Abu Raslan Mujahid
እክዋኑል ሙስሊሞች እሄን የሼክ ኢሊያስ አህመድን ዳዋ በደምብ እያሰራጩ ነዉ ።
ምን ተገኘ?
ሃይማኖትን ለምርጫ ፍጆታ ማዋል
~~~~~~~~~~~~~
በ1997 ምርጫ ጊዜ ግንባር ቀደሙ የኢህአዴግ ተገዳዳሪ ፓርቲ የነበረው ቅንጅት ነገሮች አልጋ ባልጋ ሳይሆኑለት ቀሩ እንጂ ለኢስላምና ለሙስሊሞች ግልፅ ስጋት ነበር። በጊዜው ከቅንጅት ከፍተኛ አመራሮች አንዱ የነበረው ብርሃኑ ነጋ ያለምንም ሃፍረት የፈረንሳዩን ፀረ–ሒጃብ ህግ እንደሚደግፍ በግልፅ ነበር የተናገረው። ከሙስሊሞች በኩል ፓርቲው "ፀረ–ኢስላም ነው" የሚለው ጩኸት ሲያይል ጊዜ የያኔው ሰለፊያ ጋዜጣ ላይ ቀርቦ ‘እኔ ማለት የፈለግኩት ልጆቻችን ተወያይተው፣ ተስማምተው ያስቀሩታል ማለቴ እንጂ እኛ እናግዳለን ማለቴ አይደለም’ ብሎ ነበር። (ቃል በቃል አይደለም።) በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ክርክር ሲደረግም ‘ኢትዮጵያ ከኬንያና ደቡብ ሱዳን በስተቀር በዐረብ ሃገራት ስለተከበበች ስጋት ተደቅኖባታል’ የሚል የደርግን ያረጀ ያፈጀ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች" ትርክት አስተጋባ። ፖለቲከኛ በተለይ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት መራጮቹን ከሚያስከፋ ቃል ይጠነቀቃል። እንዲያውም ሃሰተኛ የተስፋ ቃል እየገባ ሊያማልል ይሞክራል። ከብርሃኑ ነጋ የታየው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነበር። ሰውየው ወይ የፖለቲካ ብስለቱ ለእድሜውና ለአካደሚ ማእረጉ የሚመጥን አይደለም። ወይ ደግሞ ለኢስላምና ለሙስሊሞች ያለው ጥላቻ ከፖለቲካ ትርፉ በልጦበታል። አለያ ደግሞ በፀረ ኢስላም አቋሙ ለኢስላም ጥላቻ ያላቸው ምቀኞችን ድምፅ ማግበስበስ ፈልጓል። ከዚህ ሊወጣ አይችልም።
ዛሬ በኔ ላይ የሚያሴር አካል "አያቴ ሙስሊም ነበረች" እያለ ሊደልለኝ አጉል ይሟሟታል። አሄሄ! "ውሻ ጭራውን የሚቆላው ላንተ ሳይሆን እጅህ ላይ ላለው ዳቦ ነው።" ገና ስልጣን ሳይዝ እንዲህ አይነት እኩይ አላማውን ግልፅ ያወጣ ሰው ኩርሲዋን ቢቆናጠጥ ምን ሊያደርግ እንደሚችል መገመት ነው እንግዲህ።
ልደቱ አያሌውም "የኢትዮጵያ ህዝብ’ኮ የዘውድ ስርአትን ሲናፍቀው ነው የሄደበት" እንዳለ ሲወራ ሰምቻለሁ። በራሴ ግን አላረጋገጥኩም።
በጊዜው በቅንጅት ደጋፊዎች ኢህአዴግ የሙስሊም አክራሪነትን እንዳስፋፋ፣ በሃገሪቱ ከኢህአዴግ መምጣት ጀምሮ የሙስሊሞች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እንደጨመረ እና መሰል ይዘት ያላቸው ፅሁፎች ለምእራባውያን ጭምር እንደተፃፉ በሰፊው ሲሰራጭ ነበር።
ከመሆኑም ጋር ብዙ ህዝብ በኢህአዴግ ክፉኛ ተንገሽግሾ ስለነበር ለነዚህ ጉዳዮች ተገቢ ትኩረት አልሰጠም ነበር። ብርሃኑ ያንን ክፉ ንግግሩን በተናገረበት መድረክ ላይ ባቀረበው ኢኮኖሚ–ተኮር ሪፎርም (በተለይም ግብር ጋር በተያያዘ) ተሸንግለው "ለምን መርካቶ ቢሮ አትከፍቱም?" ያሉ ነጋዴዎች ነበሩ። (እርግጥ ነው "እምነታችንን በሆዳችን አንለውጥም" ብለው መድረክ ረግጠው የወጡ ቆፍጣናዎች እንደነበሩም ሰምቻለሁ።)
በሌላ ጫፍ ኢህአዴግም ሃይማኖትን ለምርጫ ፍጆታ የመጠቀም ዝንባሌ እንደነበረው በተጨባጭ የሚስተዋል ነበር። ቅንጅትን ጎጃም ላይ ፀረ ክርስትና፣ ወሎ ላይ ፀረ ኢስላም አድርገው በማቅረብ ህዝብ ሲቀሰቅሱ እንደነበር ሰምቻለሁ። በራሴም የታዘብኳቸው ነገሮች ነበሩ። ዱዓትና መሻይኾች ጭምር የኢህአዴግ አባላት ሆነው፣ የኢህአዴግ የምርጫ ምልክት (ንብ) ያለበት ቲሸርት ለብሰው ሲቀሰቅሱ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ከምርጫ በሁዋላ ምን ተከሰተ? ለብዙዎች እንደማይሰወረው ቅንጅት ውጥንቅጡ ወጣ። ኢህአዴግ ደግሞ ከወትሮው በተለየ መልኩ በኢስላም ላይ ዘመተ። አሕባሽን ከትቢያ አንስቶ በግላጭ አዝሎ በመዞር ሙስሊሞች ላይ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ውርጅብኝ አወረደ። በአይናችን የምናየውን ገልብጦ በፕሮፓጋንዳ ማሽኖቹ አጉል ሊግተን ተጋጋጠ።
ዛሬም ተመሳሳይ ድባብ ላይ ያለን እየመሰለኝ ነው። ሙስሊሞ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
132