DeritaTech Solution

DeritaTech Solution

Share

Photos from DeritaTech Solution's post 30/05/2026

ቴሌግራም Wallet በኢትዮጵያ የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊያቆም ነው!

በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌቴ (Wallet) ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም (ከ June 2, 2026) ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታወቀ።
ይህ ውሳኔ የተወሰደው የሀገሪቱን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርጎ እንደሆነም ይፋ ተደርጓል።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ሁሉም በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ትሬዲንግ ማስታወቂያዎች በሙሉ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ አዲስ ማስታወቂያዎችንም Post ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል።

ከቀነ ገደቡ በፊት የተጀመሩ ግብይቶች በተለመደው አሰራር መሠረት መፈጸም እንደሚቻል ና ተጠቃአሚዎች በሂደት ላይ ያሉ የትሬዲንግ ስምምነቶችን በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደምም ፦
- Bitget
- Binance
- Okx
- Bybit የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በP2P ግብይት በስፋት የሚታወቀው Telegram Wallet ከግንቦት 25,2018 በኋላ በኢትዮጵያ ብር መስራት እንደሚያቆም ታውቋል።

ቴሌግራም ዋሌትም ይሁን ሌሎች ከላይ የጠቀስናቸው በኢትዮጵያ ብር የክሪፕቶ ግብይት ለማቆማቸው እንደምያንያት የተገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የአቻ ለአቻ (P2P) የንግድ ልውውጥ ሕገ-ወጥ መሆኑን በመግለጹ ና ከብር ውጪ በቨርቷል ከረንሲ የሚደረጉ ግብይቶች ህጋዊ እንዳልሆኑ በቅርቡ የካቲት 27,2026 ላይ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ በማውጣቱ እንደሆነም ተነግሯል።

28/05/2026

የ2018ቱን ሚሊየን ሎተሪ ለቆረጣችሁ ፤ ዕጣው ዛሬ የወጣ ሲሆን ፤ 50 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው የአንደኛው ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 0630907 ሆኗል።

26/05/2026

ለውሮ ና ቡቺ አስተርጓሚ!

ድመቶቻችን ሚያው ሲሉ እና የውሾችን የጩኸት ድምጽ ስንሰማ ምን ማለታቸው እንደሆነ ለመረዳት የሚያስችል የቴክኖሎጂ መፍትሄ ከወደ ቻይና ብቅብሏል።

በቻይናዋ Hangzhou የሚገኝ Meng Xiaoyi የተሰኘ የቴክኖሎጂ startup ከአሊባባ ክላውድ (Alibaba Cloud) ጋር በመተባበር PettiChat የሚል ስያሜ የተሰጠው ና በኤአይ የተደገፈ Pet translator device አስተዋውቋል።

27.2 gram ብቻ የሚመዝነው ይህ አስተርጓሚ መሳሪያ በአንገታቸው ላይ በመታሰር የእንሰሳቱን ድምጽ ሪከርድ ለማድረግ ማይክ ያለው ሲሆን የሚያሳዮትን የአካል እንቅስቃሴ ደግሞ በMotion sensor እንዲሁም በAccelerometer በመረዳት እንደሚሰራ ተነግሯል።

መሳሪያው ይህን ሪከርድ ያደረገውን ድምጽና የአካል እንቅስቃሴ ለመተንተን ወይም ፕሮሰስ ለማድረግ የአሊባባ ክላውድን Qwen AI model የሚጠቀም ሲሆን ካምፓኒው የሰራሁት ተርጓሚ መሳሪያ የረሃብ ስሜት ፣ ፍርሃትን እና ደስታን ጨምሮ ከ20 በላይ ውሾች ና ድመቶች የሚያሳዩትን ስሜታዊ ሁኔታዎች እንስከ 95% በትክክል የመተጎም ብቃት እንዳለው ገልጿል።

ይህ አስተርጓሚ መሳሪያ በ799 yuan ወይም 118 ዶላር ገደማ ለገበያ ሊቀርብ እንደሚችል ና እስካሁን ባለውም በርካታ ትዕዛዞችን እየተቀበለ እንደሆነ ታውቋል።

15/05/2026

የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የ2026 የAI summer Camp ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል ፤ ከአንደኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ኤአይን ጨምሮ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ኮርሶች ልዩ የክረምት ስልጠና በነጻ ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል ።

በFundamentals of AI ፣ በProgramming ፣ በMachine Learning ፣ Robotics and IOT ፣በData science ና በሌሎችም የኤአይ ስልጠና ዘርፎች ፍላጎቱ ላላቸው ና መስፈርቱን ለሚያሟሉ ለመጪው ክረምት ስልጠና መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ለዚህ ስልጠና ለመመዝገብ ማስፈንጠርያውን በመጫን ና በgmail አድራሻችን በመግባት ና የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት መመዝገብ እንችላለን ፡ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf_0QSAISZUjQxEttCFVEBjbWtHrxYQo_XKle_vcqKREsAs9g/viewform

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa