Edil pictures

Edil pictures

Share

*አዲስ ዝማሬ* // ቤተኛም እንግዳም ማርያም // ጸጋ ሥላሴ(ዲ.ን) // New Mezmur By Tsega Silase 08/09/2022

-ተለቋል

https://youtu.be/lG5IE8NjsRI

ቤተኛም እንግዳም ማርያም
ግጥም፡-ዲ.ን አቤል ፈታ // ዜማ፡-ጸጋ ሥላሴ (ዲ.ን)// ድምጽ ቀረጻ፡-መለከት ስቱዲዮ // መሠንቆ፡-እንዳልካቸው አዱኛ // ክራር፡-ዲ.ን ይኹን ሰላም አሥራት // ዋሽንት፡-ኤልያስ ፍቃዱ // ቪዲዮ ቀረጻና ኤዲቲንግ፡-ሀብታሙ ተሾመ // አጃቢዎች፡- ዲ.ን በአምላክ ይልማ ፤ ዲ.ን አቤል ፈታ ፤ ዘማሪት ጸዳለ አማረ

ሔዋን ላላት እልፍኝ ለታላቁ አዳም
ለሰው ልጆች ኹሉ ላሉ በዚኽች ዓለም
ቤተኛም እንግዳም
ማርያም አንቺ ነሽ ፣ አንቺ ነሽ ማርያም

የዶኪማስ ተስፋ ሲጎድልበት ወይኑ
የንጽሕና ሙዳይ የኖኅ ቃልኪዳኑ
የአዳም ዘር ለምኖ አፍሮብሽ አያውቅም
በምልጃሽ የዳነው በሰማይ ከዋክብት ተሰፍሮ አያልቅም
ማርያም እመ ሕያዋን ዘትቀውሚ ለንጉሥ በየማኑ
እንግዳችን ነሽ በነጋ ቁጥር በየዘመኑ

ዳግማዊቷ ሔዋን የፍቅር ማኅደር
የመንግሥቱ መግቢያ አማናዊት በር
ርኅራኄ ልብስሽ ፍቅርም ልማድሽ ነው
በኃያል እምነትሽ ሥጋችንን ለብሶ አምላክን አየነው

ብንታረዝ ጸጋ ብንራብ ምግባችን
ቢጠማንም በአንቺ ይጠፋል ጥማችን
የጻድቃን ተስፋቸው እሙ ለአዶናይ
ተማጽነናል ባንቺ በሰጠሽ መሐላ ክፉ ሞት እንዳናይ

በፍቅሩ ስትጓዝ እስከ መስቀል ድረስ
መድኃኒት እናቱን የሰጠኽ ዮሐንስ
በቤታችን ፍቅርን እንድትሞላልን
እንግድነት ግባ ከልባችን ጠፈር ይዘሃት ድንግልን

#ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #መዝሙር

*አዲስ ዝማሬ* // ቤተኛም እንግዳም ማርያም // ጸጋ ሥላሴ(ዲ.ን) // New Mezmur By Tsega Silase #ማርያም #መዝሙር አዲስ ዝማሬ // ቤተኛም እንግዳም ማርያም // ጸጋ ሥላሴ(ዲ.ን) // New Mezmur By Tsega Silase ፡-ዲ.ን አቤል ፈታ // ዜ...

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Art

Website

Address

Addis Ababa