ETHIO MEDIA

ETHIO MEDIA

Share

11/09/2022

መልካም በዓል 🙏

10/09/2022

በነገራችን መሃል…!!

"…የመንግሥት አክቲቪስቶች ስለሚያወሩት ተያዘ ተለቀቀ ጉዳይ እኔንም ግራ እየገባኝ ነው። በራያ ግንባር ውጊያው እንደቀጠለ ነው። የሚሞተውና የሚቆስለው ስፍር ቁጥር የለውም። ውጊያው ያለው የአላውሀ ወንዝን ተሻግሮ በጉብየና በበላጎ ተራራወች ላይ ነው። ይህ የአላውሀ ወንዝ በላይኛው በኩል ያለው ተራራው በመከላከያ የተያዘ ተራራ ነው።

"…አላማጣ ደረስን፣ መቀሌ ልንገባ ነው የሚሉት ከየት አምጥተው እንደሆነ አልገባኝም። የራያው ግንባር ልክ እንደ ጎንደር እና እንደ ሰቆጣው ግንባር በወታደራዊ ዲሲፒሊን እየተመራ አይደለም። የራያ ህዝብ ሞት ቀለቡ ከሆነና በመንግሥት ከተረሳ ቆየ። የዐቢይ አሕመድ መንግሥት በራያ በኩል ለምን ወደፊት መግፋት እንደማይፈልግ እሱና የሚያመልከው አጋንንቱ ናቸው የሚያውቁት።

"…እውነት ብቻ…!!

13/07/2022

"ኦነግ ሸኔ አንድ እግሩን አዲስ አበባ፣ አንድ እግሩን ወለጋ የተከለ ነው።" - አቶ ማሙሸት አማረ

ኦነግ ሸኔ የፌደራሉንና የክልሉን መንግስታዊ መዋቅር የተቆጣጠረ ነው። ገዥው ፓርቲ በክልሉ ባሉ መዋቅር የሽብር ቡድኑን በመደገፍ የዘር ፍጅቱ አገር አቀፍም ሆነ አለም አቀፋዊ ትኩረት እንዳያገኝ በማዘናጋት፣ አጀንዳ በማስቀየር፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ራሱን የሚከላከልበት ሁኔታን በመንፈግ ለጥቃት እንዲጋለጥ በማድረግ ለተፈፀመው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ ነው። የመንግስት ሚዲያዎች ወይ ከሽብር ቡድኑ ጎን ይቆማሉ፣ ወይ የዘር ፍጅቱን እንዳላዬ ያልፉታል።

በአጭሩ ኦነግ ሸኔ የአማራን ዘር ያጠፋል፣ መንግስት መዋቅራዊ ድጋፍ ያደርግለታል፣ የመንግስት ሚዲያዎች ወንጀሉ ትኩረት እንዳያገኝ ይሸፋፍናሉ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

AA
Addis Ababa
10000