Abe Sam
31/07/2021
ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተሰጠ ማሳስቢያ
| የህዝባችን አንድነትና ፅናት ለመሸርሸር ጠላት እየፈበረከ የሚረጫቸውን አሉባልታዎች መከላከል ያስፈልጋል ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አሳስቧል።
በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የታየው ህብረትና በአንድነት መቆም ጠላቶቻችንን አስደንግጧል ያለው መከላከያ የአሸባሪው ጁንታ ጎራ በፍርሃት እንዲርድ አድርጓል፡፡
ሆኖም የህዝባችን አንድነትና ፅናት ለመሸርሸር ጠላት እየፈበረከ የሚረጨው አሉባልታዎችን መከላከል ፣ ሳያውቁ ጠላት ሆን ብሎ የሚለቀውን አሉባልታ በመቀባበል የጠላት ወኪል የሚሆኑ ወገኖችን መምከር ፣ መገሰፅ ያስፈልጋል፡፡
በአሸባሪው ህወሓት እየተፈበረኩ በማህበራዊ ሚዲያ የሚረጩ የውሸት መረጃዎችን ፣ በየአገልግሎት መስጫዎች የሚነዙ አሉባለታዎች ፣ ስለ ሠራዊታችን የግዳጅ ውሎ ሰው የሚቀባበለው ወሬ ለጠላት ግብዓት የሚሆኑና የወገንን እንቅስቃሴን የሚጎዱ ናቸው ነው ያለው፡፡
ስለዚህ ወገኖች ሁሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ጉዳዮችን በማህበራዊ ሚዲያና እርስ በርስ እንዳንቀባበል እና ሼር እንዳናደርግ እናሳስባለን፡፡
1.የመረጃ ምንጩ ያለታወቁ ቀልብ የሚስቡ መረጃዎችን ሼር ከመድረግ እንቆጠብ፤
2.የሠራዊታችን ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ፣ የሚጓጓዙ የጦር መሳርያዎች አይነትና ብዛት ፣ የሎጂስቲክስ ድጋፍ እንቅስቃሴዎችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ሚዲያ አንለጥፍ ፡፡ የህን የሚፈፅም ከተመለከቱም ያስቆሙ፤ ፍቃደኛ ካልሆነ ለፀጥታ ሃይሎች ወዲያው ይጠቁሙ፡፡
3.የጠላትን ትንኮሳን የመከላከል ሥራ በማህበራዊ ሚዲያ አንለጥፍ፤
4.አንዳንድ ዩ-ቲዩበሮች ለሽርፍራፊ ሳንቲም ብላችሁ ሰበር ! ሰበር ! እያላችሁ ምንጩ ያለታወቀና ያለተረጋገጠ አሉባልታ በመንዛት የወገናችሁንና የሀገራችሁን ጥቅም አሳልፋችሁ ለጠላቶቻችን አትስጡ፤
5.ወቅታዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት በታወቀ መንግስታዊ ወይም በሚመለከተው የመከላከያ ሃላፊ ወይም አዛዥ ያልተሰጠ መረጃ ከሆነ አንመን ፣ ሼርም አናድርግ፤
6.ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ በሰራዊታችን ግዳጅ አፈፃፀምና በህዝባችን ሞራልና ስነ-ልቦና የበላይነት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩና ጠላት ሆን ብሎ የሚለቃቸውን መረጃዎች ባለማሰራጨት እንተባበር ብሏል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በፌስ ቡክ ገጹ፡፡
13/01/2021
የመጨረሻው መጀመሪያ ‼️
አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች የሚገባቸውን ተሰጥተዋል።
የተደመሰሱት አመራሮች ፦
1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣
2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።
በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች ፦
1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ አሁንም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ~ ኢዜአ
02/01/2021
ደቡብ ዕዝ ከራያ አላማጣ ወረዳ መረዋ ቀበሌ እስከ ራያ ቆቦ ወረዳ ማህጎ ቀበሌ ድረስ 20 ኪሎሜትር የሚሸፍን የጠጠር መንገድ መገንባቱን አስታወቀ፣ የመንገዱ መገንባት ለአካባቢው ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል ።
የግንባታውን ሂደት ተዘዋውረው በመመልከት ከህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት የዕዙ ዋና አዛዥ ተወካይ ሜጀር ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ እንዳሉት ሰራዊቱ ዋነኛ ተልዕኮው ህግን ማስከበር ቢሆንም ከህዝብ የወጣና ራሱን ለህዝብ የሰጠ ሃይል በመሆኑ በህዝባዊ የልማት ስራዎች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነው ብለዋል ።
ህብረተሰቡ አንድነቱን በማጠናከር የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል ያሉት ዋና አዛዡ ከዚህ ጎን ለጎንም የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የሚጠበቅባቸውን አግልግሎት እንዲሰጡ ደህንነታቸውን መጠበቅና ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።
የማህጎ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ አለሙ ሞላ በበኩላቸው የቀበሌው ነዋሪ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ምንም አይነት አማራጭ የሌለው በመሆኑ በርካታ ወገኖቻችን በሞት አጥተናል፣ ብዙ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ይህም የሆነበት ምክንያት ቀበሌው ከራያ አለማጣ ወረዳ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ መንገዱ እንዲገንባ ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም በወቅቱ በነበረው የህውሃት አመራር ዘንድ ከፈለጋችሁ እርሻችሁ ውስጥ መሞት ትችላላችሁ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል ።
ለ30 አመታት ተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ ያላገኙት ነዋሪዎቹ አካባቢውን የተርሳ ቀበሌ ነው በማለት ይገልፁታል።
መከላከያ ሰራዊት ህዝባዊ ግዳጅ ተቀብሎ የዘመናት ጠላትችን ለመቅበር በሚጣደፍበት ሰዓት የእኛን ጥያቄ በማዳመጥ ለገነባልን መንገድ ደስታችን ወደር የለውም ያሉት ነዋሪዎቹ በግንባትው ምክንያትም በወሊድ ምክንያት የምትሞት እናት፣ በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት የሚያልፍ ህመምተኛ አይኖርም ለዚህም ክልብ እናመሰግናችኋለን ብለዋል ።
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በራያ ግንባር ተሰልፎ ጁንታው ከቀበረበት የህግ ማስከበር ማግስት ከዚህ ቀደም ያልታዩና በርካታ የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ቀበሌዎች በመለየት ህዝባዊ የልማት ስራዎችን በማከናውን ላይ ይገኛል ።
አበበ ሰማኝ
ፎቶ በአበበ ሰማኝ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Addis Ababa