ ለስደት ያበቃህ ሰው ሰው ሆኖ ሳለ
◉.አሳልፎ ለሞት የሰጠኽ ሰው ሆኖ ሳለ
◉.በመስቀል ላይ በችንካር ቸንክሮ የሰቀለህ ሰው ሰው ሆኖ ሳለ
◉.ወደ መቃብር ያወረደህ ሰው፣መቃብርህን በወንበዴዎች ያስጠበቀ የሰው ልጅ ሆኖ ሳለ ሰውን እጅግ መውደድህ እንደምን ያለ ፍቅር ነው!!!
◉.ይኽንን ሊመረምር ኅሊናዬ በነፋስ አውታር ተጭኖ ወደ ላይ አየር ወጣ ወደ ጥልቁም ወረደ፡ከአድማስ እስከ አድማስ ተሽከረከረ የፍቅርህን መጠን ግን ሊደርስበት አልቻለምና አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።
Click here to claim your Sponsored Listing.