Knowlede
የእውቀት ስራ አመራር አላማ
• የተቋምን የዕውቀት ክምችት ስርአት ባለው መልኩ መምራት፣
• ዕውቀትን ለሌሎች ማስተላለፍ /ማጋራት/፣
• ዕውቀትን መልሶ መጠቀም፣
• ፈጠራዎች ሀገራዊ ዕውቀቶች ላይ እንዲመሰረቱ ማድረግ፣
የዕውቀት ስራ አመራር አስፈላጊነት
በአሁኑ ሰአት በአለም ላይ የሚገኙ ተቋማት ያላቸውን የአገልግሎት ቅልጥፍና ውጤታማነት ለመጨመር ቅድሚያ እየሰጡት ያለው ጉዳይ በተቋማቸው የሚገኘውን ተቋማዊ ዕውቀት ማሰባሰብ ነው፡፡ ይህም ያሉበትን ደረጃ በማወቅ ያላቸውንና የሌላቸውን ዕውቀት በመለየት መፍጠር፣ ያለውን በማሸሻልና መልሶ በመጠቀም፣ የሠራተኞቻቸውን አቅም ቀጣይነት ባለው የተቋም ዕውቀት ላይ በመመስረት ማሳደግና የውስጥ አሰራራቸውን ማጎልበት ቅድሚያ የሚሰጡት ተግባር በማድረግ እየሰሩበት ይገኛል፡፡ በዚህም ዋናው አላማቸው አገልግሎትን በማሻሻል፣ ጥራትን በማስመዝገብ እንዲሁም ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር የተገልጋዮቻቸውን ፍላጎት ከሌሎች በበለጠ በማርካት ውድድርን አሸንፎ መውጣት ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚጠቀሙበት ስልት ደግሞ በተቋማት ውስጥ የዕውቀት ስራ አመራርን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡
ይህ ተግባር ባለንበት ወቅት ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለመፍጠር እንዲሁም የተቋም ትውስታዎችን በማጉላት መልካም የሆኑ ተቋማዊ ባህሎችን ጠብቆ ለማቆት አዋጪነቱ የጎላ ከመሆኑ በተጨማሪ የመንግስት ዘርፍ አገልግሎትን ከማሳለጥና ውጤታማ ከማድረግ አንጻር ሰራተኛው ባለበት በስራ ላይ ሆኖ በማንበብና በመስማት የራሱን ክህሎት በማደበር ራሱን የሚበቃበት አይነተኛ መንገድ በመሆኑ በእኛም ሀገር አሰራሩ ቢለመድ የምንሄድበትን የለውጥ ጉዞ ቀና ከማድረግ አንጻር አስተዋጽዎው ከፍ ያለ በመሆኑ ግንዛቤውን መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Addis Ababa
1000